Connect with us

Africa

ኢሳያስ አፈወርቂ፣ቀጣዩ ሙጋቤ ወይስ የነገው ጋዳፊ?

Published

on

ኢሳያስ አፈወርቂ፣ቀጣዩ ሙጋቤ ወይስ የነገው ጋዳፊ?

ኢሳያስ አፈወርቂ፣ቀጣዩ ሙጋቤ ወይስ የነገው ጋዳፊ? | መላዕክነሽ ሽመልስ በድሬቲዩብ

የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ በሚገርም ፍጥነት እየተቀያየረ ነው፡፡የቀንዱ ፖለቲካ ተዋንያን አብዛኞቹ አምባገነን ናቸው፡፡በአምባገነን ፖለቲካ ውስጥ ደግሞ ነገን መተንበይ አይቻልም፡፡ለዚህም ብዙ ምስክሮች መጥቀስ ይቻላል፡፡

ከአካባቢው ፖለቲካ መሪዎች አንዱን ጠቅሰን እንመልከት፤ኢሳያስ አፈወርቂን!!

ኢሳያስ እልም ያሉ አምባገነን ናቸው፡፡ለዚህ መሃላ አያስፈልገውም፡፡እርሳቸው የሚመሩት ሕዝብ ቁጥሩ እስካሁን በውል አይታወቅም፡፡በሌላ ቋንቋ በኤርትራ ምድር ከ1923 ዓ.ም ወዲህ ሕዝብና ቤት ቆጠራ ተደርጎ አይወቅም፡፡ በኤርትራ በጀት ተመድቦም አያውቅም፡፡ሕግዴፍ ሥልጣን ከያዘ ወዲህ በጀት በምክርቤት አጸድቆ፣ ይህን ያህል ገንዘብ ለእንትን፣ ይህንን ያህል ፐርሰንቱን ለምናምን ብሎ ነገር የለም፡፡ በኤርትራ ምንም ዓይነት ሕግና ተቋም የለም፡፡ሁሉም የሚሰራው በግምት ነው፡፡በጀት በግምት ነው፡፡ሕዝብ ቁጥር በግምት ነው፡፡መሪነት በግምት ነው፡፡መገመት የማይቻለው የነገዋን ኤርትራ ብቻ ነው፡፡

ይህ ሁሉ ግምታዊ አሰራር ባለበት ሃገር አንድ ግዙፍ እውነት አለ፡፡ሁሉም ከ18 ዓመት በላይ ያለ ሕዝብ ወታደር ነው፡፡በሌላ አገላለጽ አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ ወታደር ነው ማለት ነው፡፡ወታደር በሚበዛበት ወይም ሁሉም ጠብመንጃ ነካሽ በሆነበት አገር፣ መፈንቅለ መንግሥት ሕዝባዊ አመጽ ሊቀሰቀስ እንደማይችል መከራከሪያ የለም፡፡

ኢሳያስና ጦራቸው፤

በ2013(እ.ኤ.አ) ቀለል ያለ የመፈንቀል ሙከራ አስተናግደው የነበሩት አቶ ኢሳያስ ጦሩን በፍጥነት ፐውዘውታል፡፡ለዓመታት ቀኝ እጃቸው የነበሩትንና ሲልኳቸው ወዴት ሲጠሯቸው አቤት ይሉ የነበሩትን ጀኔራል ሥብሃት ኤፍሬምን አንስተዋቸዋል፡፡አንስተውም የጨውና የታንታለም ሚኒስትር አድርገዋቸዋል፡፡በምትካቸው ጀኔራል ፊሊጶስ ወ/ዮሃንስ ተሾመዋል፡፡በ2013 በነበረው ግርግር ላይ ሚና ነበራቸው የተባሉት የሳህሉ ሰው ጀኔራል ዑመር በእስር ላይ ናቸው፡፡ጀኔራል ዑመር ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በወረረ ወቅት የባድመውን ግንባር ከመሩት የኤርትራ የጦር አበጋዞች አንዱ ናቸው፡፡እኒህን ሰው አቶ ኢሳያስ ጦሩ በሙስሊሞችም እየተመራ ነው ለሚለው ቅስቀሳቸው ለዘመናት ሲጠቀሙባቸው ነበር፡፡በመጨረሻ ግን እንዲህ ያለ ሆኗል፡፡ጄኔራል ዑመር በማይታወቅ ቦታ፣በማይታወቅ ሁነት ታሰሩ፡፡

በእንዲህ ሁኔታ እንደ አዲስ የተደራጀው የኤርትራ ጦር በአቶ ኢሳያስ ታማኞች የተሞላ ሆኗል፡፡ይህ አጋጣሚም በመሪያቸው ላይ የሚያምጹ ጀኔራል መኮንኖች ይኖራሉ ተብሎ የሚጠበቀውን ነገር ውድቅ ያደርገዋል፡፡በሌላ አገላለጽ የኤርትራ ሰራዊት እንደ ዚምቧብዌ ጦር የበረሃ ቃልኪዳኖቻንን ተሻሩ ብሎ ሊከራከር የሚችልበት ዘመን አልፎበታል፡፡ ምክንያቱም የኤርትራ ሕዝብና ሰራዊት የታገለላቸውን ሕልሞቹን የተቀማው ከግንቦት 16-1983 ዓ.ም አንስቶ ነውና!! መሪዎቹ ሲታሰሩ፣ሲገደሉ፣ሲታፈኑ፣አገሪቱ በአንድ ሰው መዳፍ ውስጥ ስትወድቅ ወዘተ ዝምም ብሎ 26 ክረምቶችን የተሻገረ ጦር፣ለአቶ ኢሳያስ ያለው ታማኝነትና ታዛዥነት ታይቶ በተደጋጋሚ የተዋቀረን ጦር የሚመሩ ጀኔራሎች፣እንደዚምቧብዌ አቻዎቹ በንጉሱ ላይ የሚያምጽበት ገፊ ምክንያት የለውም፡፡

ሌላኛው የኤርትራ ጀኔራሎች በንጉሳቸው ላይ ሊያምጹ የማይችሉበት ምክንያት እነርሱም ከሥርዓቱ ግንባር ቀደም ተጠቃሚ መሆናቸው ነው፡፡በአገሪቱ ትላልቅ ሕገወንጥ ንግዶች፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ግዙፍ የእርሻ ሥራዎች፣ወዘተ የሚካሄዱት በእነዚሁ ጀኔራሎች ነው፡፡እናም የጀኔራሎቹ ሥብስብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ በንጉሱ ላይ እንዳምጽ ያደርገዋል፡፡

ኢሳያስም እንደ ጃንሆይ?!

ጥያቄው እዚህ ጋር ነው፡፡አቶ ኢሳያስን ጀኔራሎቻቸው አይጥሏቸውም ከተባለ በምን ሊወድቁ ነው፡፡መቼም በንፋስ አይወድቁ፡፡ እናም ከንፋስ በላይ የሆነ ጉልበት ያስፈልጋል፡፡

ኤርትራ ውስጥ ብሶት አለ፡፡የጠፋው ብሶቱን የሚመራ የተደራጀ ኃይል ነው፡፡የኤርትራን ነገር የማይገመት የሚያደርገውም ይሄው ነው፡፡ነገር ግን የታችኛው የጦሩ ክፍል ማለትም ከኮሎኔልና በታች ያለው ኤርትራዊ ሰራዊት በአለቆቹና በኢሳያስ ወዳጆች ላይ ሊነሳ ይችላል፡፡ይሄኛው የጦሩ ክፍል ብሶትና ቅራኔ ያለው ነው፡፡ከአገር እየተሰደደ ያለው የጦሩ ክፍልም የዚሁ አባል የሆነ ነው፡፡ሥለዚህ በአፍሪካ ቀንድ የሚጠበቀው ዜና ኢሳያስ በሻለቆቻቸው ተወገዱ፣ የሚል እንጂ እንደ ዚምቧብዌው ያለ አይሆንም፡፡ወዲ አፎምም በሻለቆቻቸው የተወገዱ ዳግማዊ ጃንሆይ ኃይለስላሴ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ከዚያም እጣፈንታቸው ሁለት ነው፡፡በአንድ በኩል በታማኝ ወታደሮቻቸውና በተቃዋሚው መሀል በሚነሳ ግጭት እንደ ጋዳፊ ከፍልፈል ጉድጓድ ተጎትቶ መሞት፤ አለያም እንደሙባረክ ከቢሮአቸው ተጎትቶ መታሰር!!

ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን የኤርትራ ጦር ጠላትህ ኢትዮጵያ ነች የሚለውን የኢሳያስ ትርክት ትቶ፣ጠላቶቼስ እናንተ ናችሁ ማለት ሲጀምር ነው፡፡ DireTube

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close