Connect with us

Ethiopia

መንታ ሰብዕና፡ ከመሐመድ እሰከ ሳሞራ

Published

on

መንታ ሰብዕና ፡ከመሐመድ እሰከ ሳሞራ

መንታ ሰብዕና፡ ከመሐመድ እሰከ ሳሞራ | ሬሞንድ ሃይሉ በድሬቲዩብ

ግንቦት ያነገሰው ሰው በግንቦት ተሸንቷል ፡፡ ከባድመ እሰከ ባይድዋ ከቡሬ እስከ አቤ ያዘመተውን ጦር ይከታተልበት ለነበረው ቢሮውም ጀርባውን ሰጥቷል ፡፡ የመሀመድ መንገድ በብዙ አስገራሚ ታሪኮች የተሞላ ነው ፡፡

በትምሀርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ለመምህሮቹ ተስፋ የነበረው ብላቴና ደጋግሞ መቀርተን አዘውትሯል፡፡ ከጊዜያት በኋላ እንድውም ከእናካቴው ትምህርት ቤት መሔዱን አቆመ፡፡ መምህራኖቹ የሚተማመኑበት ተማሪያቸውን የት ወደቀ ብለው ሲያጣሩ ያ ብላቴና ትግሉን መቀላቀሉን ሰሙ፡፡ መሐመድን ታጋይ አድርጎ ማሰብ ከባድ ነው፡፡ የሰውነት ክብደቱ ብቻ ሳይሆን ፍረሃቱም እሱን ወታደር አድርጎ ለማሰብ ያዳግታል፡፡

ነገር ግን የሸፈተው በወቅቱ በነበረው ስርዓት ላይ ብቻ ሳይሆን በራሱም ላይ ሆኖ በትግሉ ሜዳ በጀግንነት የሚወደስ ሰው ለመሆን በቃ፡፡ መሐመድ የሚለውን ስሙን እንደ ሰንኮፍ አውልቆ ሳሞራ በሚል የተካው የአክሱሙ ብላቴና በጊዜ ሂደት ወደ ተላቅ የጦር መሪነት ተሸጋገረ፡፡ በትግሉ ሂደት ወሳኝ ከሚባሉት ግንባሮች አንዱ የሆነውን የሽሬ ጦርነት በየበላይነት በመምራትም ለድል እንዲበቃ አደረገ፡፡

በልጅነት ዘመኑ በፍረሐት የሚታወቀው መሀመድ በአፍላነቱ ዘመን ወደ ታላቅ የጦር መሪነት ተንደረደረ፡፡ በ1993 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይም የኢትዮጵያ ኢታማዦር ሹም ሁኖ ብቅ አለ፡፡ በሀገሪቱ ዘመናዊ የውትድራና ታሪክ ውስጥ ሁለተኛው ባለአራት ኮከብ ሙሉ ጀነራል ለመሆን የበቁት ጀነራል ሳሞራ ለውትድርና የተፈጠሩ ሰው ሰለመሆናቸው ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡

ሁለት የማስተርስ ድግሪዎችን የተከታተሉት ኢታማዦር ሹሙ፤ ከሁለት የተለያዩ ሀገራትም ከፍተኛ ወታደራዊ የክብር ኒሻን ተበርክቶላቸዋል፡፡ የወታደራዊ ሳይንስ ምሁራን በአፍሪካ በፍጥነት የተገነባ ዘመናዊ ጦር እያሉ ከሚጠሩት የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት ጅራባ ያሉት ዋና ሰው አሁን የአስራ ሰባት ዓመታት የአመራርነታቸው ዘመን አክትሟል፡፡ በጦር ሜዳ ያልተረቱት ሰው ጊዜ ለሚሉት ኃይል እጅ ሰጥተዋል፡፡

በብዙ የአፍሪካ ሀገራት እንደሆነው ሀገር ሲረበሽ ለስልጣን ማሰፍሰፍ ያልተስተዋለባቸው ጀኔራል ሳሞራ የኑስ በርካታ የመከላክያ ስራዊት ማሰልጠኛ ማንዋሎችን አዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ የታነሳው ሰራዊትም ከሲቪል ስርቪሱ በተሻለ ስነ-ምግባርን ተላብሶ ህዘብን ለማገልገል ሞክሯል፡፡

በብዙ ያልተነገሩ ታሪኮች ውስጥም እራሱን ሰውቷል፡፡ ዝቅተኛ የደሞዝ ተከፋይ ቢሆንም እንደ በርካታ ሀገራት ጦር ለገንዘብና ለስለልጣን የሚሰገበገብ አልሆነም፡፡ ሕይወት ለመስጠት ለመጣ ወታደር ደሞዝ ቁምነገሩ አይደለም በሚል መንፈስም ከማናኛውም የመንግስት ሰራተኛ በታች እየተከፈለው ከዛሬ ደጃፍ ደርሷል፡፡

ይህ ሰራዊት መንግስት ለመውደቅ ሲጣጣር እንደ ሌላው ሀገር ወታደር ጎዳና ወጥቶ ህዝቡን አልዘረፍም፡፡ ስልጣን ካልሰጣችሁኝ ብሎ ወደ ቤተ-መንግስት አላመራም፡፡ እኛ በብሄር ስንተላለቅ ሰራዊቱ ግን ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ዕርስ በዕርስ አልተጫረሰም፡፡ የአማራ የኦሮሞ አልያም የትግራይ ሰራዊት ብቻ ባለመሆኑ አማራ ከትግሬው ጋር አልተኳረፈም፡፡

የኦሮሞው ተወላጁ ወታደር እነደ ፖለቲከኛው ሱማሌው ጋር አልተጣላም፡፡ አለቆቼ ገንዘብ በልተዋል በሎ እነሱ ላይ ወቅት ጠብቆ አልተነሳም፡፡ ይህ ዕውነት በአስማት የተፈጠረ አይደለም፡፡ ይህ ዕውነት በጠንካራ አመራር የተገነባ ነው፡፡ ለመለያየታችን መንግስትን ከወቅስን በሰራዊት ውስጥ ላለው የአንድነት መንፈስም አመራራሩን ማድነቅ ተገቢ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነትን በጎጥ ስንከፋፍለው ሰራዊት ውስጥ ጎጠኝነት የሌለው እነሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለማይኖሩ አይደለም፡፡ ይልቁኑ በጠንካራ ስነ-ምግባር ስለታነፁ ከራሳቸው በላይ ሀገርን ስላሰቀደሙ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የተቋሙ አደራጃጀት የበኩሉን አስተዋፆ አብርክቷል፡፡ እንዲህ ያለውን ሀቅ የምንቀበለው ከሆነ ደግሞ ከዚህ ጀርባ ያሉትን ዋና አለቃ አለማድነቅ አይቻልም፡፡ ሰለዚህም ከሲቪል ሰርቪሱ የተሻለ ሀገሩን ያስቀደመ ሰራዊትን ሰለገነቡ፤ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካውያን የዕኛ ቢጤዎች ታዛ ስለሆኑ ጄነራል ሳሞራ የኑስን እጅ ነስቻለሁ፡፡ DireTube

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close