Connect with us

Art and Culture

አንድ ሺሻ ማጨስ 20 ሲጋራዎችን ማጨስ ከሚያስከትለው ጉዳት ጋር ይስተካከላል ተባለ

Published

on

አንድ ሺሻ ማጨስ 20 ሲጋራዎችን ማጨስ ከሚያስከትለው ጉዳት ጋር ይስተካከላል ተባለ

አንድ ሺሻ ማጨስ 20 ሲጋራዎችን ማጨስ ከሚያስከትለው ጉዳት ጋር ይስተካከላል ተባለ

አንድ ሺሻ ማጨስ 20 ሲጋራዎችን ማጨስ ከሚያስከትለው ጉዳት ጋር እንደሚስተካከል የጤና ባለሞያዎች ገለጹ፡፡

በቱኒዚያ ከሚገኙ አጫሾች 60 በመቶ የሚሆኑት ሺሻ እንደሚያጨሱ የገለጹት ባለሞያዎቹ አንዳንዶች ሺሻ በጤናቸው ላይ ስለሚያስከትለው ጠንቅ እንኳ አያውቁም ተብሏል፡፡

የጤና ባለሙያዎች ግን አንድ ሺሻ ማጨስ 20 ሲጋራዎችን ማጨስ ከሚያስከትለው ጉዳት ጋር ይስተካከላል ብለዋል፡፡

ሺሻ በጤና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት አንጻር ቱኒዚያ ከፍተኛ ቁጥጥር ለማድረግ መዘጋጀቷን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ኬንያ ከታኅሳስ 19/2010 ዓ.ም ጀምሮ ሺሻ ማስመጣት፣ መሸጥም ሆነ መጠቀም የሚከለክል ሕግ አውጥታለች።

የኬንያ ጤና ሚንስትር ክሌዎፓ ማይሉ እንዳስታወቁት ሺሻ ሲጠቀሙም ሆነ አስመጥተው ሲሸጡ የተያዙ ግለሰቦች 50 ሺህ የኬንያ ሽልንግና (500 ዶላር) ከ6 ወር በማያንስ እሥራት ይቀጣሉ።

ኬንያ ሺሻን በማገድ ከታንዛኒያና ከሩዋንዳ ቀጥላ ሦስተኛዋ አፍሪካዊት ሃገር ሆናለች።

ሸሻን የታገደው ከሚያደርሰው የጤናና ማሕበራዊ ቀውስ አንፃር መሆኑን የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሺሻ በኬንያ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን ከውሳኔው በኋላ ኬንያውያን ወደ ትዊተር በማምራት በእገዳው ዙሪያ ሲወያዩ ነበር፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት በቅርቡ ሺሻ ማጨስ ጤናን እንደሚጎዳ የሚጠቁም ጥናት ማውጣቱ ይታወሳል።

ፓኪስታን፣ ዮርዳኖስ፣ ሲንጋፖርና ሳዑዲ አረቢያ ሌሎች ሺሻን ያገዱ ሃገራት ናቸው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ሱስ በወጣቶች ላይ የደቀነው ስጋት

ወጣቶች ሁሉን ነገር ለማወቅ ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ለተለያዩ ሱሶች ለአደንዛዥ እጾች፤ለትንባሆ፣ ለአልኮል መጠጥና ለልዩ ልዩ ሱሶች የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ ነው …

ሱስ በወጣቶች ላይ የደቀነው ስጋት

ስለ ጫት፣ ሲጋራ፣ አልኮልና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች ጎጂነት በተለያየ አጋጣሚ ያልሰማ እንዲሁም በሰዎች ላይ ያደረሰውን ጉዳት ያልተመለከተ ወጣት አለ ለማለት ይከብዳል፡፡ ስለጉዳዩ አሳሳቢነትም በርካታ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ ዳሩ ግን ችግሩ እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ እየሰፋ መጥቷል፡፡ አሁን እየታየ ያለው የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚነት በዚሁ ከቀጠለ የወጣቱ ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ እንዲሁም የጤንነት ሁኔታውን አሳሳቢ ደረጃ ያደርሰዋል የሚል ስጋት እያሳደረ ይገኛል፡፡ የችግሩ አስከፊነት ግን ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ በመምጣት አገሪቱን ብዙ አምራች ወጣቶችን እያሳጣት ነው፡፡

ምንም እንኳን በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚስተዋል ቢሆንም በቅርብ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት መጤ ባህሎች ወጣቱ የአደንዛዥ ዕፅ ተጋላጭነቱ ከፍ እንዲል የሚያሳድሩት ተጽእኖ ከፍተኛ ነው። የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሰሞኑን «መጤ ባህሎችና ልማዶች በወጣቶች ሰብዕና ላይ የሚያደርሱት አሉታዊ ተፅዕኖና መፍትሔዎቻቸው» በሚል ርእስ አገር አቀፍ የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ ጥናታዊ ወረቀቶች የቀረቡ ሲሆን የጥናቶቹ አንደምታ የወጣቶች በሱስ ተጠቂነት ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ እንደመጣ የሚያሳይ ነው፡፡

በኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቋንቋና የጋራ ባህል እሴቶች ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ በኃይሉ ሽመልስ «አሉታዊ መጤ ባህሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ላይ እያስከተሉት ያለው አሉታዊ ገጽታዎች» በሚል ርዕስ አንድ ጥናት አቅርበዋል፡፡ የአቶ ሽመልስ ጥናት ሰፋ ያለ፣ በዘጠኙም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች ላይ የተሰራ ስለሆነ ከእርሳቸው ተጨማሪ ማብራሪያ በመጠየቅና ጥናቱን በማየት እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

ወጣትነት እና ለሱስ ተጋላጭነት

ወጣቶች ሁሉን ነገር ለማወቅ ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ለተለያዩ ሱሶች ይጋለጣሉ። ለአደንዛዥ እጾች፤ለትንባሆ፣ ለአልኮል መጠጥና ለልዩ ልዩ ሱሶች የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ ነው፡፡ ሀገር በቀል ያልሆነና ከሌላ የተወሰደ ሺሻ ማጨሽ እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚዘወተሩ ጫት መቃም፣ ቁማር፣ የቀንና የሌሊት ጭፈራ ቤቶችና ቦታዎች ላልተገቡ የአለባበስ ሁኔታዎች የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአሜሪካን አገር ከጠቅላላው ወጣቶች ቁጥር ግማሽ ያህሉ የመጠጥ፣ የተለያዩ አደንዛዥ እፆችና መድሀኒቶች ተጋላጮች ናቻው፡፡ ወጣቶቹ ወደእነዚህ ድርጊቶች ውስጥ የሚገቡበትን ምክንያት አንድም ለመነቃቃትና ጭንቀትን ለማስወገድ እንደሆነና የችግሩ ሰለባ የሆኑ ወጣቶችም በአብዛኛው እድሜያቸው ከ12 እስከ 17 መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በውጤቱም በዓመት በመጠጥ ሱስ ብቻ ከመቶ ሺ በላይ ወጣቶችና ሴቶች ይሞታሉ፡፡

አደንዛዥ ዕፅ በኢትዮጵያ

ጫት «ካታ ኢዱሊስ ፎርስክ» የተባለ ትኩስ ቅጠሎችን እና ግንዶችን በያዘበት ሁኔታ ጥቅም ላይ የሚውል ተክል ሲሆን በኢትዮጵያ፣ በኬንያና በሶማሊያ አገር በቀል ተክል ሆኖ በሰፊው የሚዘወተር እና ከ10 ዓመት በፊት በተገኘ መረጃ 50 በመቶ በሚሆነው የኢትዮጵያ ክፍል በተለይም በከተሞች አካባቢ የሚዘወተር ዕፅ ነው፡፡

ሱስ አስያዥ ዕፆችንና አልኮልን ቀላቅሎ ወይም አሰባጥሮ በመጠቀም ረገድ አዲስ አበባን ጨምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ ትንባሆ ከካናቢስ፣ ጫትን ከትንባሆና አልኮል ጋር፣ ጫትን ከትንባሆና ጠላ ወይም ጠጅ ጋር፣ ጫትን ከቡና ወይም ሻይ ጋር፣ ትንባሆን ከአልኮልና ቤኒዚን ጋር፣ ጫትን ከካናቢስና ከአልኮል ጋር እና ጫትን ከትንባሆ ጋር ቀላቅሎ የመጠቀም ልማዶች ታይተዋል፡፡

በመላ አገሪቱ በመስፋፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን ትንባሆ ካናቢስና ኮኬይን ወይም ሄሮይንን ቀላቅሎ የመጠቀም ሁኔታ በተወሰነ ሁኔታ ይታያል፡፡ በህገ ወጥ የዕፅ እና የመድሀኒት ዝውውር ቁጥጥር በየጊዜው ከሚያዙ አምፊታሚን፣ ባርቢቹሬትስ፣ ካናቢስ፣ ኮኬይን፣ ሞርፊን እና ሊሰርጂክ አሲድ /Lysergic acid/ ከሚባሉ ዕፆች ውስጥ ካናቢስ (እፀ-ፋርስ) ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ ይገኛል፡፡ የእነዚህ አደገኛ ዕፆች አጠቃቀምም እንደ ጫት ባሉ ቀለል ያሉ ዕፆች መጠቀሚያ ቦታዎችን እንደሽፋን በማድረግ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ የላላ የህግ ቁጥጥር ለሱስ አስያዥ ዕፆች እና መድሃኒቶች ዝውውር እና የመጠቀሚያ ቦታዎች መስፋፋት ምክንያት ሆኗል፡፡

በኢትዮጵያ በተደረገው ጥናት 69 ነጥብ ሰባት በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች በግለኝነት አስተሳሰብ ውስጥ ብቻ ያሉና ያልተገቡ የአለባበስ ሁኔታዎችን በመከተል በከፍተኛ ደረጃ ተፅዕኖ ሥር ናቸው፡፡

69 ነጥብ ሦስት በመቶ የሚሆኑ ሱስ አስያዥ እፆችን (ጫት፣ ሲጋራ፣ ሀሺሽ፣ ሺሻ…) እና የአልኮል መጠጦችን ይጠቀማሉ፡፡ እነዚህ አደንዛዥ ዕፆች ጥቅም ላይ የሚውሉባቸው ቦታዎች የተለያዩ ናቸው፡፡ በተደረገው የናሙና ጥናትም 19 ነጥብ ሰባት በመቶ የሚሆኑት ከሱቅ በመግዛት ቤት ውስጥ ይጠቀማሉ፡፡ 13 ነጥብ አራት በመቶ የሚሆኑት ለዚህ ተግባር በግልጽ በተዘጋጁ ቦታዎች በመሄድ፣ 24 ነጥብ ስድስት የሚሆኑት ደግሞ ከጓደኞቻቸው ጋር ቦታ በመምረጥ ይጠቀማሉ፡፡ 11 በመቶ የሚሆኑት ግን ለዚህ ተግባር አመቺ በሆኑና ድብቅ ቦታዎች ሲጠቀሙ አራት በመቶ በትምህርት ቤቶች ነው፡፡

የአደንዛዥ ዕፆች በዓይነትና በመጠን በተለያዩ አካባቢዎች ጥቅምላይ ቢውሉም ጫትና ሲጋራ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ ካናቢስን የመጠቀም ልማድ ከአፋር፣ ከኢትዮጵያ ሱማሌ እና ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ በስተቀር በሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች አልፎ አልፎም ቢሆን ይታያል፡፡

ለወጣቶች የሱስ ተጠቂነት ምክንያቶች

ወጣቶች በተለያየ ምክንያት ለሱስ ቢጋለጡም በዋናነት የተጠቀሱት መገናኛ ብዙሃን፣ የአደንዛዥ ዕፆች ነጻ ዝውውር፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ የመዝናኛ ቦታዎች በበቂ አለመኖር፣ የህብረተሰብ የግንዛቤ ክፍተት የመሳሰሉት ተጠቅሰዋል፡፡

ብዙ ወጣቶች ስለታዋቂ ሰዎች የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት የሚሰሙት በመገናኛ ብዙሃን ነው፡፡ በመገናኛ ብዙሃን በማየት የሚያደንቋቸውን ለመምሰል ሲሞክሩ የችግሩ ሰለባ ይሆናሉ፡፡

ምን ይደረግ?

በጥናቱ ከእድር መሪዎችና ከእምነት አባቶች ጋር በተደረገ ውይይት እንደተገለጸው ህብረተሰብና ቤተሰብ ልጆች አገር ውስጥ ሰርተው ከሚለወጡ ይልቅ ከእምነታቸውም ሆነ ከባህላቸው ጋር ወደማይመስሏቸው ሌሎች አገሮች ተሰደው መሄዳቸውን እንደ ክብር የመመልከት አስተሳሰብ አላቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ልጆቹ በአስተሳሰብ፣ በአካላዊና አእምሮአዊ እድገታቸው ሳይጎለብቱ ሳይወዱም ይሁን ወደው ይሰደዳሉ፡፡ በስደት ህይወታቸውም በሚኖሩባቸው አገራትና አካባቢዎች ለመጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች ይጋለጣሉ፡፡ ወደ አገር ሲመለሱም እዛ ያዩትን ሁሉ ይዘው በመምጣት ዛሬ በየአካባቢያቸው እያሳዩ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የሚስተካከለው የማህበረሰብ አስተሳሰብ ሲለወጥ ነው፡፡

የሱስ አስያዥና አደንዛዥ ዕፆች አጠቃቀምን ከመከላከል እና ህግን ከማስፈፀም አንፃር ያሉ የህግ ማዕቀፎችን እንደገና ማየት እና አዳዲስ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ተፈፃሚ ማድረግ ይገባል፡፡ የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት መስጫ፣ የባህል ኪነጥበብና የፈጠራ ውጤቶችን የሚያዘጋጁ፣ የማስታወቂያ፣ የመዝናኛና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ተቋማት የሚያቀርቡት አገልግሎት መፈተሽ አለበት፡፡ በወሰዱት የሙያ ፈቃድ እና በተቀመጠው የአሰራር መመሪያ መሠረት ስለመሆኑ ተከታታይነት ያለው ክትትል ድጋፍና ቁጥጥር ማድረግም ወሳኝ ነው፡፡ ከዚህ የአሰራር አግባብ ውጪ በሚሆኑት ላይ ግን፣ የማስተካከያና የእርምት እርምጃ መውሰድ እንደ መፍትሔ ተጠቁሟል።

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close