Connect with us

Ethiopia

ኢሳያስም አላለም፤ ኢቴቪም አልዘገበም!

Published

on

ኢሳያስም አላለም፤ ኢቴቪም አልዘገበም!

ኢሳያስም አላለም፤ ኢቴቪም አልዘገበም! | በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን

ፈረንጆቹ post truth politics የሚሉት አስቸጋሪ ጉዳይ አለ፡፡ ይህ ድህረ-ዕውናዊ ፖለቲካ አንድ ን ጉዳይ ተከትሎ የሚመጣ ፈጠራና አሉባልታ ነው፡፡ በዚህ አሉባልታ ደግሞ ሕዝብም ይረበሻል፤ መንግሥትም በማስተባበያ ጊዜውን ይገድላል፡፡

ይህ ጉዳይ በተለይ እንደኛ ባለ ኋላ ቀር ማኅበረሰብ ውስጥ ጉልበት አለው፡፡ አሉባልታ ከእውነት ይልቅ እንዲታመን፣ሀቅ ቦታ እንዲለቅቅ የሚያደርገውን ቦታ ያገኛል፡፡ ምክንያቱም ማኅበረሰቡ ነገሮችን የሚያጣራበት አቅም የለውም፡፡ ከእኔ የተሻለ ተምረዋል የሚላቸውን ሰዎች ደግሞ የበለጠ ስለሚያምን ጉዳዩን ያራጋበቱን ሰዎች ያምናቸዋል፡፡

ሰሞኑን በዚህ መንገድ የተራገቡትን ጉዳዮች ብቻ ላንሳ፡፡ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጎንደርንና ባሕርዳርን መጎብኘቱ ይታወቃል፡፡ ጉብኝቱ የተከናወነው አርብና ቅዳሜ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ እስከ ቅዳሜ አመሻሽ ድረስም አቶ ኢሳያስ ምንም ዓይነት የአደባባይ ንግግር (public speech) አልነበረውም፡፡

አርብ ጠዋት ጀምሮ ግን፣ ‹‹ኢሳያስ እነ እንትናን ሰድቦ እኛን አወደሰን፤ እነ እከሌን እረግሞ እኛን መረቀ፤ እኛን አሞግሶ እነ አባ እከሌን አኮስሶ ተናገረ›› ተብሎ ወሬው ተራገበ፡ ፡ወሬውን የበለጠ ታማኝ ለማድረግ በአንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ ሥም ሐሰተኛ ድረገጽ ተከፈተ፡፡ ይህንን ቴሌቭዥን ዋቢ በማድረግም አሉባልታውን የሚታመን ለማድረግ ተሞከረ፡፡

ይህንን ወሬ የበለጠ እንዲራገብ ያደርጉ የነበሩት ደግሞ መንግሥት በምክንያት እና በማስረጃ ተማሪዎችን እንዲያፈሩ የቀጠራቸው አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በየቴሌቭዥኑ ፕሮፌሰርና ዶክተር እየተባሉ የሚቀርቡ በመሆናቸው ይህንን ንግግር አለማመን የቻለው የሕብረተሰብ ክፍል ከጥቂት በላይ ነበር፡፡

በዚህ በማኅበራዊ ድረገጽ ላይ ተሰራጭቶ ከፍተኛ ተቀባይነት ከነበራቸው የዚህ ሳምንት ሐሰተኛ ወሬዎች አንዱ ይህ ነው፡፡ሆኖም ግን ኢሳያስም እንዲያ አላለም፤ያ ቴሌቭዥን ጣቢያም ዘገበ የተባለው መቶ በመቶ ውሸት ነበር፡፡

ባሳለፍነው እሁድ ደግሞ እንዲህ ሆነ፡፡ በአዲስ አበባ የጎደና ላይ ሩጫ ተካሄደ፡፡ በኤርትራና ኢትዮጵያ ስም የተሰየመው ይህ ሩጫ፣ያለምንም ኮሽታ ተጠናቀቀ፡፡ ይሁን እንጂ ሐሰተኛ ወሬ በመፍጠር ሕዝብን ማስረበሽ የየዕለት ሥራቸው የሆኑ ሰዎች ሩጫው በደም የጨቀየ እንደሆነ አድርገው አቀረቡት፡፡

ኢቴቪን ዋቢ አድርገውም 89 ሰዎች እንደሞቱ አድርገው ፃፉ፡፡በሩጫ ውድድሩ ላይ መጨረሻ የወጣው ሳይቀር ይህንን አሉባልታ አመነው፡፡ምክንያቱም ምንጭ ተደርጎ የተሰራጨው አንድ ሜይን ስትሪም ሚዲያ ነዋ፡፡ ሆኖም ግን እንኳን ደም የፈሰሰበት ሊሆን እዚህ ግባ የሚባል ላብ የፈሰሳቸው ሰዎች በሌሉበት መድረክ ደም በደም የሆነ ውሎ ብሎ አሉባልታ መንዛት ሰውን ከማሸበር በላይ ከቶ ምን ሊሆን ይችላል፡፡

በንግስት ዘውዲቱ ጊዜ እንዲህ ያለ የፈጠራ ወሬ የሚያሰራጩ ሰዎች ሲበዙ ጊዜ አዋጅ ወጥቶ ነበር፡፡ ‹‹ማንም ሰው አላፊ ሊሆንበትና ዋቢ ሊያሳልፍ የማይችልበትንበ ወሬ ከሌላ ሰማሁ ብሎ ወይም ፈጥሮ ሲያወራ ቢገኝ ይቀጣል›› ይላል-ግንቦት 30 ቀን 1922 የወጣው አዋጅ፡፡

ከዚያ ጊዜ በኋላም አዋጁ ገቢራዊ ሆነ፡፡ ሐሰተኛ ወሬዎችም ያስ ቀጡ ጀመር፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን ከ89 ዓመታት በኋላም መሻሻል አላሳየንም፡፡ ዛሬም ከጥናት ይልቅ ለሀሜት ጆሮአችን ይሰላል፡፡ከሳይንስ ይልቅ አሉባልታ በልባችን ፈጥኖ ይነግሳል፡፡ የዘውዲቱን አዋጅ የሚያስመኝ ክፉ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ አሉባልተኛ ጊዜ!!

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የተለያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዝኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close