Connect with us

Ethiopia

ሌቦቹ ተለቀሙ!.. እሰየው ተፅናንተናል! | ጫሊ በላይነህ

Published

on

ሌቦቹ ተለቀሙ!..እሰየው ተፅናንተናል! | ጫሊ በላይነህ

ሌቦቹ ተለቀሙ!.. እሰየው ተፅናንተናል! | ጫሊ በላይነህ

የትላንቱ የዐቃቤ ሕግ መግለጫ አስደንጋጭ ነው። አንዳንዶቹ የሰብዐዊ መብት ጥሰቶች ባለፉት ዓመታት በአደባባይ ሲነገሩ፣ የመንግሥት አካላትም ፈጥነው ሲያስተባብሉት ከመኖራቸው ውጭ መንግሥታዊ ሽብሩ የማናውቀው አልነበረም። እነዚህ ወገኖች በአንድ በኩል ሕዝብን እያሰቃዩ በሌላ በኩል የአገሪቷን አንጡራ ሀብት ሲዘርፉና ሲያዘርፉ ኖረዋል።

ልብ በሉ!… ሕዝብን ለማገልገል ሥልጣን ላይ የወጡ ጥቂቶች እዚያው ወንበራቸው ላይ ቁጭ ብለው የአገሪቱን መሪ ለመግደል ያሴራሉ። ወንጀለኞችን አስታጥቀው ልከው ንፁሀንን ይገድላሉ።

በዐቃቤ ሕግ የትላንቱ መግለጫ መሠረት የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የተመራው በብሄራዊ መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ ኃላፊ ነው። ይህ ተቋም አገርንና ዜጎችን እንዲጠብቅ አደራ ያለበት ብቻ ሳይሆን በሕዝብና በመንግሥትም ከፍተኛ አመኔታ የተጣለበት ነው።

አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ይህን ሥልጣናቸውን ለግልና ለቡድን ፍላጎት በማዋል በአደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመግደል ተንቀሳቀሱ። የነገሩን ዱካ ለማጥፋትም በከፍተኛ ጥንቃቄ የአንድ ብሄር ሰዎችን ለእኩይ አላማቸው መልምለው አሰማሩ።

በዋንኛነት በፈጣሪ ድጋፍ እኩይ ሙከራቸው ባይጨናገፍ ኖሮ ይህችን አገር ወደማያባራ የእርስበርስ እልቂት ይከቷት ነበር። ዛሬ እነዚህ የወንጀል ተጠርጣሪዎች በሕዝብ ስም እየማሉ፣ እነሱን መንካት ብሔራቸውን መንካት መሆኑን በሚከፍሏቸው ብሎገሮች በኩል እያስነገሩ በነጻነት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ማሰብ ያማል።

የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በትላንቱ መግለጫው እንዲህም ማለቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

~ በህግ የማይታወቁ ስውር እስርቤቶች ነበሩ፤ በአዲስ አበባ ሰባት ቦታዎች በሌሎችም እንዲሁ ተገኝተዋል።
~ በሽብር ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎች በድብቅ እስር ቤት ይታሰሩ ነበር፤ ምክንያቱም በድብደባ ወንጀሉን ለማሳመን ነበር፤
~ ፖሊስ ጣቢያ፣ ማረሚያቤት እና ስውር እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በአሌክትሪንክ ሾክ ማድረግ፣ ብልትን በፒንሳ መሳብ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ ለረጅም ጊዜ ማቆየት፣ ጫካ ውስጥ አስሮ ማሳደር፣ ጥፍር መንቀል፣ በብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ አልፎ አልፎ ከአውሬ ጋር በማሰር ማሰቃየት ሲደረግ ነበር።

ጠ/ዐ/ህግ እንደገለፀው ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ 36 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። አሁንም በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ የተሸሸጉ አሉ። እነዚህ የወንጀል ተጠርጣሪዎች ተይዘው ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ግን ሩቅ አይደለም።

በሌላ በኩል የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን ከ2004 እስከ 2010 በነበሩት ጊዜያት ብቻ 37 ቢሊየን ብር የውጭ ግዢ ፈፅሟል።

እነዚህ ግዢዎች ዓለም አቀፍ ጨረታ ሳይፈፀምባቸው የተከናወኑ ናቸው።
ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መካከል እና በደላላ የተከናወነ ነው ተብሏል።

ከምንም በላይ የሜቴክ የበላይ አመራሮች ዝቅጠት ማሳያው የሕዝብን ገንዘብ ለመመዘበር ይሉኝታ እንኳን ማጣታቸው ነው።

በተለይ የመንግሥትና የግል ተቋሀማት ሠራተኞች ከእጅ ወደአፍ ከሆነ ወርሀዊ ገቢያቸው ላይ ቀንሰው ያዋጡት ገንዘብ የጥቂቶች ቀለብ ሆኖ መቅረቱ የሚያሳፍር ነው።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የጠላት አገር እንዲህ አይደረግም ያሉት ተጣርቶ የደረሳቸውን መረጃ ማመን አቅቷቸው ይመስላል።
የሆኖ ሆኖ የጠ/ሚ ዐብይ አስተዳደር ሌቦች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ብዙዎችን የሚያጽናና ሆኗል።

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close