Connect with us

Ethiopia

ዶ/ር አብይ ከልጅ እንዳልካቸው መኮንን ምን ይማሩ?

Elias Tesfaye

Published

on

ዶ/ር አብይ ከልጅ እንዳልካቸው

ልጅ እንዳልካቸው መኮንን የንጉሱ ዘመን የመጨረሻው ጠቅላይ ሚንስተር ነበሩ ፡፡ ልክ እንደ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትርነታቸውን በቃኝ ብለው የለቀቁትን አክሊሉ ሀብተወልድ ተክተው ምኒልክ ቤተ መንግስት የገቡት ሰው ስርዓቱን ሊያድኑ ጥረዋል ፡፡

የተነቃነቀውን ዙፋን መልሰው ለመትከል አዳዲስ አሰራሮችን ተግብረዋል ፡፡ህገ-መንግስቱ እንደሻሻል ተንቀሳቅሰዋል ፡፡ የጠቅላይ ሚንስትሩን ተጠሪነት ለፓርላማው እንዲሆን አድረገዋል ፡፡ ኦክሰፎርድ የተማሩት ልጅ እንድልካቸው ከጊዜ ጋር ተናንቀው የንጉሱን ስርዓት ያድናል ያሉትን መድኃኒት ሁሉ ለጃንሆይ አቅረበዋል ፡፡

ከመጋቢት እሰከ ነሀሴ በዘለቀው ስልጣናቸው ይህን ሁሉ ቢያድርጉም ዕድል ግን ከእሳቸው ጋር አልነበችም ፡፡ከዕሳቸው በፊት የተነሳው የህዝብ ጎርፍ እየጋለበ ከፊታቸው ደረሰ፡፡ አንድም ሰው ሳያስቀርም ጠራርጎ በላቸው ፡፡ አብይ (ዶ/ር) ከልጅ እንዳልካቸው የሚማሩት ብዙ ነው ፡፡ ከምንም ነገር በላይ የተበጣጠሰ ፓርቲያቸውን አንድ የማድረግ ሀላፊነት አለባቸቸው ፡፡

ለየቅል ጉዞ የጀመሩትን የኢህአዴግ ዕህት ድርጅቶች ለማዋሃድ ካልቻሉ አብይ አህመድ (ዶ/ር )የልጅ እንዳልካቸውን ታሪክ የመጋራት ናፍቆት እንዳላቸው ይቁጠሩት ፡፡ በርካታ የፖለቲካ ምሁራን እንደፃፉት ኢህአዴግ የሚፈርሰውም የሚታደሰውም በውስጡ ባለው ግንኙነት ብቻ ነው ፡፡ይህ ካልሆነ ግን ኢህአዴግ እራሱም ፈርሶ ሀገር ማፍረሱ የማይቀር ይመስላል ፡፡

ኢህአዴግ እጅግ በጣም ኮሞሲታዊ ባህሪ ያለው ፓርቲ በመሆኑ ከዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትና የቡድን አስተሳሰብ በዚህ ምዕተ ዓመተ ይላቀቃል ብየ አልገምትም ፡፡ የሀላፊ መለዋወጡም አዲስ ታአምርን ይፈጥራል ብሎ ማሰብ የዋሀነት ነው ፡፡ ከዚህ አንፃር ዋናው ጥያቄ ሀገርን እንደ ሀገር ማስቀጠሉ እንጅ አብይን (ዶ/ር)ተስፋ ማድረጉ አይመስለኝም ፡፡

አሁንም አቶ ልደቱ አያሌው እንደሚሉት ኢህአዴግ ይወድቃል አይወድቅም የሚለው ሳይሆን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጠሏ ምላሽ አላገኝም ፡፡ በአሰቸኳይ ጊዜ ውስጥ ሁንን በመጣ ሰላም ተዘናግተን የደስታ ዳኒክራን እየመታን ከሆነ ተሳስተናል ፡፡

ከእነዚህ ሁኔታዎች በመነሳት የዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መምጣት ለሀገሪቱ ምን ይፈይዳል? ማለቱ ተገቢ ነው ፡፡ የዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መምጣት ቢያንስ ከአምስት ክልሎች ጋር የተጎራበተውን የኦሮሚያን ክልል ያረጋጋል ፡፡ ይህ ደግሞ አንፃራዊ የሆነ ሀገራዊ ሰላምን ሊያሰፍን ይችላል ፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ግን ስልጣን በአመፅና ተቃውሞ የሚገኝ መሆኑን ለህዝቡ ማስተማሩ የነገዋን ኢትዮጵያ አስፈሪ ያደርጋትል ፡፡ የድህረ-ዕውናዊ (Post-truth politics)ፖለቲካ ሰደድ የሀገሬውን ሰው ዕንዳይበላው ያስጋል ፡፡እንዲህ ያለው መንገዳችን ደግሞ በፓርቲው ውስጥ ባለ አለመተማምን ከታገዘ የሚያሰፈራውን ጊዜ ቀድመን እንድንተዋወቅ ያሰገድደናል ፡፡

በኢህአዴግ ቤት አብይ(ዶ/ር) የአማራጭ ዕጦት የወለደው ተመራጭ እንጅ ሁሉንም ማዕከል ያደረገ ሰው አለመሆኑ ከተገኘው ድምፅ ማወቅ ይቻላል ፡፡ እንዲህ ከሆነ አብይ የሚገጥመው የመጀመረያው ፈተና በራሱ ፓርቲ ውስጥ እኩል አመኔታን የማትረፍ ጉዳይ ነው ፡፡ ይህ በተግባርም የሚታገዝ ከሆነ የነገዋ ኢትዮጵያ ታስፈራኛለች ፡፡

ሬሞንድ ሀይሉ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close