Connect with us

Ethiopia

የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ የመቐሌ ውይይት ሙሉ ፕሮግራም

Helen

Published

on

የመቐሌ ውይይት

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመቐለ ከተማና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይት መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያን ያለ ትግራይ ትግራይንም ያለ ኢትዮጵያ ማሰብ አይቻልም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ የትግራይ ተወላጆች ለዜጎች ነጻነትና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር መስዋዕት ሁነዋል ያሉ ሲሆን የክልሉ ተወላጆች በየትኛውም ጊዜ በኢትዮጵያዊነታቸው ተደራድረው እንደማያውቁም ነው ያስታወቁት፡፡

ትግራይ የስልጣኔ ፣ የዜማ እና ቅኔ መነሻ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ትግራውያን ለኢትዮጵያ አነድነት መጠንከር ሲታገሉ እንደነበረ አውስተዋል፡፡ በሃገሪቱ የተደረገው የነጻነትና የዴሞክራሲ ትግል ከዳር እንዲደርስ የትግራይ ልጆች ከፍተኛ ሚና መጫታቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ የትግራይ ህዝብ ያለውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት ተባብረን እንሰራለንም ብለዋል በንግግራቸው።

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው፥ ዶክተር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተመረጡበት መንገድ የዴሞክራሲው ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ሂደቱ ስልጣን በሁከትና ግርግር ሳይሆን በዴሞክራሲያዊና ህገ መንግስታዊ መንገድ እንደሚገኝ ማረጋገጫ መሆኑንም ተናግረዋል።

የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የሃገሪቱ ህዝቦች ጋር በመሆን የተሻለች ሃገር እየገነባ ነው ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፥ በጥቂት ሃይሎች አማካኝነት በህወሃትና በትግራይ ህዝብ ላይ የተቀናጀ ጥቃት መከፈቱን ጠቅሰዋል። ለዚህም ባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሲፈጸም እንደነበር አስታውሰዋል። ዶክተር ደብረጽዮን በንግግራቸው ከዚህ በኋላ የዜጎች መፈናቀል ሊቆም እንደሚገባ ጠቁመው፥ የዜጎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመስራት መብት ሊከበር ይገባልም ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የከተማዋና ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተገኙ ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ተወያዮቹ በቅድሚያ በክልሉ የተለያዩ አካባቢወች ያልተሟሉ እንደ መንገድና ውሃ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንዲሟሉ፣ የዜጎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመስራት ህገ መንግስታዊ መብት እንዲከበርና አስተማማኝ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ጠይቀዋል። ከዚህ ባለፈም በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎች ብሄር ተኮር በሆኑ ችግሮች ሳቢያ ለጥቃት የተዳረጉና በእስር ላይ የሚገኙ የትግራይ ክልል ተወላጆችን ጉዳይ መንግስት እንዴት ያየዋል ሲሉም ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው በነዋሪዎቹ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል በክልል ደረጃ የሚመለሰው በክልሉ መንግስት ከዛ ከፍ ያሉትን ደግሞ በፌደራል ደረጃ በማየት እንደሚፈቱ አስረድተዋል። ከዚህ ባለፈም የቀድሞ ታጋዮች ያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ እልባት ያገኛሉም ነው ያሉት። በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ተከስቶ የነበረው ብሄር ተኮር ግጭትም የአካባቢውን ነዋሪዎች ሳይሆን የጥቂት ሃይሎችን ፍላጎትና ድርጊት እንደሚወክልም ነው በምላሻቸው ያነሱት።

በኦሮሚያ ክልል የታሰሩ የትግራይ ክልል ተወላጆችን ጉዳይ በተመለከተም ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ጋር ተወያይተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በዚህም በክልሉ ባለፈው አንድ አመት 29 የትግራይ ተወላጆች በተለያየ ምክንያት ታስረው እንደነበር ጠቁመው፥ ከዚህ ውስጥ 18ቱ ተፈተው 11 ሰዎች ብቻ በእስር ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥ ስድስቱ የተፈረደባቸው ሲሆን አምስቱ ደግሞ በቅርቡ ተፈጥሮ በነበረ ግጭት የተለያዩ ቁሳቁሶች ይዘዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውንም ነው በምላሻቸው ያነሱት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በትግል የተሰው ሰማዕታት ኃውልት ላይ በመገኘትም የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። የጠቅላይ ሚንስትሩን ሙሉ ንግግር እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close