Connect with us

Lifestyle

ለአሥር ዓመታት የጠፋችው «አቢ»

Published

on

ለአሥር ዓመታት የጠፋችው «አቢ»

ከአስር ዓመት በፊት ነበር በጠዋት አቢ ነፋሻማውን የፔንሴልቬኒያ አየር ለመቀበል ከቤት የወጣችው። በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሁሉም የቤተሰቡ አባላት በአንድነት ተሰብስበው እየተጨዋወቱ ባሉበት ሰዓት ድንገት ነበር የወጣችው።

ከዚያ በኋላ በድጋሚ ወደቤት አልተመለሰችም። የአቢ ባልተለመደ ሁኔታ ቀኑን ሙሉ ከቤት መጥፋት ቤተሰቡን አሳስቦታል። ካሁን አሁን ትመጣለች ተብሎ ቢጠበቅም አቢ የውሃ ሽታ ሆና ቀረች።

የቤቱ ሰው ተደናግጦ ፍለጋ ጀመረ። ጎረቤትና ፖሊስ በአቢ መጥፋት ከቤተሰቡ እኩል ተደናግጠው ፍለጋውን አጧጧፉት። አቢ የገባችበት ሳይታወቅ ምስጢር ሆና ቀረች። ለቤተሰቡ የደስታ ምንጭ ነበረች እርሷ ከሌለች ሁሉ ነገር አይደምቅም። ተጫዋች እና ደስተኛም ነበረች። ከብዙ ድካም እና ኀዘን በኋላ ቤተሰቡ አቢ ሞታለች ከአሁን በኋላ እሬሳዋን እንኳን አናገኘውም ብሎ ተስፋ ቆረጠ።

ዓመታት ነጎዱ አቢ ተፈጥሮ ነውና በትዝታ ብቻ ልትታወስ በእነ ዴብራ ሲልቬርድ ቤተሰብ ልብ ውስጥ ተቀብራ ተረሳች።
ዓመታት እየነጎዱ እንደ ቀልድ አስር ዓመታት ተቆጠሩ።

የጥር 27 ቀን የ2017 ዓመት ግን የእነ ዴብራን የተቀበረ ተስፋ በድጋሚ በተአምር የሚያነሳ ዜና ተሰማ። ስልክ አቃጨለ። ዴብራ ነበረች ያነሳችው። አቢ የምትባል ውሻ አለችሽ። ከወዲያኛው ቀጭን ሽቦ ቤተሰቡን ያስፈነጠዘ ዜና ነበር። ቤተሰቡ ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ የሚወዷትን ውሻቸውን ማግኘታቸው እጅጉን አስገረማቸው።

በህይወት መኖሯ አስገራሚ ነበር። አቢ ይሄን ሁሉ ዓመት ከቤቷ 33 ማይል ርቃ በምትገኘው ፒተስብራ በምትባል ከተማ ውስጥ ጆርጅ በሚባል መልካም ሰው እንክብካቤ በድሎት ስትኖር ነበር።

አቢን ከቤተሰቦቿ ጋር ያቀላቀላት በሰውነቷ ላይ ተቀብሮ የነበረውን ማይክሮ ቺፕስ ነበር። ይህች ቺፕስ በውሾች ሰውነት ላይ የምትቀበር ሲሆን፤ የሩዝ ያክል መጠን ያለው ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ነው። ብዙ ጊዜ ውሾች ከቤታቸው ወጥተው ሲጠፉ በዚህ መሳሪያ አማካኝነት ይገኛሉ።

በአቢ ላይ የተቀበረው ግን ለአስር ዓመት ውጤታማ ባይሆንም እንደ ድንገት ተንከባካቢዋ ጆርጅ ቺፕሱን ከአቢ ሰውነት ላይ በማግኘቱ ለቤተሰቦቿ አስረክቧል። ዴብራ ስለ ውዷ ውሻቸው ለኤቢሲ የቴሌቪዥን ጣቢያ ስትናገር «አቢ ከሞት የተነሳች ያህል ነው የተሰማን። ሁሉም ቤተሰብ ይወዳታል። እሷም ሁሉንም ነገር አልረሳችውም ስላገኘችን በጣም ደስ ብሏታል» ብላለች።

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close