Connect with us

Ethiopia

የአብዮት ጋጋታ፡ ከመከረም 2-መጋቢት 24!

Published

on

የአብዮት ጋጋታ፡ ከመከረም 2-መጋቢት 24!

የአብዮት ጋጋታ፡ ከመከረም 2-መጋቢት 24! | በሬሞንድ ኃይሉ

ኢትዮጵያ አብዮት ያልተለያት ሀገር ናት፡፡ 1967 ዓ.ም በዛሬዋ ቀን ንጉሳዊው አስተዳደር በወታደራዊው ደርግ ተተካ፡፡ የደርግ አብዮት ግን ሌላ አብዮት የሚጠራ እንጅ ለሀገር የሚበጅ አልነበረም፡፡ ከሳይንሳዊ ሶሻሊዘም እሰከ ዲሞክራሲያዊ አብዮት የተጓዘው የዘመኑ ፖለቲካ አዕላፍትን ለመስዋዕት ከመዳረግ ውጭ የፈየደው ነገር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡ በርግጥ ደርግ መሰረታዊ የሚባል የመሬት አዋጅን በማውጣት ታሪክ የማይረሳውን አሰተዋጾ አብረክቷል፡፡ ከተቀናቀኞቹ ጋር ያለውን ልዩነት ለማጥበብም የአብሮ መስራት ግብዣ አቅርቧል፡፡ ይሁን እንጅ ከአንገት በላይ የነበረው የወታደራዊው መንግስት አብዮት አንድ ትውልድን እንደዋዛ ነጠቀ፡፡

በዚህ መኃል ብሄርን መሰሪያቸው ያደረጉ የትግራይ ወጣቶች ገጠርን መነሻቸው አድረገው ለሌላ አብዮት ወደ አዲስ አበባ ገሰገሱ፡፡ ተሳክቶላቸው የደርግን ዲሞክራሲያዊ አብዮት በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ለመተካት ቻሉ፡፡ የወታደራዊውን መንግስት ውርሶች ከመሰረታቸው የገረሰሰው ህውሓት መራሹ ኢህአዴግ በጅማሮው ዘመን ያሰባቸውን እያሳካ ወደፊት ተንደረደረ፡፡ አብዮታዊ የሚያስብለውን ስር ነቀል ስራም በተለያዩ መስኮች መተግበር ጀመረ፡፡

በትጥቅ ትግል ስልጣን የያዙ የአፍሪካ ወታደሮች ከሚያድረጉት በተለየ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሽግግር መንግስት መስርቶ ስልጣኑን አስረከበ፡፡ ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎችን ያሳተፈው ይህ ጎዳና ግን በጊዜ ሂደት ታቃውሞ እየበረከተበተ ሄደ፡፡ ኢህአዴግ አብዮታዊ ሁኖ ብቅ አለ አንጅ የተሳካለት አብዮተኛ ለመሆን አልታደለም፡፡ በዚህ የተነሳም የሚመራት ሀገር ለሌላ ለውጥ ተዘጋጀች፡፡ በ2008 ዓ.ም የተጀመረው ዝምተኛው አብዮትም በጊዜ ሂደት ገዥውን ፓርቲ መገዳደር ያዘ፡፡

በእኔ ግምት ከሁለት ዓመት የህዝብ ትግል በኋላ የተፈጠረው ለውጥ ሁለት መልኮች ያለው ነው፡፡ የመጀመሪያው የድህረ ዕውናዊ ፖለቲካ እንቅስቃሴ /post truth polticis / ምስራቅ አፍሪካ ደጃፍ መድረሱን ማስገንዘቡ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ሂደት በቀጠናው ነፍጥ አንግበው ለፖለቲካ ለውጥ ከሚታገሉ ኃይሎች በላቀ ማህበራዊ ድረ-ገጾችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ልሂቃን ውጤታማ መሆን መጀመራቸውን ያሳየ ነበር ፡፡ነገርየው ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ መንገድ ይልቅ የጁሃር መንገድ የተሻለ መሆኑን ለምስራቅ አፍሪካ በውሉ ማስመተማሩን ያስገነዝባል፡፡

ሁለተኛው ግን ውዝግብ የማይለየው ነው ፡፡ በተለየም በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ የቀለም አብዮት ሊባል ይችላል? በሚል ጥያቄም ይፈተናል ፡፡ በእኔ ግምት ዶ/ር አብይ በቀለም አብዮት ለስልጣን የበቃ ሰው ነው የሚል ሃሳብን መሰንዘር በርካታ ሙግት ያስነሳል፡፡ በመሆኑም ይህን መከራከሪያ ወደጎን አድረገን ሁለት መልክ ያለውን የዛሬው ዘመን አብዮት ጉዳይ ለመመልከት እንሞክር፡፡ ሀገራችን አሁን የምታዘግምበት አብዮት እንደቀደመው ዘመን በነፍጥ የመጣ አለመሆኑን ከላይ ለመጠቀስ ሞክሪያለሁ፡፡

ይህ ደግሞ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ አዲስ ታሪክን የሚፈጥር ነው ፡፡ እንዲህ ያለው የታሪክ ፈጠራ ግን ለነገው የፖለቲካ ጉዟችንም ወሳኝ መሆኑ አያከራክርም፡፡ የድሀር ዕውናዊ ፖለቲካ ሰደድ የትናንት ብቻ ሳይሆን የነገም መዳረሻችንን የሚወስነውም ለዚህ ነው፡፡ በፖለቲካ ልሂቁ የሚዘወረው የድህረ ዕውናዊ ፖለቲካ የነገ ዕጣ ፋንታቸንን የሚወሰን ብቸኛ ጉዳይ ግን አይደለም፡፡ በቅርቡ ፕሮፌሰር ብራሀኑ ነጋ የገለጸው የማህበረሰቡ ሞራላዊ ዕሴት እየተሸረሸረ መሄድም የወደፊቱን መንገድ ዳገት ያደርግብናል፡፡

ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች መበራከት፤ በዚህ መዘዝም ኢ ሰብአዊ በሆነ መልኩ የሰው ህይወት ማጥፋት እየተለመደ መሄዱ በኢትዮጵያ ታሪክ ውሰጥ አዲስ ታሪክ ብቻ የነገም ጉዟችን እንድነፈራ ያስገድደናል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ግን ባለፉት ጥቂት ወራት የተስተዋለው የመንግስት አመራሮችን የለውጥ ኃይል አድርጎ የማድረግ እሳቤ ለነገው ሀገር ግንበታችን ጥሩ ግብአት ይሆናል፡፡ ከጦርነት ሀንጎቨር የተላቀቀ ምስራቅ አፍሪካ ዕውን መሆንም ከማንም በላይ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ማድረጉ የማቀር ይመስላል፡፡

ጠቅላይ ሚንሰትር አብይ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የጀመሩትን አብዮት ከዳር ለማድረስ ትናንት ካባከናቸው አጋጣሚዎች በርካታ ጉዳዮችን መማር ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው በሀገራችን ተጀምረው የከሸፉት ሁሉም አብዮች አነሳሳቸው አሰደሳች የሚባል ነበር፡፡ በአስከፊነቱ ተወዳዳሪ የሌለውን ደርግን ለስልጣን ያበቃውን አብዮት ብንመለከተው እንኳን የመሬት ጥያቄን መልሶ ጉዞ መጀመሩ ለጭቁኖች ትልቅ ድል ነበር ፡፡ ነገር ግን እንደ አጀማመሩ ፍጻሜው የሚምር አልሆነም፡፡ አሁን እየተጓዝንበት የምነገኘው አብዮትም አጀማመሩ በአንጻራዊነት መልካም የሚባል ነው፡፡ ነገር ግን በርካታ ውስብስብ ችግሮች ያሉበትን ሀገር ወደ ሌላ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከአጃማመር ይልቅ በየወቅቱ የሚያስፈልጉ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ወሳኝ አስተዋጾ ይኖራቸዋል፡፡

መስከረም 2 1967 ዓ.ም ለ2011 ዓቻዋ የምታስተምረው ዕውነትም ይህ ነው፡፡ በጅምር ወዳሴ ሳይኩራሩ ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማምጣት መጣር፡፡ አብዮት ብርቅ ያለሆነባትን ሀገር ከአብዮት ጫፍ እንድትደርስ መደክም፡፡ ለሁሉም ዜጋ የምትበቃ ኢትዮጵያ መመስረት፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close