Connect with us

Ethiopia

መረጃ አዘል ጥያቄ | የጠ/ሚኒስትር አብይን ጉድለቶች ቢያሳዩን?

Published

on

“ ዶ/ር አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማት ይገባቸዋል” -ኤን ቲቪ

መረጃ አዘል ጥያቄ | የጠ/ሚኒስትር አብይን ጉድለቶች ቢያሳዩን?

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ የኢትዮጽያ ጠ/ሚ ሆነው ተመርጠው ቃለመሀላ ከፈጸሙ ዛሬ 100 ቀን ሞላቸው፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ባለፉት 99 ቀናት ያከናወኑዋቸው ተግባራት በተመለከተ በርካታ ወገኖች (ሚዲያዎችን ጨምሮ) አዎንታዊ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ ምናልባት በእነዚህ ቀናት መስራት እየተገባቸው ያልሰሩት ወይንም በሰሩት ስራ ያልረኩበት ካለ ሃሳብዎን ቢሰጡን? (በጨዋ ደንብ ለሚሰጡን ሀሳብ ምስጋናችን የላቀ ነው)

=

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ 100 ቀናት!

ዶ/ ር አብይ አሕመድ የኢትዮጽያ ጠ/ ሚ ሆነው መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ቃለ መሐላ ከፈፀሙ እነሆ በዛሬው ዕለት (ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ም) 100 ቀናትን ደፈኑ። በእነዚህ ቀናት ካከናወኙዋቸው በርካት ተግባራት መካከል የሚከተሉት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
1. ኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ በወሰነው መሠረት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የነበረው የድንበር ግጭት እልባት እንዲያገኝ አድርገዋል፡፡ ከ20 ዓመታት ቁርሾ በኋላ ባለፈው ሳምንት እሁድ ዕለት ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በአስመራ ከተማ ሲገኙ ፕሬዚደንት ኢሳያይስ አፈወርቂን ጨምሮ ከፍተኛ የኤርትራ መንግሥት ባለስልጣናት እና የኤርትራ ሕዝብ ደማቅ አቀባባል አድርገውላቸዋል፡፡ ሠላሙን ማስቀጠል የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነትም ሁለቱ መሪዎች ተፈራርመዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት የተጀመረ ሲሆን የኢትዮጽያ አየር መንገድ መደበኛ በረራውን ከሐምሌ 17 ቀን 2010 ዓ. ም ጀምሮ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

2.ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሕመድ ባለፉት 100 ቀናት በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ተጉዘው ከመሪዎችና ከሕዝብ ጋር ስኬታማ ምክክር አድርገዋል፡፡ ከተጓዙባቸው የውጭ አገራት መካከል በሱዳን፣ በጅቡቲ፣ በሳዑዲ ዓረቢያ፣ በግብጽ በተለያዩ ምክንያቶች በእስር ላይ የሚገኙ ወገኖች እንዲፈቱ ከአገራቱ መሪዎች ጋር በደረሱት ስምምነት መሠረት በመቶዎች የሚቆተሩ ወገኖች የነጻነት አየር መተንፈስና ወደአገራቸውም መመለስ ችለዋል፡፡ ይህ ድንቅ ስራ እጅግ በርካታ ወገኖችን ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል፡፡

3. ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባለፉት 100 ቀናት ከወሰዱት ተጨማሪ እርምጃዎች መካከል የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ማንሳት ይገኝበታል፡፡ አዋጁ ባለፉት ጊዜያት ከታየው የሕዝባዊ ተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ በመደበኛ ሁኔታ የአገሪቱን ላም ማስጠበቅ አልተቻለም በሚል ወጥቶ ስራ ላይ የዋለ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አዋጁ ከተነሳ በሃላ አንጻራዊ ሠላም ሰፍኗል፡፡

4. በክልሎች እና የፌዴራል መንግሥታቱ ሥር የተያዙ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ማድረጋቸው በተለይም የግንቦት ሰባት ሁለተኛ ሰው የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከመፍታት በተጨማሪም በጽ/ ቤታቸው በክብር ማነጋገራቸው በሰላም ወዳድ ወገኖች ታላቅ አድናቆትን አትርፎላቸዋል፡፡

5. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “አሸባሪ” ተብለው የተፈረጁትን ግንቦት 7፣ ኦነግ እና ኦብነግ ፍረጃ እንዲነሳ አድርገዋል፡፡

6. በውጭ አገር የሚኖሩ ዜጎችና የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎች ወደአገር ውስጥ ገብተው በሠላም እንዲታገሉ በተደጋጋሚ ባደረጉት ጥሪ መሠረት መግባት ጀምረዋል፡፡

7. የፕረስ ነጻነት እና የሃሳብ ብዝሃነት እንዲከበር በተደጋጋሚ ባነሱት ሃሳብ መሠረት የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጽያ ቴሌቭዥንን ጨምሮ የሚደነቅ የይዘት ለውጥ (መሻሻል) ማድረግ ችለዋል። ተቀማጭነታቸውን በውጭ አገር ያደረጉ ሚዲያዎች እንዲከፈቱ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ በዚህም በመበረታታት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ በአዲስአበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለመክፈት በቅቷል፡፡

8. የፀረ-ሽብርተኝነት፣ የሲቪል ማኅበራት እና የመገናኝ ብዙሃን የመረጃ ነጻነት አዋጆችን ለማሻሻል ኮምቴ ተዋቅሮ ሥራ መጀመሩ በአዎንታ የሚወሰድ ነው፡፡

9. በቀጣይም የፍትሕ አካላትን (ማለትም ፍርድ ቤቶችን፣ ፖሊስ፣ ደኅንነት እና መከላከያ)፣ በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ ብዙኃን መገናኛዎችን እንዲሁም ምርጫ ቦርድን ለሕዝብ እና ሕገ መንግሥቱ ወገንተኛ እንዲሆኑ በማድረግ መልሶ ማዋቀር ለማከናወን ዕቅዶች መኖራቸው የሚበረታታ ነው፡፡

10. የጠ/ሚ አብይ አሕመድ አመራር ለመደገፍና እስካሁን ለተሰሩ ሥራዎች ዕውቅና ለመስጠት አዲስአበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቁ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ በተለይ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስአበባ የተካሄደውን ሰልፍ ለማደናቀፍ ታስቦ የተወረወረ ቦምብ ንጹሐን ወገኖቻችን መጎዳታቸው በአስከፊነቱና በነውረኝነቱ በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ ሆኗል፡፡

11. ሚኒስቴሮች ብክነትን ለማስወገድ ከሰኞ እሰከ አርብ የሚካሄዱ ስብሰባዎቻቸውን ወደ ቅዳሜና እሁድ እንዲያሽጋግሩ እንዲሁም አላስፈላጊ ተደጋጋሚ የውጪ ጉዞዎችን ከማድረግ እንዲቆጠቡና እነዚህን መተላለፍ ቀይ መስመር ነው በማለት ጥብቅ ማሳሰቢያ የሰጡትም ባሳለፍነው 100 ቀናት ውስጥ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ጠ/ሚ የሚመሩት የካቢኔ ስብሰባ ወደቅዳሜ የተዛወረ ሲሆን በአንዳንድ መንግሥታዊ ተቋማት ለስብሰባ የሚጠፋ ስራ ጊዜ እንዲቀንስ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

12. ጠ/ሚኒስትሩ ካቢኔያቸውን እንደአዲስ ከማዋቀራቸው በተጨማሪ በተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት የነበሩ አመራሮች ሹም ሽር አድርገዋል፡፡ አንዳንዶችን በጡረታ አሰናብተዋል፡፡ በተለይ በሙስናና ብልሹ አሰራር የሚጠረጠሩ ተቋማት መሪዎች “ከቦታቸው መነሳታቸው ብቻ አይበቃም፣ ለምን አይከሰሱም” የሚል የሕዝብ ጥያቄ ከመኖሩ በስተቀር ሹም ሽሩ በሕዝብ ዘንድ በአዎንታ የተወሰደ ነው፡፡

 

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close