Connect with us

Ethiopia

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ጤነኛ ነውን?

Published

on

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ጤነኛ ነውን?

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ጤነኛ ነውን? | በጫሊ በላይነህ

ከከፍተኛ ይቅርታ ጋር!.. የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ጤንነት መጠራጠር መጀመሬን እናገራለሁ።

እኔ እስከማውቀው ድረስ ዶክተሩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው። ማክሰኞ ዕለት!… ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ካብኔውን ሲያዋቅር በፌስቡክ ገጹ “የአማራው ውክልና አንሷል” ብሎ ለመወንጀል የቀድመው አልነበረም። በዚህ ሐተታውም የአማራውን ሕዝብ ለክልሉ ገዥ ፓርቲ አዴፓ/ብአዴን ሲል ሐዘን ማስቀመጥ ፈለገ። በዚህ ብቻ መች አበቃና!..ለአማራ ክልል ገዥ ፓርቲ አዴፓ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጠ። ትዕዛዙ በአጭሩ አዴፓ/ብአዴን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሹመት ተቃውሞ በአስቸኳይ መግለጫ እንዲሰጥ የሚያዝ ነበር።

ዛሬ ደግሞ ጨርሶ ተቃዋሚ ፓርቲነቱን ረስቶ አዴፓ ተጎዳ ከማለት አልፎ የአዴፓ ከፍተኛ አመራር አንዱን በስም ጠቅሶ አለመሾሙ አማራውን ይጎዳል እያለ ማለቃቀሱን ቀጥሏል። ዶክተር ደሳለኝ ለቢቢሲ አማርኛ ከሰጠው ቃለምልልስ የሚከተሉት ነጥቦች ምልከታዬን ይገልፁታል።

“1. … ከ20 ካቢኔ አባላት 4 ወይም 5 አማራዎች አሉ። ይህም ብዙ የሚያስከፋ አይደለም። ያነሳሁት ጥያቄ ሆነ ተብሎ ጠንካራ የአዴፓ ተወካዮች ቦታ አልተሰጣቸውም ነው። ለምሳሌ በአዴፓ የማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ ላይ ከፍተኛ ድምጽ አግኝተው የተመረጡት ዶ/ር አምባቸው መኮንን ናቸው። ዶ/ር አምባቸውን እዚህ ካቢኔ ውስጥ አለማካተት ማለት ተሰሚነት ያላቸውን አዴፓዎች ሆነ ተብሎ ገሸሽ የማድረግ ስልት ነው።..”

“2. ..ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሾሙት ሰዎች የፖለቲካ ካፒታል የሌላቸው እና የፓርቲውም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ያልሆኑ ጭምር ናቸው። እነኚህ ሰዎች የአማራን ሕዝብ ፍላጎቶች እና ጥያቄዎች ማስከበር የሚችሉ መሆናቸው እርግጠኛ የማይኮንባቸው ግለሰቦች ናቸው። ከዚህ ቀደምም የማይታወቁ እና የፖለቲካ ዕውቅና የሌላቸው ሰዎች ናቸው። እኔም እንደ አንድ የአማራ ብሔርተኛ ድርጅት መሪ፤ ዐብይ አሕመድ አማራውን ከወሳኝ የፌደራል መንግሥት የሥልጣን ቦታዎች እንዲገለል እያደረገ እንደሆነ ነው የምረዳው።…”

“3. … ወሳኝ የሚባሉ የፋይናንስ፣ የዲፕሎማሲ፣ የመከላከያ፣ የደኅንነት፣ የውጭ ጉዳይ ውስጥ አንድም አማራ አለመካተቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገዳዳሪያቸውን ስልታዊ በሆነ መልኩ እያገለሉ እንደሆነ ያሳያል።..”

“4. …አምባገነን መንግሥታት የሚያደርጉት የሥልጣን ማደላደል እና ሥልጣን ጠቅልሎ የመያዝ እርምጃ ነው እያየሁ ያለሁት።..”

እኔ ደግሞ ለዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ጥያቄ አለኝ።

~ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢህአዴግ ነው። የኢህአዴግ አሰራር በሚፈቅደው መሠረት ካቢኔውን አዋቅሯል። ዶክተር አብይ ተቃዋሚዎችን የማማከር ግዴታም ውዴታም ነበረበት ወይ?

~ አብን የካብኔ ምርጫ ሂደቱን ከመተቸት በዘለለ በኢህአዴግ የውስጥ ጉዳይ ገብቶ፣ ዶክተር አምባቸው ካልተሾመ የሚለው በምን አግባብ ነው?

~አብን ለተቀናቃኙ አዴፓ ተጎድተሀል ብሎ ለመጮህ ይችላል ወይ?

ዶክተር ደሳለኝ የአማራው ህዝብ ተገቢውን ውክልና አላገኘም በሚል ጥቅል፣ አደገኛ የብሔር አጀንዳ ተንደርድሮ ዶክተር አምባቸው አለመሾሙ፣ አገርና ሕዝብ እንደተጎዳ አድርጎ ማቅረቡ የአእምሮውን ጤንነት ጥያቄ ላይ ከመጣል ያለፈ ውጤት የለውም።

(ከአዘጋጁ፡- ይህ ጹሑፍ የጸሐፊውን እንጂ የድሬቲዩብን ኤዲቶሪል አቋም አያንጸባርቅም)

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close