Connect with us

Business

የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ የውጭ ምንዛሪ የተዓቅቦ ጥሪን አስመልክቶ የሰጡት ምላሽ

Helen

Published

on

የውጭ ምንዛሪ

ከአለም አቀፍ የጋራ ኢትዮጵያውያን ግብረ ሃይል አባላት በአለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደሃገር ቤት የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ እንዳይልኩ የተዓቅቦ ጥሪ ተላልፎ ነበር። የሚመለከተው የኢትዮጵያ መንግስት አካልም በጉዳዩ ምላሽ ሰጥቶበታል።

“አለም አቀፉ የኢትዮጲያዊያን የጋራ ግብረ ሀይል” ካለፈው ሳምንት አርብ ጀምሮ በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን የውጪ ምንዛሬ ወደ ኢትዮጲያ እንዳይልኩ የተዕቅቦ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ግብረ ሀይሉ በዘመቻ መልክ ላቀረበው ጥሪ እንደዋነኛ ምክንያት ያቀረበው በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን የውጪ ምንዛሬ ወደ ሀገሪቱ መላካቸውን ከቀነሱ አሊያም ካቆሙ ገዢው መንግስት ህዝቡን ለማፈን ፤ ለመጨቆን እና ለመግደል የሚጠቀምባቸውን የጦር መሳሪያዎች የመግዛት አቅሙ ይዳከማል ፤ ለሰራዊቱም የሚከፍለውን ክፍያም ይቀንስበታል የሚል ነበር፡፡

አለም አቀፉ የኢትዮጲያዊያን ግብረ ሀይል በውጪ ሀገራት የሚኖሩ እትዮጲያዊያን ገንዘብ ወደሀገር ቤት እንዳይልኩ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ የኢትዮጲያ መንግስት ምለሽ ምን እንደሆነ ለማወቅ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የውጪ ገዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ወደሆኑት ወደ አቶ መለስ አለም ደውሎ ነበር፡፡

አቶ መለስ አለም ንግግራቸውን የጀመሩት “በመላው አለም ለሀገራቸው እድገት የራሳቸውን ሚና እየተወጡ የሚገኙ ኢትዮጲያዊያንን ከልቤ ላመሰግን እፈልጋለሁ” በማለት ሲሆን ቀጥለውም ከተአቅቦው ጋር የተያያዙ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ በእነ አቶ ፋሲካ እየተካሄ የሚገኝውንም የገንዘብ አትላኩ ዘመቻና ጥሪን “በአዲስ አመት የቀረበ አሮጌ ገጸ በረከት ነው” ሲሉ አንኳሰውታል፡፡

“በመላው አለም የሚኖሩ ወገኖቻችን ገንዘብ እንዳይልኩ የተያዘው ዘመቻ ገና ሳይወለድ የሚጨነግፍ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ሙከራ ተካሂዶ ነበር፡፡ ያኔ ዘመቻው መካሄድ ሲጀምር የሀገሪቱ ሪሚታንስ ወይንም ከውጪ ወደ ሀገር ቤት የሚላከው ምንዛሪ 300 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር፡፡ ከአመት ቡሀላ ይሄ ቁጥር ወደ 3.6 ቢሊዮን ዶላር አደገ፡፡ ከዛም 4 ቢሊዮን ሆነ፡፡ አሁን ደግሞ የመጨረሻው 4.6 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ይሄ የሚያሳየው በውጪ የሚኖሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሀገር ቤት ያሉ ወገኖቻቸውን ለመርዳት እንደሚፈልጉና ዘመቻውም ብዙ እርቀት ሊራመድ እንደማይችል” ብለዋል፡፡ ቃል አቀባዩ “የዘመቻው ሀሳብ በራሱ ቤተሰቦቻችሁን አትርዱ የሚል መንፈስ ያለው በመሆኑ ዲያስፖራውን የሚንቅ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የዘመቻው አስተባባሪዎች ዘመቻው የሚካሄደው ሀገር ቤት ያሉ ወገኖችን እምብዛም በማይጎዳ መንገድ እንደሆነ በአባላቸው በአቶ ፋሲካ ጌታሁን በኩል ለቪኦኤ ተናግረው የነበሩ ሲሆን ይህን ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ መንገዶች እንዳሉ ጠቅሰው ነበር፡፡ ከነዚህም መንገዶች ውስጥ ዋነኛው የሚላከውን ገንዘብ በተወሰነ መጠን መቀነስ ቢቻል ተደማምሮ መንግስት ላይ የሚያመጣው ቀውስ ብዙ መሆኑና ገንዘብም መላክ የግድ ከሆነ በቀጥታ መንግስት ገቢ በማያገኝባቸው አማራጮች አለመላክን አመላክተው ነበር፡፡
ያ ማለት ዲያስፖራው ዶላሩን እንደ ዌስተርን ዩኒየን እና እንደመኒ ግራም ባሉ የገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል ለቤተሰቡ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ ቢልክ የሚላከው ገንዘብ የመንግስት እጅ አይገባም የሚል ነው፡፡

አቶ መለስ የዘመቻ አስተባባሪው ቡድን አባል የሆኑት አቶ ፋሲካ ጌታሁን በሰነዘሩት በዚህ ሀሳብ ላይ ያላቸውን ስሜት ሲገልጹም “50 በመቶ ከውጪ የሚላከው ገንዘብ ለእንጀራ እና ዳቦ የሚውል ነው፡፡ 27 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ውጪ ያሉ ወገኖች ሀገርቤት ላሉ እህትና ወንድሞቻቸው ለደፍተር እና እስኪብርቶ መግዣ የሚልኩት ነው፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ደርሶ ገንዘብ አትላኩ ማለት በሁሉም አቅጣጫ ቢታይ ስሜት የማይሰጥ ነው” ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close