Connect with us

Ethiopia

ወደ ድንገተኛ አደጋ ጥሪ ማዕከላት የሚደረጉ የተሳሳቱ የስልክ ጥሪዎች የማእከሉን ስራ እያስተጓጎሉት ነው

Helen

Published

on

ድንገተኛ አደጋ ጥሪ ማዕከላት

በመላው አለም ድንገተኛ አደጋዎች እና ህመሞች እንዲሁም ወንጀሎች ሲያጋጥሙ የእርዳታ ምላሽ ለመስጠት የተቋቋሙ የጥሪ ማዕከላት አሉ፡፡ እኒዚህ ማዕከላት እርዳታ ፈልጎ የደወለውን ሰው ጥያቄ መሰረት በማድረግ ለተፈጠረው ችግር አፋጣኝ መፍትሄ የሚሰጡ ባለሞያዎችን ወደ ስፍራው ይልካሉ፡፡ ድንገቴ ለሆኑ አጋጣሚዎች ምላሽ የሚሰጡ ድርጅቶች አገልግሎታቸውን በአጠቃላይ በ3 ከፍለን መመልከት እንችላለ፡፡ እነሱም የአምፑላንስ ፤ የእሳት ማጥፋት እና የፖሊስ አገልግሎት ናቸው፡፡ ከ3ቱ አገልግሎቶች ውስጥ ሁለቱን አሊያም 3ቱንም አገልግሎት በአንዴ የሚፈልጉ ተረጂዎች ሊደውሉም ይችላሉ፡፡

ለምሳሌ እሳት አደጋ ቢያጋጥም እሳት የሚያጠፉ ባለሞያዎችን ከእሳት ማጥፊያ መኪና ጋር ብቻ መላክ በቂ አይሆንም፡፡ ከባለሞያዎቹ ጋር አምፑላንስ እና ፖሊስም አብሮ መላክ ይኖርበታል፡፡ አምፑላንሱ በቃጠሎው አሊያም በጭሱ ሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ካለ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም ለማድረስ ሲሆን ፖሊስ ደግሞ አካባቢውን እንዲያረጋጋ እና እሳት መነሳቱን ተገን አድርገው የዘረፋ ወንጀል ሊፈጽሙ የሚችሉ ሰዎች ካሉ እነሱን ለመከላከል ነው፡፡

ባደጉት ሀገራት ሰዎች እነዚህን በ3 ዘርፍ ተጠቅልለው የሚገኙ በርካታ የእርዳታ አይነቶችን ለማግኝት ወደተለያዩ ቦታዎች መደወል አይጠበቅባቸውም፡፡ አንድ የተዘጋጀ አጭር ስልክ ቁጥር አለ ፤ ሲደውሉም እንደሚፈልጉት የእርዳታ አይነት ከሚመለከተው አካል ጋር እንዲገናኙ ይደረጋሉ፡፡

በሀገራችን ግን ፖሊስን ፤ እሳት አደጋን ፤ ቀይ መስቀልን እና ሌሎቹን የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪ ተቋማትን ለማግኝት የግዴታ የተለያዩ ስልኮችን ማወቅ እና ስልኮቹ ላይ መደወል ያስፈልጋል፡፡ አገልግሎቱ ቀልጣፋ እንዲሆን ሁሉንም ጉዳዮች በአንዴ ተቀብሎ እንደየጉዳዮቹ አይነት ወደ ሚመለከተው ክፍል የሚመራ አንድ የጥሪ ማዕከል በሀገሪቷ መኖሩ እንዳለበት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሞያዎች ያደጉትን ሀገራት ተሞክሮ እየጠቀሱ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡

በሀገሪቷ ድንገት ለሚከሰቱ ችግሮ ምላሽ ከሚሰጡ አካላት ጋር የሚያገናኝ አንድ የታወቅ ስልክ ቁጥር ካለመኖሩም ባሻገር ህብረተሰቡ ያሉትን ቁጥሮች በአግባቡ ከመጠቀም አንጻር ከፍተኛ ከፍተት እንዳለበት ይገለጻል፡፡ የኢትዮጲያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው የዘርፉ አካላት ወደ ጥሪ ማዕከላቱ በርካታ የተሳሳቱ የስልክ ጥሪዎች እንደሚመጡ እና ይህም ስራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እያስተጓጎለ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

ወደ አሳት አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ባለስልጣን እና ወደ ፖሊስ በቀን ከ 300 ያላነሱ ጥሪዎች ይደርሳሉ፡፡ ከእነዚህ ጥሪዎች ውስጥ ደግሞ ተሳስተው የሚደውሉ እና ኦፕሬተሮቹ ላይ ለማሾፍ የሚደውሉ ሰዎች ቁጥራቸው ይበዛል፡፡ ም/ሳጅን አባትነህ ጌቴ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የማዕከል መረጃ ባለሞያ ናቸው፡፡ ስለጉዳዩም ሲናገሩ “የሚቀልዱ አሉ፡፡ ሰዎች በብዛት እየደወሉ እባካችሁን የ5 ብር አሊያም የ10 ብር ካርድ ሙሉልን ይላሉ” ብለዋል፡፡

የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር የማዕከል ባለሞያ የሆኑት አቶ ወንደሰን በበኩላቸው ደግሞ ለቀልድ ተብሎ እና በስህተት የሚደወለው ስልክ መብዛቱ በትክክል እርዳታ ፈልገው የሚደውሉት ሰዎች መስመሩን እንዳያገኙት በማድረግ በፍጥነት እርዳታ እንዳያገኙ እያደረጋቸው ይገኛል ብለዋል፡፡ ኢቢስ በዚህ ዙሪያ ያሰናዳውን ሙሉ ዘገባ እንዲከታተሉት እንጋብዛለን፡፡

ድንገተኛ አደጋ ፤ ወንጀል እና ህመም መቼ እንደሚያጋጥም አያታወቅም እና እኚህን ወሳኝ ቁጥሮች በህሊናዎ መዝገብ ላይ ቢያሰፍሯቸው መልካም ነው፡፡ ለፖሊስ 991 ፤ ለእሳት አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ባለስልጣን 939 ፤ ለጠብታ አምፑላንስ 8035 ለቀይ መስቀል 807 ላይ ይደውሉ፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close