Art and Culture
የመቻቻል እሴትን ለማጎልበት የሚያስችል “Our Ethiopia” የቪዲዮ ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ፤ ጥር 9፣2010 ዓ.ም. – የአሜሪካ ኤምባሲ “Our Ethiopia” በሚል ጭብጥ የሚካሄደውን የዚህ ዓመት የቪዲዮ ውድድር መጀመርን ሲያበስር በደስታ ነው፡፡
የቪዲዮው ውድድር፤ ኤምባሲው ነፃና አዎንታዊ የሀሳብ ልውውጥን በማበረታታት፤ ተቻችሎ የመኖርን እና የብዝሃነትን አወንታዊ ሚና ለማጉላት የሚያደርገው ጥረት አካል ነው፡፡
ዓለም አንድ መንደር በሆነች በዚህ ዘመን፤ ሰዎች ዋጋ እና ክብር እንዳላቸው እንዲሰማቸው የሚያደርግ እና የየራሳቸው ሀሳብና ህልም ያላቸው ሰዎች ተሰሚነት የሚያገኙበትን ማህበረሰብ ለመፍጠር መቻቻል አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ የቪዲዮ ውድድርም እነኚህን እሴቶች ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡
በዚህ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ክፍት በሆነው የቪዲዮ ውድድር፤ የፊልም ባለሙያዎች የሦስት ደቂቃ ርዝመት ያለውና፤ ስለ ኢትዮጵያ ብዝሃነት ጠንካራ ጎኖች፤ ስለሀገሪቱ ተግዳሮቶች፤ እንዲሁም ዜጎቿ መቻቻልን እና የርስ በርስ መከባበርን ለመደገፍ ማድረግ ያለባቸውን ነገሮች የሚያሳይ መሆን ይኖርበታል፡፡
የውድድሩ አንደኛ ደረጃ አሸናፊ 80, 000 (ሰማኒያ ሺህ) ብር የሚገመት ሽልማት ተሸላሚ ሲሆን፤ ሁለተኛ ለሚወጣ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር እና ሦስተኛ ለሚወጣ 30, 000 (ሰላሣ ሺህ) ብር የሚገመት ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡
ተወዳዳሪዎች ሥራቸውን እስከ የካቲት 11, 2010 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ብቻ በዩቲዩብ ወይም በአሜሪካ ኤምባሲ የህዝብ ጉዳዮች ክፍል “Our Ethiopia” የቪዲዮ ውድድር ፖ.ሣ. ቁ. 1014 በሲዲ ወይም ዲቪዲ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ቪዲዮውን ዩቲዩብ በሚቀበላቸው ማናቸውም የአቀራረብ መንገዶች መጫን የሚቻል ሲሆን፤ ቪዲዮው ከተጫነ በኋላ አድራሻው በ AddisVideoChallenge@state.gov መላክ ይኖርበታል፡፡
ሁሉም ቪዲዮ በአማርኛ ቋንቋ መሰራት ያለበት ሲሆን፤ የእንግሊዝኛው ትርጉም በጽሑፍ በቪዲዮው ላይ መካተት ይኖርበታል፡፡ ኤምባሲው በማንኛውም ቪዲዮ ላይ፤ ሃይማኖትን፤ ዘርን፤ ባህላዊ እሴቶችን፤ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሠረት ያደረገ አድልዎን
ያለመቀበል መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ውድድሩ ዝርዘር መረጃ ለማግኘት https://et.usembassy.gov/ourethiopia-video-challengeguideline/
ይጎብኙ፡፡
-
Ethiopia4 days ago
መንግሥት ሆይ… እባክህ ንቃ!
-
Art and Culture4 days ago
ተዋጽዖ | በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
-
Entertainment1 day ago
ሕጻኑ ሳይንቲስት የኢትዮጵያን ድብቅ ኮድ ተናገረ! ክፍል 2
-
Ethiopia18 hours ago
ታራሚው ተሞሸረ
-
Entertainment1 day ago
‹‹ጠቅላያችን አንበሳ ጋር ፎቶ የሚነሱት መቼ ይሆን?››
-
Ethiopia4 days ago
ሲሾሙ በብቃቴ ሲወርዱ በጎሳዬ | በሬሞንድ ኃይሉ
-
Ethiopia1 day ago
ኢሳት አዲስ አባ: ግንቦት ሰባት ማርቆስ: በረከት እስር ቤት የገቡበት የካቲት 11
-
Ethiopia5 days ago
ለፈጣሪም፣ ለመንግስትም፣ ለራሱም የማይመች ሕዝብ – ከአብዱራህማን አህመዲን