Connect with us

Law or Order

ሕግ ነክ ክብረወሰኖች

Published

on

ሕግ ነክ ክብረወሰኖች - ኪዳኔ መካሻ

ሕግ ነክ ክብረወሰኖች |  ኪዳኔ መካሻ በድሬቲዩብ

እነኚህን ሰባት ጉዳዮች አስገራሚ የህግ ጉዳዬችን የሚዘግበው ሀፍንግተን ፖስት ምንጭ ጠቅሶ በድረ ገፁ ላይ በአለማችን የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ መመዝገብ የነበረባቸው የአለማችን የሕግና የፍትህ ነክ ክብረ ወሰኖች ብሎ አስፍሯቸዋል።

1.በአለም ወጣቱ ዳኛ

ካሊፎርኒያ ውስጥ በ19 64 ዓ.ም የተወለደው ዳኛ ጆን ኤድዋርድ ፓይቶን የሁለተኛ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በቴክሳስ ግዛት ውስጥ በዳኝነት ሲሾም እድሜው ገና 18 አመት ከ11 ወራት ነበር።
ጆን እስከ መጋቢት 2003 ድረስ በዳኝነት ስራው ላይ ነበር።

2. የረጅም ዘመናት የሞት ፍርድ አስፈፃሚው

ዊሊያም ካርክራን ከ1792 እስከ 1871 ኖሯል። የሞት ፍርድን በገመድ ስቅላት ባስፈፃሚነት በኢንግላንዱ ኒውጌት ወህኒ ቤት የተቀጠረው በ1921ዓ.ም ነበር።

ለአርባ አምስት አመታት በስራው ላይ ሲቆይም 450 የሞት ፍርደኞችን አንገት በስቅላት መድረኩ ላይ ሸምቅቆ ገድሏል።
በስራ ውሉ ላይ የሟቾችን የግል ቁሳቁሶች የመውሰድ መብት ተሰጥቶት ስለነበር የሟቾችን የግል እቃዎችና ጌጦች ለአንድ ሙዝየም እየሸጠ ገቢ ያገኝ ነበር።

3. ለረጅም አመታት በጥብቅና

በቅፅል ስም “ሩቢይ” የሚባሉት ጠበቃ ሬዮቤን ላንዱ በ103 አመት እድሜያቸውም ስራቸውን አላቋረጡም ነበር።
በአረጋውያን እንክብካቤ ማእከል ውስጥ እያሉም በየቀኑ ጥቂት ሰአታትን ለካምብሪጅ ማሳሱቼትሱ ለዱና የጥብቅና ድርጅት በሙያቸው ያገለግሉ ነበር።

በ1918 ከህግ ት/ቤት ከተመረቁ ጀምሮ ለ86 አመታት በሙያቸው አገልግለዋል። በ1951 የልብ ህመምተኛነታቸውን ሀኪም ቢነግራቸውም እስከ እለተ ሞታቸው በሙያቸው አገልግለዋል ።

4. ፈጣኑ ፍርድ

በሀምሌ 22 1996 ዓ.ም የኒውዝላንዱ ፍ/ቤት ከህዝብ የተውጣጡ ጥፋተኝነትን ወሳኞች (ጁሪዎች) የማሪዋና ተክል በማብቀል የተከሰሰው ኒኮላስ ክራቬ ላይ ጥፋተኛ አይደለም ብለው ለመወሰን 1 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀባቸው።

5. ለብቻው ታሳሪ

ሞርዳቺ ቫኑን የተባለውን የቀድሞው የኒዩክሌር ቴክኒሽያን በ1978 እስራኤል ከሮም አግታ በሀገሯ ፍ/ቤት አቀረበችው።
የቀረበበት ክስ የእስራኤልን የቦንብ ፋብሪካ ግንባታ ሚስጥር ለለንደን ታይምስ ጋዜጣ በፎቶ አስደግፎ በመሸጥ ሀገር የመክዳት ወንጀል ነበር።በክሱ ጥፋተኛ ተብሎ በ18 አመት እስር እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።

ከዚህ የእስር ዘመኑ ውስጥ 12 አመቱን ስድስት ካሬ በስድስት ካሬ ክፍል ውስጥ ብቻውን ከታሰረ በሁዋላ ነበር፤ ቀሪ ዘመኑን ከሌሎች ታራሚዎች ጋር እንዲቀላቀል የተፈቀደለት።

6. አረጋዊው የባንክ ዘራፊ

በ80ዎቹ እድሜያቸው ወደ ወንጀል ህይወት የገቡት ጄ ኤል ሀንተር ከዛ በፊት በነበረው እድሜያቸው ጨዋ እና ብሎም የአንድ ኩባንያ ባለቤት ነበሩ።

በ76 አመታቸው ሚስታቸው ስትሞት ያገቧት የ31 አመቷ ሚስታቸው በነበረባት የአደንዛዥ ዕፅ ሱስ ችግር የተነሳ ወደ ግማሽ ሚሊዬን ዶላር እዳ ይገባሉ።ባንኩ እዳ ክፍያ ሲጠይቃቸው ነበር በ86 አመት እድሜያቸው ላይ የመጀመሪያውን ባንክ የዘረፉት።

ከአንድ አመት በኃላ ደግሞ በሌላ የባንክ ዘረፋ ላይ እያሉ ተይዘው ሶስት አመት በስር ቢቀጡም አዛውንቱ አልታረሙም።
በ91 አመታቸው ከአሜሪካ ፈርስት ባንክ በጠራራ ፀሀይ 1999 ዶላር ዘርፈው አመለጡ።

አዛውንቱ ዘራፊ ብዙም ጠንቃቃ ባለመሆናቸው በራሳቸው መኪና እረጋ ብለው
እየነዱ ነበርና ሚዘርፉት፤ ብዙ የባንክ ሰራተኞች ስላዩዋቸው በመጨረሻ ዘረፋቸው ላይ ተይዘው ተጨማሪ 12 አመት እስር ተፈረደባቸው። እዛው ወህኒ ቤት እያሉም ቅጣታቸውን ሳይጨርሱ ህዳር 1997 ከዚህ አለም በሞት ተሰናብተዋል።

7. አጭሩ ፍርድ

በእንግሊዝ የፍርድ መመዝገቢያ ላይ በቬርን ቅፅ ውስጥ በ1700 ዓ.ም እንደተሰጠ ተመዝግቧል።
የምንጊዜውም የአለማችን አጭሩ ፍርድ ባለ ዘጠኝ ቃላት ነው።

ፍርዱን የሰጡት የኢስኩየሩ ከ/ፍ/ቤት ዳኛ ቶማስ ቬርሞን እንደሆኑ ቢታ….መንም የተከራካሪዎቹ ማንነት ላይም ሆነ የክርክሩን ዝርዝርን በሚመለከት ፍርዱ በቂ መረጃ አይሰጥም።

ፍርዱ የተሰጠው የወቅቱን ጠበቆች ከጥንት ጀምሮ ሲያከራክር በነበረው የተሰናዳ ምግብ የቤት መገልገያ ቁሶች ውስጥ ይመደባል ወይስ አይመደብም በሚለው ጭብጥ ላይ ነበር።ፍርዱም…” የቤተሰብ መገልገያ ቁስ መባል የሚገባው የሚቀርብበት ሰሀን ነው” የሚል ነበር።

 

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** ኢትዮጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close