Connect with us

Ethiopia

“ህይወቱን ሊገብር ለወጣ ሰራዊት ገንዘብ ምኑ ነው ? “ጄነራል ሳሞራ የኑስ

Published

on

"ህይወቱን ሊገብር ለወጣ ሰራዊት ገንዘብ ምኑ ነው ? "ጄነራል ሳሞራ የኑስ

“ህይወቱን ሊገብር ለወጣ ሰራዊት ገንዘብ ምኑ ነው ? “ጄነራል ሳሞራ የኑስ  | ማዕረግ ጌታቸው  በድሬቲዩብ

የመከላክያ ስራዊት የደሞዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄ ጉዳይ ዘመናትን የተሸገረ ነው፡፡ ኢህአዴግ ሰልጣነ መንበሩን በያዘ ማግሰት በርካታ ታጋዮች የደሞዝ ጥያቄ አንስተው ነበር፡፡ ከእኛ ጋር የታገሉት ከተማ ገብተው የሚያገኙት ገንዘብና የእኛ የሚቀራረብ አይደለም ሲሉም አመጽ ሲዳዳቸውም ተስተውሏል፡፡ ይህ ዓይነቱ የ1980ዎቹ አጋማሽ ውጥረት ግን በአቶ መለስ ያላሰለሰ ጥረት በሰላም ተፈታ፡፡ ከዛሬው ይልቅ ነጋችሁ ጥሩ ይሆናል የሚል ቃልም ተገባላቸው ፡፡ ቃሉ ግን አልተተገበረም፡፡

በዚህ ምክንያትም የሰራዊቱ ዓባላት ዳግም የደሞዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄን ማንሳት ጀመሩ፡፡ የሰራዊቱ ኢታማዦር ሾም የነበሩት ጄነራል ሳሞራ የኑስ ወታደሩን ሲጎበኙ በየቦታው የሚነሳላቸውም ጥያቄ ይህ ብቻ ሆነ፡፡ ጄነራሉም ህይወቱን ሊገብር ለወጣ ሰራዊት ገንዘብ ምኑ ነው? “እያሉ ጥያቄውን በጥያቄ ሲመልሱ ኖሩ። በወቅቱ የሰሜን ዕዛ ዋና አዛዥ የነበሩትና የአሁኑ የጄነራል ሳሞራ የኑስ ተተኪ ጄነራል ሳዕረ መኮንን ግን የሰራዊቱ ደጋፊ ሁነው ከወቅቱ አመራር ጋር ሲላተሙ ቆዩ፡፡ ስራዊቱም ይህን ውለታ ይዞ ከሁሉም የጦር አዛዥች በላቀ መልኩ ጄነራል ሳዕረ ለእኛ ያደላል የሚል አክብሮት ውስጥ ገባ፡፡

ጠቅላይ ሚንትር ዓብይ አህመድ ጄነራል ሳዕረን ለኢታማዦር ሹምነት የመረጡበት (የመጀመሪያ ምርጫቸው አልነበሩም ቢባልም )አንዱ ምክንያተም ይህን ቅቡልነታቸውን በማየት መሆኑ አያከራክርም፡፡ የጄነራሉ በሰራዊቱ ውስጥ ያለቸው ተወዳጅነት ግን በጥቂት ጊዜያት ውስጥ መንገራገገጭ የገጠመው ይመስላል፡፡ ከወራት በፊት የኤርትራን ድንበር ልቀቅ የተበላው የሀገራችን መከላክያ ኃይል ከወታደራዊ ዲሲፕሊን ውጭ ማንገራገር ጀምሮ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ የሰራዊቱ ዓባላት ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊንን ጥሰው ቤተ መንግሰቱን በረጋግደው እስከ መግባት ደረሱ፡፡ የትናንቱ ወታደራዊ ትርምስ ብዙ የሴራ ትንትና የሚያሰጥ ቢሆንም ጋሃድ ያወጣው ነገር ግን የመከላክያ ኃይሉ የፈለገውን ለማድረግ አፍታም እንደማይወስድበት ማረጋገጡ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማረሪም የመከላክያው አደረጃጀት መዳከሙን አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያ መከላክያ ኃይል በጣም ጥብቅ ዲሲፕሊን ካላቸው ሀገራት ተርታ ውስጥ የሚካተት ሆኖ ለዘመናት ተጉዟል፡፡ ወደ ግዳጅ ከመሰማራቱ በፊትም የሚሄድበትን ተዕልኮ የማወቅ መብት ተሰጥቶት በዚህ አግባብ ሲሰራ ኑሯል፡፡ እንዲህ ያለው አሰራር ደግሞ አንድ የጦሩ አዛዥ ኑ ተከተሉኝ ብሎ ያሻውን እንዳያደርግ ያግደዋል፡፡ የወታደራዊ ሳንይንስ ምሁራን የኢትዮጵያ መከላክያ ኃይል ለመፈንቅለ መንግስት አይመችም የሚሉትም ከዚህ በመነሳት ነው፡፡ ትናንት ግን ይህን ዕውነት በሚሽር መልኩ በርካታ ሰራዊት በይፋ ተነጋግሮ በመምጣት የምኒልክነ ቤተ-መንግስት አስጨንቋል፡፡

ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?

የኢትዮጵያ የመከላክያ ደህንነት ከሲቪል አቻውም በላይ አስተማማኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከሀገር ውስጥ አልፎ በምስራቅ አፍሪካ የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችን ቀድሞ ለሀገራቱ መረጃ በመስጠትም አድናቆትን አትርፏል፡፡ በኬንያ ዌስት ጌት የገብያ ማዕከል የሽብር ጥቃት ሊሰነዘር መሆኑን ከሲ አይ ዔ በፊት ለኬንያ መንግሰት ሹክ ያለው የእኛው መከላክያ ድህንነት ነበር፡፡ በሱማሊያ የሚከሰቱ በርካታ የሽብር ጥቃቶችን አስቀድሞ በማምከንም ተወዳዳሪ የሌለው ተቋም መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ እንዲህ ከሆነ ቁጥሩ በርከት ያለ ሰራዊት በግልጽ ሲነጋገር፣ ከእነ ሙሉ ትጥቁ ከካምፕ ወጥቶ ወደ ምኒልክ ቤተ-መንግስት እንደሚያመራም አስቀድሞ ማወቁም የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

ይህን ተከትሎ የሚመጣው ጥያቄ ግን መረር ያለ ነው፡፡ የመከላክያ ደህንነቱ ሰራዊቱ ቤተ-መንግስት ድረስ ሂዶ የደሞዝ ጭማሪን እንደሚያቀርብ ካወቀ ለምን ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ (ጠ/ሚ ዓብይ) ለማሳወቅ አልቻለም?

ጄነራል ሳዕረ መኮንን አልያም ጄነራል ሀሰን (የመከላክያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ ) ተቀምጠው የፖሊሲ ኮሚሽነር ጄነራሉ ዘይኑ ጀማል ስለ ሰራዊቱ የትናንት ውሎ ሲያብራሩ መስማትን የመሰለ አሰገራሚ ነገር የለም፡፡ ጠቅላይ ሚንትሩም የተጋነነ የፖለቲካ ፈገግታ ሊያሳዩን መሞካረቸው የኮሜዲ ምሽት የታደሙ እንጅ ከወታደር ጋር የተወያዩ አላስመሰላቸውም፡፡ እናም ትናንት ምን አንደተካሄደ ለማወቅ አሁንም መረጃን ዕጠብቃለሁ፡፡

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** ኢትዮጵያን የተመለከቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close