Ethiopia
የሟች ቤተሰቦች ገዳይን የሚበቀሉበት ‘የደም መላሽ’ የተባለ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት

አለመግባባት ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል፡፡ ግጭት ሲፈጠር ከስሜታዊነት ተወጥቶ በንግግር መፍታት ካልተቻለ ደግሞ አለመግባባቱ ወደ ሀይል እርምጃ እንዲቀየር እድል ይሰጠዋል፡፡ የሀይል እርምጃ እስከ ግድያ የሚያደርስበት አጋጣሚም በርካታ ነው፡፡ ጊዜና አጋጣሚን ጠብቆ የሞተ ቤተሰብን ደም መመለስ ወይንም መበቀል በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በአማራ ክልል በስፋት ሲፈጸም የኖረ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ነው፡፡
የበቀል ግድያ ገዳይን አሊያም የገዳይን የቤተሰብ አሊያም ደግሞ ገዳይን ከነ ቤተሰብ በአንድ ላየይ መግደል ሊሆን ይችላል፡፡ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ሸበል በረንታ ወራዳ በገብሲት ቀበሌ የበቀል ግድያ ለዘመናት ሲተገበር ነሯል፡፡ ይህን ድርጊት ለማስቆም የመንግስት የጸጥታ አካላት ፤ የሀገር ሽማግሌዎች እንደሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ደም አድርራቂ የተሰኝ ኮሚቴ አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ኮሚቴው ከተቋቋመ ወዲህ የደም መመለስ ተግባር ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል ሊባል ወደ ሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
በቀበሌው ደም መላሽ የሚልና ሌሎች ደም መመለስና መበቀልን የሚያበረታቱ ስሞች እየተቀየሩ ይገኛሉ፡፡ ለልጁ ደም መላሽ ብሎ ስም ያወጣ ቤተሰብም እየተቀጣ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡ የወረዳው የአስተዳደር ጽ/ቤት በቀለቤው ይህንን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ለማስቀረት የተሰራውን ስራ ወደ ሌሎቹ የወረዳው ቀበሌዎች ለማስስፋፋት ጥምረት እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ደም መላሽ ፤ አሸብር ፤ እርገጤ ፤ ውቃቸውና ሌሎች በቀልን የሚያበረታቱ ስሞችን ያስቀረችው የገብሲት ቀበሌን ተሞክሮ በክልሉ ለማስፋት የሚመለከተው አከል በትኩረት ሊሰራ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በዚህ ጉዳይ ላይ አጠር ያለ ዘገባ አሰናድቷል፡፡
-
Ethiopia2 days ago
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አዳዲስ ተሿሚዎች ታውቀዋል
-
Entertainment4 days ago
አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ተሞሸረች
-
Ethiopia22 hours ago
ለሜቴክ እና ለኢንሳ አዲስ ዋና ዳይሬክተሮች ተሾሙ
-
Ethiopia4 days ago
ከህገ-መንግስቱ የተኳረፉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ!
-
Art and Culture2 days ago
በወርቅ የተሞላው ነገር ግን በሴጣን የተከበበው ተራራ
-
Ethiopia1 day ago
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሶስት ቁልፍ ቦታዎችን ለኦህዴድ መስጠታቸው ጠቃሚ እርምጃ ነው ተባለ
-
Ethiopia24 hours ago
‘የምሞት እየመሰለኝ በጣም ተጨንቄያለው’ ከመሞቱ ሶስት ቀናት በፊት የተናገረው
-
Entertainment22 hours ago
የአርቲስት ታምራት ደስታ የቀብር ሥነሥርዓት ተከናወነ