Connect with us

Sport

ከስፖርት ማዕድ_ አጫጭር የውጪ ስፖርታዊ መረጃዎች

Asfaw Juliana

Published

on

  1. የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀምራል። ሁለቱ የእንግሊዝ ክለቦች ማንቸስተር ሲቲና ቶትንሀም ከሜዳቸው ውጪ ባሴልንና ጁቬንቱስን ይገጥማሉ። ቶትንሀሞች በፕሪሚየር ሊጉ ሶስት ከባድ ጨዋታዎችን ማለትም ከማንቸስተር ዩናይትድ፣ ከሊቨርፑልና ከአርሰናል ጋር ገጥመው ነው ዛሬ ከአሮጊቶቹ ጁቬንቱሶች ጋር የሚገናኙት።ስፐርሶች በፕሪሚየር ሊጉ በሶስቱ ጨዋታዎች አስፈላጊውን ነጥብ ቢያገኙም የዛሬው ጨዋት ግን ሊከብዳቸው እንደሚችል ተገምቷል።በአንፃሩ ሲቲዎች ከባሴል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ሊቀላቸው ቢችልም በቻምፒዮንስ ሊጉ ያላቸው ደካማ ሪከርድ ግን የተሰጣቸውን ግምት ሊያፋርስባቸው ይችላል ተብሏል።ሁለቱም ጨዋታዎች ምሽት 4:45 ላይ ይካሄዳሉ።
  2. የቀድሞው ድንቅ ተጫዋች ፓትሪክ ክሊቨርት ልጅ የሆነው ጀስቲን ክላይቨርት በአያክስ እያሳየ ባለው ድንቅ አቋም የተነሳ በተለያዩ ክለቦች ራዳር ውስጥ ምግባቱ ይታወቃል። ማንቸስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ከአስራ ስምንት አመቱ ወጣት ተጫዋች ጋር ስማቸው የተያያዘ ክለቦች ናቸው። ጀስቲን በፕሪሚየር ሊጉ የመጫወት ፍላጎት እንዳለው ከዚህ በፊት ፍንጭ ቢሰጥም ሁለቱ የስፔን ክለቦች ግን የልጁ ቀንደኛ ፈላጊ መሆናቸው ዩናይትዶችን እና አርሰናል ተጫዋቹን የማግኘት ዕድል ሊያሳጣ ቸው ይችላል ተብሏል።
  3. አርሜኒያዊው ተጫዋች ሄነሪክ ሚኪታሪያን ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አርሰናል ያደረገው ዝውውር ትክክለኛ ምርጫ መሆኑን ተናግሯል። ሚኪ አርሰናል ኤቨርተንን አምስት ለአንድ በረታበት ጨዋታ ሶስት የጎል ኳሶችን አመቻችቶ ያቀበለ ሲሆን በስፐርሱ የደርቢ ጨዋታ ግን ይህን ሊደግም አልቻለም። ሚኪታሪያን በዝውውሩ ዙሪያ በሰጠው አስተያየት < አርሰናል የእግር ኳስ ዘመኔን የማድስበት ክለብ እንዲሆን እፈልጋለው።ሀያ ዘጠኝ አመቴ ላይ እንደመገኘቴ የመጫወት ዘመኔ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ስለሚጠናቀቅ በዚህ ሰዓት ጠንክሬ በመስራት በአርሰናል የታላቅነት ስም መትከል እፈልጋለው።> ሲል ሃሳቡን ሰንዝሯል።
  4. ጆሴ ሞሪንሆ በቶትንሀምና በኒውካስል ከሜዳቸው ውጪ ሽንፈትን ካስተናገዱ በኃላ በተከላካይ መስመር ተጫዋቾቻቸው ተስፋ መቁረጣቸው እየተነገረ ይገኛል፣ በመሆኑም ሁለቱ ተከላካዮቻቸውን ፊል ጆንስንና ክሪስ ስሞሊንግን በክረመቱ የዝውውር መስኮት በማሰናበት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ኦልድትራፎርድ ለማምጣት ማሰባቸውን የተለያዩ ጋዜጦች ዘግበዋል። ያልተረጋጋውን የዩናይትድ የተከላካይ መስመር ከአዲስ ለመመስረት በፖርቹጋላዊው እይታ ውስጥ ከገቡ ተጫዋቾች መካከል ሀሪ ማጉዬርና ራፋኤል ቫሬን ይገኙበታል።
  5. የቀድሞው የባርሴሎና አሰልጣኝ ሊዊስ ኤነሪኬ ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂና ከእንግሊዙ ቼልሲ የስልክ ጥሪ እንደደረሰው የስፔን ጋዜጦች አስነብበዋል።ኤነሪኬ ከባርሳ ጋር ከተለያየ በኃላ ከእግር ኳሱ አለም ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከሁለቱ ክለቦች የቀረበለትን አሰልጥንልን ጥያቄ ያስብበታል ተብሎ ይጠበቃል። ሊዊስ ኤነሪኬ በባርሴሎና የአሰልጣኝነት ዘመኑ ሁለት የቻሚፒዮንስ ሊግና የላሊጋ ዋንጫን ወደ ካምፕ ኑ እንዲመጣ ማስቻሉ የሚታወስ ነው።

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close