Connect with us

Art and Culture

የጎብኚዎችን ቁጥር እያበራከተ ያለው መስህብ

Published

on

የጎብኚዎችን ቁጥር እያበራከተ ያለው መስህብ

የህብረተሰቡን አቅም ባማከለ ወጪ አገልግሎት እየሠጠ ያለዉ የጣና ሐይቅ የጀልባ ትራንስፖርት ለጎብኚዎች መበራከት እና እርካታ ምክንያት ሆኗል፡፡

ወጣት ፍሬዉ አስረስ በጣና ሃይቅ ለጎብኝዎች አገልግሎት ከሚሰጡ ጀልባዎች መካከል የአንዷ ቀዛፊ ነዉ፡፡

ተቀጥሮ በሚሰራበት ጀልባ ወደ ስፍራዉ የሚመጡ ጎብኝዎችን በሀይቁ ላይ ከማንሸራሸር በተጨማሪ በጣና ደሴቶች ላይ የሚገኙ ጥንታዊ ገዳማትን ያስጎበኛል፡፡

በወጣለት ተራ መሰረት ደንበኞችን ለማስተናገድ ጀልባውን በሀይቁ ዳርቻ ወደተሰራው ወደብ በማስጠጋት እንግዶችን መጠባበቅ የዘወትር ስራው ሆኗል ፡፡

ተማሪ ሜሮን እና ሁለት ጓደኞቿ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ በጣና ሃይቅ ላይ በተደጋጋሚ በጀልባ የመመላለስ ልምድ ስላላቸው ወደ ፍሬዉ ጀልባ ገብተዋል ፡፡

የዛሬው የጉብኝት እቅዳቸዉ ደግሞ በቅርብ ርቀት ወደ ምትገኘዉ ደሴት በመጓዝ ደብረ ማርያም ገዳምን መጎብኘት ነዉ፡፡

በቅርቡ የአስረኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱት እነዚህ ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸዉን በዚህ መንገድ መጀመራቸዉ አስደስቷቸዋል፡፡

ታዲያ ወጣት ፍሬዉ እና የስራ ባልደረቦቹ የደንበኞቻቸዉን የጉብኝት እርካታ ለመጨመር ስለጥንታዊ ቅርሶቹ መረጃዎችን ለደንበኞቻቸዉ በማድረስ ጉዞውን ያማረ ያደርጋሉ፡፡

በደሴቶቹ ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት፣ገዳማት፣ጥንታዊ፣ባህላዊ፣ ሐይማኖታዊ የመገልገያ ዕቃዎች እና የቀደምት ነገስታት ቅሬተ-አፅሞች እንዲጎበኙም ያደርጋሉ፡፡

‹ የጠዋት ብርሀን › የቱሪስት ጀልባ ኪራይ ማህበር ፀሀፊ የሆነዉ ወጣት ገበየሁ ታምሩ ‹‹ ወደ ከተማዋ የሚመጡ ሀገር ጎብኚዎችን ቢሯችንን ክፍት በማድረግ እያስተናገድን ነው ›› ይላል፡፡

የቤዛዊት ቤተ-መንግስት፣ የባህር ዳር ገበያ፣ የጭስ-አባይ ፏፏቴ፣ የነገደ ወይጦ መንደሮችን እና ከተማዋን እንዲጎበኙ ከማድረግ በተጨማሪ የጣና ሃይቅን፤ በውስጡ ያሉትን ደሴቶችን፣ ገዳማትን እና በሃይቁ ዙሪያ የሚገኙ ታሪካዊ አካባቢዎችን ለጎብኚዎች በማሳየት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን አጫወተን፡፡

ዘመኑ ያፈራቸው ከፋይበር ግላስ እና ከብረት የተሰሩ ሃያ ጀልባዎች ማህበሩ እንዳለው የተናገረው ወጣት ገበየሁ ጥንካሬያቸው እና ጉልበታቸው አስተማማኝ በመሆኑ ያለስጋት ለደንበኞች አገልግሎት እንድንሰጥ አስችሎናል ብሎናል ፡፡

ጀልባ ቀዛፊዎቹ አካባቢዉን በቅርበት የሚያዉቁ እና ከገዳማቱ ጋር የቅርብ ቁርኝት ያላቸዉ መሆን ለጎብኚዎች የሚሰጡት መረጃ የተሟላ እንዲሆን ማድረጉን ፀሃፊው ጨምሮ አስረድቶናል፡፡

በትራንስፖርት ዋጋ ረገድም በሚመለከተው አካል የተተመነ ታሪፍ የወጣ ሲሆን የመክፈል አቅም የሌላቸውን ከሌሎች ጋር በማቀናጀት ተመጣጣኝ ክፍያ እንዲከፍሉ በማድረጋችን የጎብኚዉ ቁጥር በየጊዜው እንዲጨምር ምክኒያት ሆኗል፡፡

በዚህም የተነሳ ለሌላ ጉዳይ ወደከተማዋ የመጡ የሀገራችን ሰዎች ሳይቀሩ አጋጣሚዉን በመጠቀም በጀልባችን ጉዞ የማድረግ ዕድል ማግኘታቸውን የማህበሩ ጸሃፊ ጨምሮ ነግሮናል ፡፡

ምንጭ፡ – አብመድ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close