Connect with us

Law or Order

እና ምን ይጠበስ? ላለመታሰር ዘሯን የጠቀሰችው አስገራሚ ሴት

Published

on

እና ምን ይጠበስ

እና ምን ይጠበስ? | ኪዳኔ መካሻ – የህግ ባለሞያ በድሬቲዩብ

ላለመታሰር ዘሯን የጠቀሰችው አስገራሚ ሴት።
ኤልዛቤት ከትሻው የ32 አመት የቤት አሻሻጭ ሰራተኛ ነች።

ታዲያ ከሰሞኑ አቁም የሚለውን የትራፊክ ምልክት ጥሳ በሰአት 60 ኪ.ሜ ስትከንፍ አሜሪካ፣ ደቡብ ካሮሊና፣ ብሉፍቶን ከተማ ውስጥ ያየቻት ፓሊስ ተስቆማታለች።

ፖሊሷ ጠጋ ብላ ስታያት ኤልሲ አይኖችዋ ፈዘው፣ ፊቷ ፍም መስሎ አፏንም ያዝ እያደረጋት ነው። ፖሊሷ ጠርጥራ ትንፋሿን ስትመረምረው የደሟ የአልኮል መጠን 0.18% ሆኗል።

ጥንብዝ ብላ እየነዳች ስለደረሰችባት፤ ፖሊሷ በይ ወደ ጣቢያ ስትላ ፤ ት/ቤት የልጃገረዶች መሪ፣ የተዋጣልኝ ዳንሰኛ ስለነበርኩ እና እጅግ ከተከበረ ዩንቨርስቲ ስለተመረኩኝ ልታስሪኝ አይገባም ብላ ትላታታለች። በዚህ ብታበቃ ጥሩ ለዜናም ባልበቃች ነበር።

ፓሊሷ አልሰማ ብላ እጇን የሃኋሊት አስራ ስትወስዳት” ዘሬ ኩልል ያለ የጠራሁ ነጭ ሴት፣ እንዴት ልታሰር ጠጥቶ በመንዳት!” እንዳለቻት ፖሊሷ አሳፋሪ የዘረኝነት ምክንያቷን የእለት መዝገቧ ላይ አስፍራዋለች።

“እና የሆንሽ እንደሁ ምን ይጠበስ!?” ስል ጠየኳት ብላለች እንደሷው ነጯ ፓሊስ።

“እንደ ፓሊስነትሽ ምን ማለቴ እንደሆን ማወቅ ነበረብሽ። እዚህ በሚመጡ ሰዎች ላይ ተመስርተሽ ማወቅ አለብሽ። ፍቅረኛዬም ፓሊስ ነው፤ የሱን ቤት በማፈላለግ ላይ እያለሁ ነው ያስቆምሺኝ” እያለች ያዝ በሚያደርገው የስካር አነጋገሯ እንደነገረቻት ፖሊሷ ገልፃለች።

ሁለት ብርጭቆ ወይን ብቻ መጎንጨቷን ምትናገረው ኤልሳ ልደቴ ስለነበር ነው የጠጣሁት ብትልም፤ ምን ያህል ብርጭቆውን ሞልታ ብጠጣ ይሆን ይህን አሳፋሪ አነጋገር ያናገራት?

በመኪናዋ ውስጥ በተደረገ ፍተሻም ማሪዋና እና የመጠቅለያ ወረቀቱ ተገኝቶባታል። አደንዛዥ እፅም ተጠቅማ እንደሚሆን ፓሊስ ይገልፃል።

ኤልሳ አሳፋሪ አነጋገሯ ሳያድናት፤ ጠጥቶ እና ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር ብሎም አደንዛዥ እፅ ይዛ በመገኘት ክስ ቀርቦባት ወህኒ ወርዳለች።

“ላለመታሰር እንዲህ አይነት ነገር የሚናገር ሰው በስራ ቆይታዬ አጋጥሞኝ አያውቅም የስካሯን መጠን የሚያሳይ ነው” ብላለች አስገራሚና የዘረኝነት አነጋገሯን ያጋለጠችው ፖሊስ ።

እኔ ደግሞ ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል ብዬዋለሁ።

ኤልሳ ጨብሳ ስታሽከረክር ስትያዝ የተናገረችውና ሰክራ ነው እንጂ በጤናዋ አይደለም የተባለላት ለዜና ያበቃት የዘረኝነት አነጋገር፤ ህግም ብጥስ በዘሬ የተነሳ በተለየ አይን ልታይ ይገባል የሚለውን ኋላ ቀር አመለካከቷን አሳብቆባታል።
ዘገባውን ትላንት ያስነበበን አሶስዬትድ ፕሬስ ነው።

ይህ አስገራሚ ዘገባ የተዘገበው፤ አንድ ቁምነገር ስለሚያስተላልፍ ነው፤ ከዘር አንፃር የተቃኘ አስተሳሰብ እስከምን እንደሚደርስ ያሳያል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደምንታዘበው በሀገራችንም ዘርን መሰረት ባደረገ ፖለቲካም ሆነ የግል እና የቡድን አስተሳሰብ፤ በሆነ ባልሆነው ዘራቸውን ወይም የሌላውን ዘር የሚያነሱትን እና አላግባብ ለመጠቀሚያነት ወይም ከተጠያቂነት ለማምለጫነት ሊያውሉት የሚሞክሩ አሉ።

እነኚህን ዘራቸውን አላግባብ የሚጠቀሙ ሰዎች፤ ልንነቃባቸውና እንደ ፖሊሷ “እና ምን ይጠበስ!? ሕግ ሕግ ነው ከህግ ፊት ሁላችንም እኩል ነን” ልንላቸው ይገባል።

ምክንያቱም አለምአቀፍ ተቀባይነት ባለውና በሕገመንግስታችንም በተሰመረበት መርህ መሰረት፤ ሰው ሁሉ ከህግ ፊት እኩል ነው። ማንም ሰው በዘሩ፣ በቋንቋው፣ በፆታው፣ በሀይማኖቱ፣ በማህበራዊ ደረጃው በፖለቲካ አመለካከቱ አድሎ ሊደረግበት ወይም ሊደረግለት አይገባም።
ታዲያ ከሰሞኑ አቁም የሚለውን የትራፊክ ምልክት ጥሳ በሰአት 60 ኪ.ሜ ስትከንፍ አሜሪካ፣ ደቡብ ካሮሊና፣ ብሉፍቶን ከተማ ውስጥ ያየቻት ፓሊስ ታስቆማታለች።

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close