Connect with us

Ethiopia

የአዲስ አበባ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ባለቤት አማራው ነው – የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ

Published

on

የአዲስ አበባ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ባለቤት አማራው ነው - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ

የአዲስ አበባ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ባለቤት አማራው ነው።

አዲስ አበባ የኔ ነች ብሎ መጠየቅ የሚችል አካል ቢኖር አማራው ብቻ ነው ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ገለጹ።

“የብሔር ፖለቲካ የሚፈጥረው የማንነትና የይገባኛል ጥያቄ ማለቂያ የሌለው ብጥብጥ ውስጥ ይከተናል አይበጀንም።” – ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ

ልደቱ አያሌው 2002 ዓ.ም እንዲህ ጽፎ ነበር …

የልደቱ አያሌው መድሎት መጽሐፍ ስለአዲስ አበባ

አዲስ አበባ መጀመሪያ የተቆረቆረችበት የፍልውሀ አካባቢ በወቅቱ “ፊንፊኔ” ይባል እንደነበር የሚያሻማና የሚያከራክር አይደለም።

ያ- ፍልውሃ አካባቢ ዛሬም ቢሆን ፊንፊኔ ተብሎ ቢጠራ ተገቢ ይሆናል።

ነገር ግን ከዚያች ፊንፊኔ ተብላ ትጠራ ከነበረው ጠባብ አካባቢ በንግስት ጣይቱ ስም የወጣላትና በምንሊክ ዘመን የተቆረቆረችው አዲስ አበባ ዛሬ በሁለንተናዊ መልኩ የሰፋች እና የገዘፈች በውስጧም ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች የመጣ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ሀብት ንብረት አፍርቶ የሚኖርባት የአገር ርዕሰ- ከተማ ነች።

ከተማዋ ከኢትዮጵያዊያን አልፋ ዛሬ የአፍሪካ መዲና በመባል የምትታወቅ ነች።

ይህችን የፊንፊኔ ዓይነት በሺህ የሚቆጠሩ ትናንሽ ሠፈሮችን ከመቶ አመት በላይ በሆነ የጊዜ ሂደት እያካተተች በመምጣት የአገር ርዕሰ- ከተማ ለመሆን የበቃችን ግዙፍ ከተማ የአንድ ጠባብ ሰፈር ወይም የፀበል ቦታ በሆነ “ፊንፊኔ” በሚል ለመጥራት መሞከር የተለየ የፖለቲካ ትርጉም ስላለውነው እንጂ ምንም ዓይነት የታሪክ ጭብጥ የለውም።

በዚህ ጉዳይ ላይ ሃቁን ደፍረን እንነጋገረው ከተባለ ለጉዳዩ ከጀርባው ምንም ዓይነት የፖለቲካ ትርጉም ሳይሰጡት በተለምዶ ጤናማ በሆነ መልኩ አዲስ አበባን “ፊንፊኔ” እያሉ የሚጠሩ ብዙ የኦሮሞ ተወላጆች የመኖራቸውን ያህል፣ አዲስ አበባ ከተማ በተለየ ሁኔታ “የኛ ነች” ከሚል ፖለቲካዊ አጀንዳ “ፊንፊኔ” የሚለውን መጠሪያ ሆን ብለው መጠቀም የሚፈልጉ የተደራጁ ኃይሎች መኖራቸው ግልፅ ነው።

ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ የሚያደርገውም አንድ ርዕሰ – ከተማ በሁለት ስም መጠራቷ ሳይሆን “ፊንፊኔ” በሚለው መጠሪያ ጀርባ ያለው የፖለቲካ አጀንዳ ነው።

ከየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ መጥቶ አዲስ አበባ ላይ ሕይወቱን የመሰረተው እና በተለያዩ የልማት መስኮች ጥሪቱን እያፈሰሰ የሚገኘውን በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ስጋት ውስጥ የሚከት እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ለኢኮኖሚ ዕድገታችን እንቅፋት ከመሆኑም በላይ በአገራችን ብሔራዊ መግባባት እንዳይፈጠርም የሚያደርግ ከፍተኛ ችግር ነው።

ስለዚህም ሁላችንም የአገራችን ርዕሰ – ከተማ አዲስ አበባ መሆኗን አምነን በመቀበል በሁለት ሳይሆን በአንድ መጠሪያ ልንጠራት ይገባል።

መንግስትም እንዲህ አይነቱን ሁኔታ በዝምታ ሊያየው አይገባም። የወቅቱን ሠንደቅ አላማ እና ብሔራዊ መዝሙር ሕዝቡ እንዲያከብረው ሁልግዜ ሲወተውት የሚደመጠውን ያህል ግለሰቦችን ማስገደድ አስፈላጊ እና የሚቻል ባይሆንም ቢያንስ ግን የአገሪቱን የመንግስት መዋቅሮች እና ሕጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች የአገሬቱ ርዕሰ- ከተማ አዲስ አበባ ተብላ የምትጠራ መሆኑን በተግባር እንዲያከብሩ ማድረግ ይጠበቅበታል።

(ልደቱ አያሌው:- መድሎት መጽሐፍ ከገጽ 38/39 የተወሰደ)

 

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close