Connect with us

Business

የኃያላኑ ፍጥጫ በአዲስ አበባ

Published

on

የኃያላኑ ፍጥጫ በአዲስ አበባ - እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንኩ!

የኃያላኑ ፍጥጫ በአዲስ አበባ – እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንኩ! | ሬሞንድ ሃይሉ በድሬቲዩብ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2010 (በድሬቲዩብ) ሜዳው ሸራተን ነው፡፡ ተፋላሚዎቹ ደግሞ ሬክስ ቲለርሰንና ሰረጌ ላችሮቭ፡፡ ትናንት ምሸት ኃያላኑ ሀገራት በአዲስ አበባ ያደረጉት የፖለቲካ ጨዋታ በማን አሸናፊን እንደተጠናቀቅ እስካሁን አልታወቀም፡፡ ”ኒውስዊክ” መፅሔት ከስዓትት በፊት ባወጣው ዕትሙ የፖለቲካ ባላንጣዎቹ ቲለርሰንና ላቭረሮቭ መገናኛኘትም መተያየትም እንድማይፈለጉ ከነገሩን በኋላ ‘ለምን አንድ ሆቴል ውስጥ ሊያርፉ መረጡ?’ የሚል ጥያቄ አዘል ሀሳቡን ይሰነዝራል፡፡

ሩሲያ በገለልተኛ ሜዳ የአፍሪካዋ መዲና ላይ ከአሜሪካ ጋር ለመገናኛት ፈለገች ቢባልም ወደኋላ ላይ መረጃው ውሸት ነው ስትል ተደምጣለች፡፡ ቲለርሰንም ጉዞየ አፈሪካ ጋር ያለንን ወዳጅነት ለማጠናከር እንጅ ከሩሲያ ጋር ያለውን አይደለም የሚል ሃሳብ እንደሰነዘሩ ውስጥ ውሰጡን ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይህ ሁሉ መግደርደር ግን ትናንት ማምሻውን ተሸንፏል፡፡

አንድ ሆቴል ያረፉት የፖለቲካ ባላንጣዎቹ ቲለርሰንና ላቭረሮቭ በሸራተን የዕንግዶች ማረፊያ ተገናኝተዋል፡፡ ታስቦበት ይሁን ባጋጣሚ ባልታወቀው የቲለርሰንና የላቭሮቭ የአፍታ ውይይት ምን እንደተነሳ እስስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ የአለም መገናኛ ብዙሃንም የሁለቱን የፖለቲካ ባላንጣዎች አጭር ቆይታ የተመለከተ መረጃን እስካሁን አላደረሱም፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ አሰቸጋሪ ስዓትም ውስጥ ሁና ካለአንዳች ኮሽታ የኃያላኑ ሀገራትን የፖለቲካ ጨዋታ አስተናግዳለች፡፡ ይህ በእርግጥም የሚያስደስት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን እንዳለመታደል ሁኖ መሪ ባይወጣልንም እራሳችንን ለማስተዳደር ግን የምናንስ ህዝቦች አይደለንም፡፡ ደርግ ከስልጣነ መንበሩ ሲለቅ በረካቶች ሀገር ፈረሰ ብለው ቢያሟርቱብንም ህዝቡ ግን ድንበር ብቻ ሳይሆን የሀገርን ሀብትም በመጠበቅ ታሪክ ሰርቷል፡፡

ኢህአዴግ ተደራጅቶ ሙሉ የመንግስት ስልጣኑን በአግባቡ ከመቆጣጠሩ በፊት በነበሩት ጥቂት አመታትም ኢትዮጵያውያን ዕራሳቸውን በመምራት ለሀገራቸው አንድነት ያላቸውን ቀናኢነት አሳይተዋል፡፡ ዛሬም የሀገሬ ህዝብ ለመሪ ባይታደልም እራሱን ለመምራት ግን አልሰነፈም፡፡ ለዚህ ማረጋገጫው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ህዝቡ ወደ አላስፈላጊ የስልጣን ሽሚያ ውስጥ አልገባም፡፡

እውነት ኢትዮጵያውያን በርግጥም የተለየን ህዝቦች ነን፡፡ የትኛው የአፍሪካ ህዝብ ነው መሪው ስልጣን ለቅቄያለሁ ብሎት አደባባይ ወጥቶ ለስልጣን ያልተጋደለው?

የትኛውስ የአፍሪካ ወታደር ነው የሀገሪቱ መሪ እለቃለሁ ሲል እየሰማ ሀገር ለማረጋጋት የሚባትለው? የትኛውስ የአፍሪካ ዋና ከተማ ነዋሪ ነው ስልጣን እለቃለሁ ያለ መሪው ላይ ቂም ሳይዝ በዝምታ የሚሸኘው?

የትኛው ሀገር ያለስ ጄነራል፣ ኮለኔል፣ ሻለቃ፣ ሻንበልና ተራ ወታደር ነው እንዲህ ያለ የፖለቲካ ቀውስ መኖሩን እያየ ለስልጣን የማይጓጓው?

የትኛው የአፍሪካ ሀገርስ ነው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ ተዋጆ፣ መሪው ስልጣን ሊለቅ አኮብኩቦ ባለበት ስዓት የኃያላኑ ሀገራት ባለስልጣናት ያልስጋት የሚሔዱበት? መልሱ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ ብቻ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በየትኛውም አዳጋች ወቅት ሁሉ የሚታደጓት መሪዎቿ ሳይሆኑ ህዝቦቿ ናቸው፡፡ ይህን ደግሞ ከእኛ በላይ ውጮቹ በደንብ ያውቁታል፡፡

ከእስራኤል የግብርና ሚንስትር እሰከ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ከቲለርስን እሰከ ላችሮቭ ድረስ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በተመሳሳይ ሳምንት አዲስ አበባ መምጣት ትርጉሙ ብዙ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ነው፡፡

ስለዚህ ከመሪዎቹ ለሚሻላው ህዝባችን ክብር እንስጠው፡፡ ፊደል ከቆጠረው በላይ ስለሀገሩ የሚያሰበውን ያን ምስኪን አርሶአደር እናድንቀው፡፡ ለእኔ ኢትዮጵያዊነት የሚወለደውም የሚሞተውም ፌስቡክ ላይ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን ሀገር ያደረጋት ህዝቡ ነው፡፡ መሪ ወረደም ነገሰም እዚህ ህዝብ ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ አሁንም አለች ወደፊትም ትኖራለች፡፡ ይህ ደግሞ እንኳንም ከእንትና ብሄር ተወለድኩ ሳይሆን እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንኩ ያስብላል፡፡ DireTube

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close