Ethiopia
መሰረታዊ ፍላጎት ያልተሟላላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች

በአዲስ አበባ ተገንብተው ለነዋሪዎች የተላለፉ ባለ 12 ፎቅ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አሳንሰር ወይንም ሊፍት ስላልተገጠመላቸው ነዋሪዎች መቸገራቸውን ገለጹ፡፡ በጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ውስጥ የመጠጥ ውሀ አገልግሎት ባለመኖሩም አንድ ጀሪካን ውኃ እስከ 25 ብር ድረስ እየገዛን ነው ይላሉ ነዋሪዎቹ፡፡ አቶ ረጋሳ ነጋዋ አቅመ ደካማ አዛውንት ናቸው፡፡ እሳቸው እና ባለቤታቸው የቤት እድለኛ ሁነው ኑሯቸውን በልደታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች – ህንጻ ቁጥር 55 ላይ ካደረጉ 1 አመት ከ 4 ወር አልፏቸዋል፡፡ አቶ ረጋሳ እና ባለቤታቸው በዚህ ባለ 12 ወለል ህንጻ ላይ አሳንሰር ባለመገጠሙ የተነሳ 9ኛ ፎቅ ላይ ወደ ሚገኝው መኖሪያ ቤታቸው ለመግባት ዘወትር አድካሚ ጉዞ በደረጃ እንደሚያደርጉ ፤ ይሄም በስተእርጅና ከአቅማቸው በላይ እየፈተናቸው እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡
e style=”position: absolute;” src=”https://content.jwplatform.com/players/tWqJk2NG-1mWSWLQ5.html” width=”700″ height=”400″ frameborder=”0″ scrolling=”auto” allowfullscreen=”allowfullscreen”>
እስከ 2ኛ ፎቅ ለሱቅ አገልግሎትና ከዚያ በላይ ደግሞ 103 መኖሪያ ቤቶች ያሉት በ20/80 የቤቶች የግንባታ መርሀ ግብር ውስጥ ብቸኛውና እረጅሙ የልደታ ባለ 12 ፎቅ ህንጻ ከአሳንሰር አለመገጠም ባሻገር ውኃ አለመኖሩም ሌላኛው ከባድ ችግር እንደሆነባቸው አስተያየታቸውን ለኢትዮጲያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሰጡ ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡ ከውኃ እጥረት የተነሳም እንድ ጀሪካን ውኃም እስከ 25 ብር ድረስ እየገዙ መሆናቸው ለአላስፈላጊ ወጪ እየዳረጋቸው እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ የሊፍቶቹ አለመገጠም ችግር በዋነኛነት የተፈጠረው በሀገር ውስጥ የሊፍት አቅራቢ ድርጅቶች እጥረት በመኖሩ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ጽ/ቤቱ አያይዞም ከ 4 ወለል በላይ የሆኑ ከ አንድ መቶ የሚበልጡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በከተማዋ አሳንሰር እንዳልተገጠመላቸው ገልጿል፡፡ የጽ/ቤቱ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ተክሉ ፍቅሩ “የሊፍት አቅራቢዎች እጥረት ቢኖርም የተቻለውን ያክል ተገዝቶ ለህንጻዎቹ እንዲገጠም ከዚህ ቀደም የግዢ ሙከራ አድርገን ነበር ፤ ነገር ግን አጋጥመውን በነበሩ የቴክኒክ ችግሮች ሳቢያ ግዢው ሳይሳካ ቀርቷል” ብለዋል፡፡
“በልደታ ባለ 12 ወለል የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ያለባቸውን የመሰረተ ልማት ችግር የሚያጠና የቴክኒካ ኮሚቴ አቋቁመን ነበር” የሚሉት አቶ ተክሉ ፍቅሩ ኮሚቴውም ቦታው ድረስ ተግኝቶ ችግሩን እንደተመለከተ እና ሪፖርት እንዳቀረበላቸው ገልጸዋል፡፡ የነዋሪዎቹ ችግርም በቀረበው ሪፖርት መሰረት በቅርቡ እንደሚፈታ አስታውቀዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሲሉ ግን በሳምንታት ፤ በወራት ፤ አሊያም በአመታት ውስጥ የሚለካ የጊዜ ገደብ አላስቀመጡም፡፡
-
Ethiopia2 days ago
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አዳዲስ ተሿሚዎች ታውቀዋል
-
Entertainment4 days ago
አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ተሞሸረች
-
Ethiopia22 hours ago
ለሜቴክ እና ለኢንሳ አዲስ ዋና ዳይሬክተሮች ተሾሙ
-
Ethiopia4 days ago
ከህገ-መንግስቱ የተኳረፉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ!
-
Art and Culture2 days ago
በወርቅ የተሞላው ነገር ግን በሴጣን የተከበበው ተራራ
-
Ethiopia1 day ago
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሶስት ቁልፍ ቦታዎችን ለኦህዴድ መስጠታቸው ጠቃሚ እርምጃ ነው ተባለ
-
Ethiopia24 hours ago
‘የምሞት እየመሰለኝ በጣም ተጨንቄያለው’ ከመሞቱ ሶስት ቀናት በፊት የተናገረው
-
Entertainment22 hours ago
የአርቲስት ታምራት ደስታ የቀብር ሥነሥርዓት ተከናወነ