Connect with us

Art and Culture

ሴትስ እኛ ሀገር ቀረች

Published

on

ሴትስ እኛ ሀገር ቀረች፤

ሴትስ እኛ ሀገር ቀረች | ዛሬ ዓለም ስለሴቶች እኩልነት ያወራል፡፡ ዓለም አቃተኝ እያለ የሚሰብከውን ሴቶችን የስልጣን ባለቤት የማድረግ የፍትሕ ጥያቄ የሀገሬ ሴቶች ከግማሽ ሚሌኒየም በፊት አድርገውት ነበር ይላል ተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም 㝕㝕㝕የዛሬ ዓመት ማርች 8 በጸጻፈወው ጽሑፍ፡፡ ቀኑን ምክንያት አድርገን በድጋሚ አቅርበንዋል፡፡ | ሔኖክ ስዮም በድሬትዩብ

በእርግጥ እኔ ሞኝ አይደለሁም፡፡ የሀገሬን ሴቶች በዚህ አልጠረጥራቸውም፡፡ ስለ ሌላው ዓለም ሴት አላውቅም፡፡ በእኔ ሀገር ግን የሴት አቅም ታሪክ ብቻ አይደለም፡፡ ዛሬም በየአደባባዩ አፍ የምታሲዝ ብርቱ ሄዋን አለች፡፡ አደባባይ መውጣት ቢያቅታት ከማጀቷ ሆና በባሏ ነፍስ የምታዘው ብዙ ናት፡፡ ምክሯ ተአምር የሰራለት ባል በአደባባይ ሲኮፈስ ጓዳው ውስጥ የሀሳቡን የብርታቱን የስኬቱን ባለቤት አስቀምጦ ነው፡፡

ዓለም ስለ ሴቶች ጭቆና የሚያወራበት ወቅት ላይ ሆነን ጥቂት ስልጡን ሀገራትን ደረት ያስነፋው የሴቶች መጠንኛ የሃይል /ስልጣን/ ተጋሪነት እንደ እኛ ላሉ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት ህዝቦች ምንም አይደለም ብንል ማን ከልክሎን? ዮዲትን ተረት ያስባላት የጀግንነቷ ልኬት ድንበር አልፎ መሰለኝ፣ የባቲ ድል ወንበሯን እልህ ከጽሑፍ በላይ ያደረገው የድፍረቷ መጠን እስከ ከመባል ቢያልፍ ነው፣ የእነ እቴጌ ሰብለወንጌል ወኔና ጥበብ፣ የእቴ ምንትዋብ ብስለትና የእነ እቴጌ ጣይቱን ቆራጥነት ነፍስ በዘራበት ምድር ሌላ ታሪክ አለ፡፡

ጌዴኦ ብሔር አባቶች ሴት ሀገር የመራችበትን የቀደመ ታሪካቸውን ያወጉታል፡፡ በጌዴኦ ባህል ሴት እስከ በሌለው ክብር ከታላቁ ስፍራ የምትቀመጥ ፍጥረት ናት፡፡ ጌዴኦ ሴት ወላድ በመሆኗ ንግስት ናት የሚል እምነት አለው፡፡ ይህ እምነት የተቀዳው ከነባር ባህሉ ነው፡፡ ጌዴኦ ሴትን እንዲያከብር የተባበሩት መንግስታት ቀን ሰይሞ ዘመቻ አለወጣበትም፡፡ ጌዶኤ ስለ ሴቶች አርቆ እንዲፈላሰፍ ፖስተርና ባነር አላጥለቀለቁትም፡፡ ባህሉ የሴት ልጅን መውለድ ማጥባት ማሳደግ የቤት ውስጥ ሃላፊነት የመሳሰሉ ክህሎቶችን ወደር አልባ አድርጎ ስለሚመለከት ለሴት ልጅ የሚሰጠው ክብር ከፍተኛ ነው፡፡

ስለሆነም የባህላዊ አስተዳደሩ መስራች ሴት ናት የሚል የቀደመ እምነት አለ፡፡
የጌዴኦ ባህል ዛሬም ይህንን ያሳያል፡፡ ጌዴኦ ተሰብስቦ ዛሬም አምላክን ሲለምን ሴትና ህጻናትን ከፊት አስቀድሞ ነው፡፡ ባህሉ ሴትና ህጻናት ንጹሃን ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም ማጌኖ ወይም ፈጣሪ እነሱ የቀደሙበትን ምህላ ይሰማል የሚል እምነት አለው፡፡ አኮማኖየ የሚባለው የጌዴኦ ባህላዊ አስተዳደር ሴት መር አስተዳደር ሲሆን ስርዓቱ በጎሣሎ ባህላዊ የአስተዳደር ስልት እስኪቀየር ድረስ በጌዴኦ ዘንድ የሰራ ባህል ነው፡፡

አኮማኖየ የአንዲት ሴት አስተዳደር መንግስትም አይደለም፤ ሥርወ መንግስት ነው፡፡ በዚህ ስርወ መንግስትም የተለያዩ ሴቶች እየተተካኩ ስልጣኑን በመያዝ አስተዳድረዋል፡፡ ይህ መተካካትም የአንዲት ሴት አኮማኖየ የአስተዳደር ዘመን በእድሜ ምክንያት ሲያበቃ ሌላኛይቱ እየተተካች ለረጅም ዘመን የቆየ የአስተዳደር ሥርዓት ነበር፡፡

ይህ ወቅት አስገራሚ ክስተቱ የስራ ክፍፍሉ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ሴቶች የሚሰሩት ልጅ የመመገብ፣ የማዘል፣ የመንከባከብ፣ ምግብ የማብሰልና እንጨት የመልቀም ተግባራትን የሚሰሩት ወንዶች ነበሩ፡፡ ይህንን እውነታ አንጋፋ የጌዴኦ ሀገር ሽማግሌዎች ከቀደሙት አባቶቻቸው እንደተቀበሉት ሁሉ ዛሬም ለልጆቻቸው ያወሱታል፡፡

ይህ ዘመን ብዙ ከዛሬው ዘመን ጋር የሚቃረኑ እውነታዎች ያሉት ነበር፡፡ ለምሳሌ ጋብቻ በሁለቱ ጥንዶች ስምምነት ቢከናወንም የጋብቻ ጥያቄው የሚቀርበው ግን በሴቷ ነበር፡፡ ጋብቻው ፍጻሜውን የሚያገኘውም በሴቷ ቤት ነበር፡፡ አኮማኖየ መንግስቱን እንደምታስተዳድረው ሁሉ በየቤቱ ያሉ እማወራዎችም የቤታቸው አስተዳዳሪ ነበሩ፡፡
የተወለደው ልጅ በእናቱ የሚጠራ ሲሆን የንብረት ባለቤትነት ደግሞ የሚስት ነው፡፡ ቤተሰባዊ አለመግባባቶች ሲከሰቱ ወሳኝ የሚባለው ውሳኔ የሚሰጠው በሴቷ ነው፡፡ ይህ ስርዓት ከዘውዳው አገዛዝ ጋር ተመሳሳይነት ሲኖረው ችሎትን ጨምሮ ውሳኔዎችን የምትሰጠው ደግሞ ንግስቲቷ ናት፡፡ ይህች ንግስት በምንም መልኩ ሴቶችን ተጎጂ የሚያደርግ ውሳኔ እንደማትሰጥ ይነገራል፡፡

ለአኮማኖዬ ስርዓተ መንግስት መውደቅ ምክንያት የሚባለውን በተመለከተ የጌዴኦ አባቶች ሲገልጹ የወንዶች ጭቆና መብዛትና የሴቶች የበላይነት በከፍተኛ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣት ነው ይላሉ፤ ከዚያም ወንዶቹ ንግስቲቷን በመገርሰስ የወንዶች የበላይነትን በእያንዳንዷ ሴት ላይ የሚጭን አዲስ ሥርዓት ተመሰረተ፡፡

በመጨረሻም አኮማኖዬ የሚባለው ሥርዓት በወንዶች ምስጥራዊ አመጽ ተወግዶ የጎሣሎ አስተዳደራዊ ሥርዓት ተተካ፡፡ ዛሬም ግን በጌዴኦ ባህል ሴት ክቡር ናት፤ የተለየ ትርጉም ያላት ታላቅ አጋር፤፤

DireTube

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close