Connect with us

Africa

‹ምስጢረኛው› የኢትዮጵያና የኤርትራ ስምምነት

Published

on

‹ምስጢረኛው› የኢትዮጵያና የኤርትራ ስምምነት

‹ምስጢረኛው› የኢትዮጵያና የኤርትራ ስምምነት | ያየሰው ሽመልስ በድሬቲዩብ

ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ዳግማዊ ፍቅር ከገቡ ቆዩ፡፡ አንድ ሶስት ወር ሊሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ሀገራት ሰሞኑን ደግሞ የጂዳ ስምምነት ተብሎ የሚጠራ አዲስ ውል አስረዋል፡፡ ውሉን በተመለከተ በኢትዮጵያ በኩል መደባበቅ ቢሞከርም ኤርትራዎቹ ይፋ አድርገውታል፡፡ አንድ የኤርትራ ባለሥልጣን በትዊተራቸው ላይ ውሉን ለጥፈውታል፡፡

የጂዳው ስምምነት ሰባት አንቀጾች አሉት፡፡

የመጀመሪያው አንቀጽ የጦርነት ጊዜ ማብቃቱንና የሰላምና የትብብር ዘመን መጀመሩን ይገለፃል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ ሁለቱ ሀገራት በፖለቲካ፣ በሰላም፣ በመከላከያ፣ በኢኮኖሚ፣በባሕል ወዘተ በቅንጅት እንደሚሰሩ ይገልፅና፣ የጋራ የኢንቭስትመንት ፕሮጀክቶችና የኢኮኖሚ ዞኖች እንደሚመሠረቱ የሚያትተውን አንቀጽ ሶስት ያስከትላል፡፡

አራተኛው አንቀጽ ደግሞ፣ አወዛጋቢውን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ እንደሚያስፈጽሙ ይደነግጋል፡፡

አምስተኛው፣ ሁለቱ ሀገሮች ቀጣናዊና አለማቀፋዊ በሆነ የሰላም የደህንነትና የፀጥታ ትብብሮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ያትታል፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርንና ሽብርተኝነትን በጋራ እንደሚከላከሉና እንደሚዋጉ የሚያትተው አንቀጽ ደግሞ ስድሰተኛው ነው፡፡

የመጨረሻው ደግሞ ሁለቱ ሀገራት ይህንን ስምምነት የሚያስፈጽም የጋራ ዓቢይ ኮሚቴና ንዑስ ኮሚቴ እንደሚያዋቅሩ አስቀምጧል፡፡

ይህ ስምምነት የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ ሕብረት አመራሮች በተገኙበት በአረቦቹ ፊታውራሪነት የተፈረመ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጠ ባለሥልጣን እስካሁን የለም-በሁለቱም ወገን፡፡

ለምሳሌ በአንቀጽ አራት ላይ የተቀመጠውና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ እንተገብራለን የሚለው ስምምነት አፈፃጸሙ እንዴት ነው የሚሆነው…? የሕዝቡ ሚና ምንድን ነው የሚሆነው…? እንደሚታወቀው ኤርትራ የመንግሥታቱ ድርጅትን ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ካባረረች በኋላ የድንበር ኮሚሽኑ አዲስ አበባ፣ አድግራትና አስመራ የነበረውን ቢሮውን ዘግቶ ወጥቷል፡፡

ኮሚሽኑ የወረቀት ሥራውን (Delimitation )ጨርሶ ገና ወደ ማካለል ሥራ (Demarcation ) ሳይገባ ነው በኤርትራ የተባረረው፡፡ እና አሁን ኮሚሽኑ እንደገና ይዋቀራል ማለት ነው…ይህንን ኮሚሽን ለማዋቀርስ ወጪው በማን ይሸፈናል…?ይህ ሁለቱን ሀገራት ለዳግማዊ ግጭት ላለመዳረጉስ ምን ዋስትና አለ…?


ይህ ስምምነት (የጂዳው ውል) የሚያነሳው ስለ ድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ ተፈፃሚ መሆን ብቻ ነው። ሆኖም ከድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ ጎንለጎን የካሳ ኮሚሽኑ ውሳኔም አለ። ውሳኔው ኤርትራ ለኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል የሚያስገድድ ነው። ኤርትራ እስካሁን ይህንን ገንዘብ እንዳልከፈለች ይታወቃል። ሆኖም አዲሱ ስምምነት ስለዚህ ጉዳይ ያነሳው ነገር የለም ።ለምን እንዳልተካተተም የተባለ ነገር የለም።

እነዚህን ነገሮች ሁሉ የሚያስከትል ነው-የሁለቱ ሀገራት ስምምነት አለመብራራት፡፡

ሌላው ትኩረት የሚስበው የሥምምነቱ አንቀጽ ሰባተኛው ነው፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያና ኤርትራ የ1990ውን ጦርነት ከማካሄዳቸው በፊት ተመሳሳይ የጋራ ኮሚቴዎችን አዋቅረው ነበር፡፡ ኮሚቴዎቹ ግን መደማመጥ ሳይችሉ ነገሩ ወደ ብሔራዊ ጦርነት ሄዷል፡፡

አሁንም ግን ስለኮሚቴ መታሰቡ አልቀረም፡፡ነ ገርዮውን አሁንም ያለ ሶስተኛ ወገን በራሳችን ኮሚቴዎች እንፈታዋለን የሚል ድምዳሜ ላይ የተደረሰ ይመስላል፡፡

ሆኖም ይህ አደገኛ ነገርን እንዳዘለ የሚተነብዩ ሰዎች አልታጡም፡፡ በዱሮው ኮሚቴ ውስጥ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የሁለቱን ሀገራት ጉዳይ የሚያስፈጽሙና አሁንም በኮሚቴው ውስጥ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁ ሰዎች በኤርትራ በኩል አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከዚያ ለጦርነት ከዳረገን አቋማቸው ስለመሻሻላቸው የታወቀ ነገር የለም፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ግን ከድሮዎቹ ተደራዳሪዎች አንድኞቹ እንኳን ወይ በሕይወት ወይ በሥልጣን ላይ የሉም፡፡ ታዲያ ይህ በሚን ሚዛን ነው ሊታይና ታሪካዊ ዳራውን ጠብቆ እንደሚሄድ የሚገመተው…ያልተመለሰ ጥያቄ ነው፡፡

ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ግን የሶስተኛ ወገንን ጣልቃ ገብነት ይመክራሉ፡፡ ይህ ስምምነት ሲፈጸምና ገቢራዊ ሲሆን የሚያማክሩ እና መሀል ቤት ሆነው ሊዳኙ የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከኤርትራም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር የጥቅም ግጭት የሌላቸው እንዲሆኑ ይመከራል፡፡

ሌላው በዚህ ሰሞነኛ ጉዳይ አጀንዳ የሆነውና መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው አቶ ኢሳያስ በዛላንበሳ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ጋር ሆነው የድንበሩን መከፈት ባወጁበት ዕለት ልጃቸው አብርሃም ኢሳያስ መገኘቱና፣ በጂዳ ስምምነቱ ሲፈጸምም በቦታው መኖሩ ናቸው፡፡

እንደሚታወቀው አብርሃም ኢሳያስ፣ በመንግሥት ውስጥ እዚህ ግባ የሚባል ስልጣን የለውም፡፡ የአየር ኃይል መሥመራዊ መኮንን ነው፡፡ ታዲያ አቶ ኢሳያስ ለምን በነዚህ ሁለት ወሳኝ የኢትዮጵያ ነክ ጉዳዮች ላይ ተገኙ…መልሱ አይታወቅም፡፡

ሌላኛው ጉዳይ በኤርትራ በኩል ያለው ለዘብተኛነት ነው። የኤርትራ ልሂቃን እንደሚሉት መንግሥታቸው ከኢትዮጵያ ጋር ስለገባበት ፍቅር ማብራሪያ እየሰጣቸው አይደለም። መረጃ እያገኙ ያሉት ከኢትዮጵያ በኩል ከሚሰጡ ማብራሪያዎች እንጂ የመንግሥት መገናኛ ብዙሀን እንኳ የረባ ሽፋን ሲሰጡት አይስተዋልም።

ከታች ሙሉውን የጂዳ ስምምነት የእንግሊዝኛ ቅጂ መመልከት ይችላሉ።

Full text of the agreement reached between Ethiopia and Eritrea a.k.a Jeddah Accord

The Two Parties agree as follows;-

Article One

The state of war between the two countries has ended and a new era of peace, friendship and comprehensive cooperation has started.

Article Two

The two countries will promote comprehensive cooperation in the political, security, defense, economic, trade, investment, cultural and social fields on the basis of complementarity and synergy.

Article Three

The two countries will develop Joint Investment Projects, including the establishment of Joint Special Economic Zones.

Article Four

The two countries will implement the Eritrea-Ethiopia Boundary Commission decision.

Article Five

The two countries will promote regional and global peace, security and cooperation.

Article Six

The two countries will combat terrorism as well as trafficking in people, arms and drugs in accordance with international covenants and conventions.

Article Seven

The two countries will establish a High-Level Joint Committee, as well as Sub-committees as required, to guide and oversee the implementation of this Agreement.
This Agreement is made at Jeddah, Kingdom of Saudi Arabia on this day of September 16, 2018 in two original copies in Amharic, Tigrinya, Arabic and English languages; in case of discrepancy in interpretation, the English version shall prevail.

** የቪዲዮ ዘገባዎችና መዝናኛዎችን ለማግኘት www.diretube.com ይጉብኙ
** የቴሌያዩ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ዜናዎችን ለእንግሊዘኛ ለማንበብ www.ethio.news ይጉብኙ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close