Connect with us

Ethiopia

አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ስለኢትዮጵዊነት ምን እያሉ ነው?

Published

on

አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ስለኢትዮጵዊነት ምን እያሉ ነው?

አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ስለኢትዮጵዊነት ምን እያሉ ነው? | ማረግ ጌታቸው

የሶማሌ ክልል ፖለቲካ ዳግም ወደታች እየተንደረደረ ነው፡፡ የዘመን ቁልቁለቱ 27 ዓመት ወደኋላ ይመልሰናል፡፡ 1983 ዓ.ም ላይ ሶማሌ ኢትዮጵያዊ ነው አይደለም የሚል የማነነት ፖለቲካ ውስጥ የገቡት የክልሉ ልሂቃን፣ አሁንም እንዲህ ያለው መንታ መንገድ ላይ መቆማቸውን መናገሩ ስህተት አይመስለኝም፡፡

በቅርቡ እዚ ገጽ ላይ ለማቅረብ እንደሞከርኩት የሶማሌ ፖለቲካ ፌርማታው የት እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ለዚህ ደግሞ መሰረታዊው መነሻ የክልሉ ፖለቲካ ልሂቅ ህገ-መንገስታዊ የሆነውን የራስን ዕድል በራስ መወስን እሰከ መገንጠል መበት መጠቀም መፈለጉ ነው፡፡

በ1987 ዓ.ም ምርጫ በክልሉ አብላጫ ወንበር ያገኘው ኦብነግ ከጥቂት የማስተዳደር ሙከራ በኋላ የክልል ምክር ቤቱን ሰብስቦ የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል መብቱን ለመጠቀም ውሳኔ አሰለፈ፡፡ በክልሉ ህዝበ ውሳኔ ሊያካሂድ አንደሆነም ለፌደራል መንግሰቱ አሳወቀ፡፡ በዚህ ሳይወሰንም የክልሉ ሰንደቅ ዓለማ የታላቋ ሶማሊያ ሪፐብሊክ መለያ የሆነውን የኮከብ ምልክት እንዲኖረው ከመግባባት ላይ ደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት አቶ መለስ በኦብነግ የፖለቲካ ቁማር እንደተበለጡ ስለገባቸው የሀሳቡን አራማጆች ጠራርገው ከክልሉ ማሰወጣትን መረጡ፡፡

የሶማሌ ክልል ፖለቲካ ቴርሞ ሜትሩ ሰንደቅ አላማ ነው፡፡ ከፊሉ ወገን በክልሉ ሰንደቅ ውስጥ አንድ የኮከብ ምልክት መስፈር አለበት የሚል ሀሳብ ይሰነዝራል፡፡ የዚህ ሀሳብ አራማጆች የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን የታላቋ ሶማሊያ ሪፐብሊክ አንድ አካል አድርገው የሚቆጥሩ ናቸው፡፡

የሶማሊያ ሪፐብሊክ ከቀኝ ግዛት ከተላቀቀች በኋላ ባለ 5 ኮከብ ሰንደቅአላምን መጠቀም ጀመረች፡፡ የአምሰቱ ኮከቦች ትርጉምም በአምሰት ሀገራት የሚኖሩትን የሶማሊያ ጎሳ ተወላጆ ሁሉ አንድ ሶማሊያን ይገነባሉ የሚል ተስፋ ነው፡፡

በኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሌላንድና ዋናዋ ሶማሊያ የሚገኙትን የሶማሌ ጎሳ ተወላጆች አንድ መሆን የሚሰብከው የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ለዛያድ ባሬ የኢትዮጵያ ወረራ መነሻ የሆነውም ከዚህ የተነሳ ነበር፡፡

ዛያድ ባሬ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወደ እናት ሀገሩ ሶማሊያ መመለስ አለበት የሚል ትልቅ ሙግት ሲከፍት ኑሯል፡፡ በሶማሊያ ሪፐብሊክ ሰንድቅ ላይ የተወከለውን የኢትዮጵያ ሶማሌን ግዛት ወደ እናት ሀጋሩ እመልሳለሁም ብሎ ጦርነት አካሂዷል፡፡ እንዲህ ያለው የታላቋን ሶማሊያ ሪፐብሊክን የመመስረት ዕሳቤ ግን ሶማሊያ ውስጥ ብቻ የታጠረ አይደለም፡፡ በዚህ ምክንያትም በሶማሊያ ሰንደቅአላማ ላይ መወከላቸውን ወደው በየአከባቢያቸው ሰነድቅ ላይ አንድ ኮከብ እየጨመሩ የሚታገሉ የነጻነት ቡድኖችም በርካታ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንገስት ራስን በራስ የማሰተዳደር መብትን ካቀናጀው በኋላ የራሱን ሰንደቅ አላማ ሲፈጥር ኮከብ አንዲኖረው አድርጎ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ አቶ መለስ እናነት ጥንትም ዛሬም ኩሩ ኢትዮጵያዊ እንጅ የሶማሊያ ሪፐብሊክ ተለጣፊ አይደላችሁም የሚል ማባብያና ቁጣ ከሰጡ በኋላ የኮከቡ ምልክቱ ከሰንደቁ ላይ ተንሰቶ በግመል ተተክቷል፡፡

የአብዲ መሐመድ ዑመር ወደ ክልሉ መሪነት መምጣትም ክልሉን ፍጹም ኢትዮጵያዊ በማድረግ በኩል የተሻለ ስራን ስርቷል፡፡
አብዲ የሶማሌ ክልል የሚለውን ስያሜ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሚል የተካ ሲሆን ሁሉም የሶማሌ ጎሳዎች የሚኖሩባት ሀገር ኢትዮጵያ እንጅ ሶማሊያ አይደለችም የሚል ትርክት በመፍጠር የክልሉን ተወላጅ ኢትዮጵያዊነቱን በማያወላውል መልኩ እንዲቀበል ለማድረግ ጥሯል፡፡

የሶማሌን ክልል ፖለቲካ ሙቀት የሚጠቁመው የሰንደቅ ጉዳይ አሁን አዲስ መነታረኪያ ሁኗል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መሰተዳደር በማህበራዊ ድረ-ገጻቸው የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ ሰለመቀየሩ ይፋ አደርገዋል፡፡ የእሳቸው አመራር በክልሉ ሰንደቅ ላይ የነበረውን የግመል ምልክት አንስቶ የኮከብ ምልክት እዲጨመር ውሳኔ ማሳለፉን ገልጽዋል፡፡ ይህ ደግሞ ክልሉ በይፋ የታላቋ ሶማሊያ ሪፐብሊክ ቅርንጫፍ መሆኑን አረጋገጠልን ማለት ነው፡፡rip ኢትዮጵያዊነት!

መደመር የሚሉትን የፖለቲካ ትርክት መነሻ ያደረገው የሶማሌ ክልል ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ሊመንን ጉዞ ጀምሯል፡፡ ያሰበው ቦታ ስለመድረሱ ግን ማንም እርግጠኛ አይደለም፡፡

 

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close