Connect with us

Lifestyle

በ40 አመቷ የ44 ልጆች እናት የሆነችውን ማርያም ናባታንዚን ተዋወቋት

Published

on

በ40 አመቷ የ44 ልጆች እናት የሆነችውን ማርያም ናባታንዚን ተዋወቋት

በ40 አመቷ የ44 ልጆች እናት የሆነችውን ማርያም ናባታንዚን ተዋወቋት | Bekky @diretube

በኡጋንዳዋ ሙኮኖ መንደር የምትገኘው ማሪያ ናባታንዚ በአፍሪካ እጅግ ወላዷ እናት ተሰኝታለች። ከእድሜዋ በላይ ልጆች እናት ባለቤት መሆኗ እርግማን ይሁን ምርቃት ግልጽ ባይሆንም ከ13 አመቷ ጀምሮ በርከት ያሉ መንታዎችን በመውለድ 44 አድርሳቸዋለች አሁን ላይ 38ቱ በህይወት ቢገኙም።

ማሪያ ናባታንዚ ኡጋንዳዊት ስትሆን ህይወት ለእሷ ከልጅነቷ ጀምሮ እጅግ አስቸጋሪ ነበር። ገና በልጅነቷ በእንጀራ እናቷ የመግደል ሙከራ ይደርስባት ስለነበር ገና በ12 አመቷ ከቤት ጠፍታ ወጣች። ምርጫም ስላልነበራት በ28 አመት ከሚበልጣት ሰው ጋር በትዳር ተጣመረች። ካሁኑ ልመጅ ብሏት ይመስል ከባሏ ከቀደሙ ሚስት ከተገኙ ልጆች በእድሜ የሚበልጧትን ጭምር ማስተዳደር ጀመረች።

በቅጽል ስሟም የመንቶች ማፍሪያ የምትሰኘው ማሪያ በ18 አመት የእርግዝና ህይወቷ 6 ባለ ሁለት፣ 4 ባለ ሶስት፣ እንዲሁም 3 ባለ አራት መንቶችን እንዲሁም ስምንት ልጆችን በነጠላ ወልዳለች። በ13 አመቷም ለመጀመሪያ ጊዜ ስታረግዝ የመጀመሪያ መንታ ስታገኝ በወቅቱ ደስተኛ ነበረች። ባለቤቷ እጅግ ያጎሳቁላት ስለነበር ከወለድኩለት ይወደኛል ብላ ታምን ነበር። ከዛም ባለፈ ስድስት ልጆች እንዲኖሯት ትፈልግም ስለነበር ባንዴ ሁለት ማግኘቷ አስደስቷት ነበር ኋላ እንዲህ ጉድ ሊያደርጋት። ግን ስድስተኛ እርግዝናዋ የ18 ልጆች እናት ነበር ያደረጋት። በህክምና ለመረዳት ሙከራ ብታደርግም ህክምናው ለህይወቷ አስጊ በመሆኑ ሊጠቅማት አልቻለም ነበር።

ይህ ሁሉ ሲሆን ባሏ ምንም ባያግዛትም በየቀኑ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራች ለልጆቿ የሚያስፈልገውን 3 ኪሎ የበቆሎ ዱቄት፣ 3 ኪሎ ስኳር እንዲሁም ሳሙናዎችን እየገዛች ብቻዋን እንደምታስተዳድራቸውም ታውቋል። 100 ሺህ የዩጋንዳ ሽልንግ በቀን ያስፈልጋት ነበር።

በአባቷ በርካታ ልጆች መውለድን በጂን እንደወረሰች የሚናገረው ሀኪሟ “አባቷ ከተለያዩ ሴቶች የወለዳቸው 45 ልጆች ነበሩት በርካቶቹም መንታ ነበሩ የሷ ግን ፈጽሞ የተለየ ነው“ ብሏል እጅግ ከመማረሯም የተነሳ በጎርጎሮስያውያኑ 2016 የማህጽኗን ውስጠኛ ክፍል ታስቆርጥና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማርገዝን ተሰናብታለች።

አስገራሚ የሆነው ባሏ ይሄን ሁሉ ስታልፍ አንድም ቀን አግዟት አስቧትም አያውቅም አልፎ አልፎ ብቻ ብቅ ይላል። ትልቁ ልጇም ሲጠየቅ “ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት ከ10 አመት በፊት በ13 አመቴ ነው። ብዙዎቹ ወንድሞቼና እህቶቼ ጭራሹን አያውቁትም ሲመጣም ጠጥቶና በጣም ረባሽ ሆኖ ነው ሁሌ እሱ መጥቶ እንደሄደ የማውቀው እናቴ ስለምትከፋ ነው” ብሎ ለዴይሊ ሞኒተር ተናግሯል።

ይህ ወሬም በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰማ በኋላ በጎ ፈንድ ሚ(Gofundme) አማካይነት 10000 ዶላር የተሰበሰበላት ሲሆን የዩጋንዳ መንግስትም በተወሰነ መልኩ ድጋፍ እንደሚያደርግላት ተሰምቷል።

ይሄ ሁሉ በህይወቷ ቢያልፍም ፈጣሪዋን ማመስገንን ግን አላገዳትም “በቻልኩት ሁሉ ሰርቼ ልጆቼ የሚበሉት አጥተው አያውቁም ለዚህም ፈጣሪ ይመስገን ትላለች።

Sours: Oddity central

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close