Connect with us

Art and Culture

በታላቁ ቤተ መንግሥት ቅጥር ግቢ ያየነውን እንመሰክራለን …

Published

on

ያየነውን እንመሰክራለን

ያየነውን እንመሰክራለን … ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሀገራችን ከያኒያን ጋር ያደረጉት ቆይታ የሁሉንም ስሜት ያረካ ነበር | ሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

አስቴር በዳኔ አዳራሹን ለቃ ስትወጣ አይቻለሁ፡፡ 

እዚህ ብቅ ብለው የቅርብ ሰው ነኝ የሚሉ ሰዎችን ጠቅላያችን አስጠንቅቀዋል፡፡ ሁላችሁም ለእኔ እኩል ናችሁ ብለዋል፡፡ 

የአንዳንድ አርቲስቶች ዳግም በዚህ የመደመር ዘመንም መታየታቸው ሊኮነን እንደማይገባው ፍላጎታችን አንዱን ወገን አባረን በሌላ የአርቲስት ወገን የመከበብ ሳይሆን ሁሉም እኩል የሚታይበት ሥርዓት ማስፈን ነው የሚል ይዘት ያለው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የአዳራሹን ታዳሚ እየዞሩ አቅፈው ስመው ሰላምታ አቅርበዋል፡፡ ምሳ ሲጋብዙ እየዞሩ እንዴት ነበር ቆይታችሁ ሲሉ ሁሉንም በየጠረጴዛው አናግረዋል፡፡ 

በታሪክ አጋጣሚ ታናሽ ብንሆንም ከታላላቆቹ ጋር በታላቁ ቤተ መንግሥት ቅጥር ግቢ ታድመናል፡፡ እውነት ለመናገር የሀገራችን ከያኒ ዘጠና ከመቶው ነበር፡፡
እንግዲህ ደራሲ ነኝ ብሎ እሚያምነው ብቻ ከአስር ሺ በሚበልጥበት ሀገር እኔ ቀረሁ ብሎ ማላገጥ ትዝብት ውስጥ ይጥል እንደሁ እንጂ አያንጽም፡፡

በእርግጥ ጥቂት ሰዎች ተዘንግተው ይሆናል፡፡ ያ ደግሞ ትልቁን ስኬት አያደበዝዘውም፡፡ ከራስ ወዳድነት መውጣት አለብን፡፡ እኔ እንደሁ እንጂ ከተጋበዘው ሰው አይገባውም የሚባል በአደራሹ አላየሁም፡፡

አስቴር በዳኔ ከቤተ መንግስቱ አዳራሽ ተባረረች የሚለውን ዘመቻ ስመለከት አዝኛለሁ፡፡ ወሬውን አቀብለኝ እንጂ እኔ ከአንተ በላይ እንዳየሁ አሳይሃለሁ የሚሉ ሰዎች መብዛታቸውን ያየሁበት ነው፡፡

አስቴር በዳኔ እንደመጣች መንገድ ዘግቶ በተቀመጠ ወንበር ላይ ቁጭ አለች፡፡ ሥርዓት ያለው ሴኪዩሪቲ መንገድ መሆኑን በእጁ ጭምር እያሳየ ውስጥ ገብታ እንድትቀመጥ ጠየቃት፡፡ ተነስታ ወደ መሀል ቦታ በዓይኗ ፈልጋ ቦታ ያለው ወደ ኋላ መሆኑን ስታይ አዳራሹን ለቃ ወጣች፡፡

ቤተ መንግስትን ያህል ቦታ የማይፈለግ ሰው መጥሪያ ደርሶት፣ ተጠርቶ፣ ተፈትሾ ገብቶ ከአደራሽ ይባረራል ብሎ ማሰብ ስፍራውንና የጸጥታ ቁጥጥሩን ካለማጤን የመጣ ነው፡፡

ዶክተር አብይ ታላቅ ሰው መሆኑን አሳይቶናል፡፡ ልብ ሰብሯል፡፡ ዝም ብሎ ደገሰው ድግስና የጠራው ጥሪ አይደለም፡፡ ይሄ ሁሉ የዘር ግጭት እና ሰው በላነት ጥበብ በኢትዮጵያ ሚናዋን ስላልተጫወተች ነው ብሎ የቁጭት እሳት ነው የጫረው፡፡ ይሄን ሰው ለዛሬ አንተ ልበለው፤ ሁሉም ሰው የረካበት ውሎ ነበር፡፡

ቤተ መንግስቱን ሙልጭ አድርገን እንድናስሰው ተፈቅዶልን ጎብኝተናል፡፡ ከኪነ ጥበብ ቤተሰቡ ጋር አብሮ መስራት ከባድ መሆኑን ሲገልጽ እዚህ ብቅ ብሎ የወጣ ሁሉ የቅርብ ሰው ነኝ እያለ ከተማው ላይ የሚያናፍሰውን ጉዳይ እንደማይወደው ገልጾልናል፡፡

“ሁላችሁም ለእኔ እኩል ናችሁ ሲል ቴዎድሮስ ተሾመ አብሮ አደጌ ነው፡፡ በእርግጥ እሱ እንዲህ ያለ ነገር አይልም፤ እሱም እንኳን ከእናንተ እንደ አንዱ ነው” ሲል ነበር ጓደኛዬ ነው እያሉ ከተማውን ያዳረሱ የኮነነው፡፡

በእርግጥ ቴዎድሮስ ተሾመ የቅርበቱን ያህል ሌላ ቅብጠት ያልታየበት ጨዋ ሰው ነው፡፡ ዶክተር አብይ እያንዳንዱን ታዳሚ በየወንበራችን እየዞረ አቅፎ ሰላም ሲል አንዳንዶች አልቅሰዋል፡፡

በምሳ ግብዣው ላይም ቢሆን በየጠረጴዛው እየዞረ እንዴት ነበር ጉብኝቱ ውሎው በሚል ሁሉንም አነጋግሯል፡፡ እንዲህ ያለ የመሪ ልብ ማግኘት እድል ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያየ አግባብ ከያኒውን ወክለው ሁሉን ተቆጣጥረው ነበር የሚባሉ ግለሶች በመደመር ዘመን ለምን አብረው ታዩ ተብሎ የሚነሳው ጥያቄ ልክ እንዳልሆነ ያስረዱት ጠቅላያችን እኛ ያንን አባረን በሌላ ባለ ግዜ አርቲስት ለመከበብ አይደለም ፍላጎታችን ሁሉም እኩል የሚታይባት ሀገር ለመፍጠር ነው እየደከምን ያለነው ብለዋል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ግንባር ሆኖ ተብሎ ሲጻፍ ባነብም በተጨባጭ ያየሁት ግን ኋላ ተቀምጠው እንደ አንድ ተራ ሰው ጉባኤውን ሲታደሙ ነው፡፡
እንደ ታማኝ በየን እና በእውቀቱ ስዩም ያሉ ሰዎች በስፍራው አልተገኙም፡፡ ዶክተር አብይ የአርት ጥበብን ሲያሳይ ካቀረባቸው መጻሕፍት አንዱ የበእውቀቱ ስዩም ነበር፡፡ ቴዲ አፍሮም በባለቤቱ ተወክሏል፡፡ የምንወዳቸው ሰዎች ጥቂቶቹ ቀርተው ይሆናል፡፡

አዘጋጆቹ በቀጣይ እንዲህ ያለ ክፍተት እንዳይፈጠር እንደሚሰሩ እምነቴ ነው፡፡ ከዚያ በተረፈ የታዳሚውን ፎቶ በማየት ይሄ የማይገባው ሰው ነበር የምትሉት ማንን ይሆን ብዬ ጥያቄ ማንሳት እሻለሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሀሜት መገለጫችን እንደሆነ ጠቆም አድርገው አልፈዋል፡፡ DireTube

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close