Connect with us

Politics

የሰሜን ኮሪያና አሜሪካ ጉዳይ

Published

on

የሰሜን ኮሪያና አሜሪካ ጉዳይ

የፖለቲካ ተንታኞች ሰሜን ኮሪያ በሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ዓመታት አሜሪካንን በተምዘግዛጊ ሚሳይልዋ የማጥቃት ተግባሯን ልትቀጥልበት እንደምትችል ይገምታሉ፡፡ የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን አስተዳደር በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ፖለቲካዊ መፍትሔ ካልተበጀለት አህጉር ተሻጋሪ የባላስቲክ ሚሳይል የመልቀቅ ተግባሩ እንደሚቀጥልበት በሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የደህንነት ዘርፍ ሐላፊ ሚካይል ኡልያኖቭ ይናገራሉ፡፡

ሚሳይል የማምረት ፕሮግራም ፍጹም መቆም የሚገባው ሲሆን በአሜሪካና ሌሎች አገራት የሚጣሉ ማዕቀቦች ግን ለአራት ወይም አምስት ዓመታት ብቻ ሊቆዩ እንደሚችሉ ሐላፊው ይጠቅሳሉ፡፡ ሩሲያና አሜሪካ ሊያቀራርባቸው የሚችል ጉዳይ ቢኖር የሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ሁኔታ ሲሆን ይህም እንደ አሜሪካ ሩሲያም የሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ሐይል ፍጹም አትደግፈውም ብለዋል፡፡ ሩሲያና ቻይና ሁኔታውን ለማብረድ ለተወሰኑ ወራቶች ሰሜን ኮሪያ የሚሳይል ሙከራ እንድታስቆም እንዲሁም አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ በጋራ የሚያደርጉትን ወታደራዊ ልምምድ በመግታት የመደራደሩ ተግባር ዳግም እንዲጀመር ጥሪ ማድረጋቸውን ሐላፊው ጠቁመዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ አሜሪካ ለቀረበው የማደራደሪያ ሐሳብ አለመቀበልዋ እና የሰሜን ኮሪያ ህጋዊ ያልሆነው የኒኩሌር ሙከራ ተግባሯ መቀጠልም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀቦችን በመጣል ልትተናኮል ትፈልጋለች፡፡ በዚህም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከአቻቸው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር በቬትናም የኤስያ ፓስፊክ ኢኮኖሚክ ትብብር ጉባኤ አጀንዳ ላይ ይመክራሉ፡፡

ነገሩን ለማብረድ ያክል ሰሞኑን በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፕዮንግያንግ አስተዳደር የኒኩሌር ፕሮግራሙ ጉዳይ በጠረጴዛ ዙሪያ መፈታት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጉዳዩ ላይ የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርጉም በቀጥታ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ንግግር ለማድረግ ግን አልፈለጉም፡፡ አሜሪካ ዝግጁ ናት ማለታቸው ግን ሙሉ ወታደራዊ አቅማቸውን መጠቀም ትችላለች ለማለት መሆኑም ተንታኞች ይገልጻሉ፡፡

ሰሜን ኮሪያ በበኩልዋ፤ የኒኩሌር ፕሮግራሟ በአሜሪካ ለሚፈጸምባት ስርዓቱን የመጣል ትንኮሳ ለመከላከል እንደምትጠቀምበት ትገልጻለች፡፡ በቻይናና ሩሲያ የቀረበላት የድርድር ጉዳይም የመቀበል ወይም ያለመቀበል ምላሽ ሳትሰጥ መቅረቷ ኡልያኖቭ ጠቁመዋል፡፡ በጉዳዩ ምላሽ አለመስጠቷም የሚመጣውን ነገር እንደ አመጣጡ ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን የሚያመላክት ነው፡፡

ሰሜን ኮሪያ ባለፈው መስከረም ወር ባደረገችው ስድሰተኛው የኒኩሌር ሙከራ ተከትሎ ውጥረቱ እየተባባሰ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ ሙከራው አሜሪካን በስጋት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ፕሬዚዳንቱ ተናግረው ነበር፡፡ በተመሳሳይ ባለፈው ወር የፒዮንግያንግ ግዛትን የጎበኙ የሩሲያው የህግ ባለሙያ ሰሜን ኮሪያ ምዕራባዊ የአሜሪካ ድንበር መድረስ የሚችል የኒኩሌር ሃይል ለማስወንጨፍ በእቅድ ላይ መሆኗን መስማታቸውን አጋልጠው ነበር፡፡

በሌላ በኩል በሰሞኑ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኤስያ አገራት ጉብኝታቸው አምባገነኑ የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት አገሪቱን ወደ ምድራዊት ሲኦል የቀየረ መሪ በመሆኑ ዓለም ድጋፍ እንዳታደርግበት ጥሪ አድርገዋል፡፡ ትራምፕ በተለይ ቻይናና ሩሲያን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አገራት ማንኛውም የድጋፍ፣ አቅርቦትና ተቀባይነት ለኪም አመራር ማቆም እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ ፓርላማ ላይ በሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ትንኮሳ ዙሪያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ ማነኛውም ሀገር ለሰሜን ኮሪያ ድጋፍ ማድረግ እንደሌለበት አስገንዝበዋል፡፡ ጊዜ በወሰደን ቁጥር አደጋው ይበልጥ እየከፋ እንዲሁም አማራጮች ይበልጥ እየተባባሱ ይመጣሉ በማለት ተናግረዋል፡፡ ይህን አደጋ ለመከላከል ወይም ለመቀበል ደግሞ ሀገራት የራሳቸው ትክክለኛው የመቀበልና ያለመቀበል መብት ይሆናል ብለዋል፡፡

ከዚህ በመነሳት ተንታኞች የትራምፕ የኤስያ ጉብኝት ዋና ዓላማው ሀገራት በሰሜን ኮሪያ ላይ እንዲነሱ ለመቀስቀስ ነው በማለት ይገልጹታል፡፡ በቻይና ያደረጉት ጉብኝት ታሪካዊ መሆኑ በመጠቆም የትራምፕ እንቅስቃሴ የሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ፕሮግራም በውይይት ለመፍታት ከማቀራረብ ይልቅ ቁጣን የሚያስከትል እሳት የሚጭር ብለው የሚተቹም አልጠፉም፡፡ የትራምፕ አቋም ሰሜን ኮሪያ ጠብ ጫሪነቷን፣ የባሊስትክ ሚሳይል ማልማት ተግባሯን ካቆመች እንዲሁም ከኒኩሌር ሃይል ሙሉ በሙሉ ነጻ ከሆነች የተሻለች ሀገር ለማድረግ የሚያስችል መንገድ እንደሚያበጁላትም ተናግረዋል፡፡

አሁንም ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኪም ላይ የማስጠንቀቂያ አዘል ንግግራቸውን ያስተላለፉ ሲሆን ሰላም በኃይል ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ እንዲሁም ደቡብ ኮሪያን ለመደገፍ የሚያስችል ጠንካራ ማረጋገጫ መስጠታቸውን ይገልጻሉ፡፡ አሜሪካ ወይም አጋሮቿ አንዳችም ጥቃት ሊደርስባቸው አንደማይፈልጉ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፤ የአሜሪካ ከተሞች አንዳችም ጥቃት ሊደርስባቸው እንደማይገባ ለዚህም ህዝባቸው ስጋት እንዳይገባው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ንግግር በተለይ በተወሰኑ አናሳዎች ወይም አክብሮት የተነፈጉ የኪም አስተዳደር ፖሊሲዎች በማብጠልጠል የሰሜን ኮሪያ ህዝብ የዚህ ሰለባ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ እንደሚታወቀው ንግግራቸው አወዛጋቢ ሲሆን በደቡብ ኮሪያ ካደረጉት የትርክት ንግግር ላይም እንዲህ ብለዋል «አንድ ልጅ ከአባቱ ቻይናዊ በሰሜን ኮሪያ እንደተወለደና የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ለህጻኑ እናት ከቻይናዊ አባት በመወለዱ በህይወት መኖሩ ጠቃሚ አለመሆኑን እንደነገሯት» የሚገልጽ ትርክት አቅርበዋል፡፡ አክለውም ለምን ቻይና ሰሜን ኮሪያን የመደገፍ ግዴታ ሊሰማት እንደሚገባ ይጠይቃሉ፡፡ ይህም ሰሜን ኮሪያ የቻይና ታሪካዊ ጠላት እንደሆነች ለማሳየት የተጠቀሙት ማስረጃ ነበር፡፡

በሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳለም ትራምፕ ይከሳሉ፡፡ በቅርቡ የሰሜን ኮሪያ ስደተኛ በሰጠው በሰሜን ኮሪያ ሰው ከመሆን እንስሳ መሆን በጣም ይበልጣል ባለው ሐሳብ ይስማማሉ፡፡ በዚህ ንግግራቸው ትራምፕ በሰሜን ኮሪያ አሰቃቂ ህይወት መኖሩን በመግለጽ ህዝቡ በራሱ እንደባሪያ ወደ ውጭ አገራት ለመሰደድ ሙስና ለመንግስት ባለስልጣናት ይከፍላሉ ብለዋል፡፡

በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ እአአ በ2014 የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት አሰቃቂ የሆነ ክስተት መኖሩ እናት ልጇን እንድትገድል መደረጓ፣ የሞቱ እስረኞችን አስክሬናቸው እንዲቃጠልና የተቀረው አካላቸው በገመድ ተጎትቶ እንዲወገድ ያደረገ ሰው በምሳሌነት በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ሪፖርቱ ከታማኝ ምንጮች የተገኘ ነበር፡፡ ይህ ሪፖርትም በሰሜን ኮሪያ ሰብአዊ መብት ጥሰት አለ ለሚለው የፕሬዚዳንት ንግግር ማስረጃ ይሆናል፡፡

ፕሬዚዳት ትራምፕ በንግግራቸው የሁለቱም ኮሪያዎች በንጽጽር አስቀምጠዋል፡፡ ዓለም በታሪክ ላባራቶሪ አሳዛኝ ክስተት በኮሙኒስቷ ሀገር ተመልክታለች፤ ይህም በሁለቱም ኮሪያዎች የሆነ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ንግግራቸው መረዳት እንደሚቻለው በርካቶች የትራምፕ ደጋፊዎች በኮሪያ ጦርነት ጊዜ ወታደር ነበር ጨምሮ በአንድ በኩል ሲሰለፉ ጥቂቶቹና የትራምፕ ተቃዋሚ የሆኑት በሌላ በኩል መሰለፋቸው አይቀሬ መሆኑ ነው፡፡

ከዚህ በመነሳትም የኋይት ኃውስ አማካሪዎች ፕሬዚዳንቱ በደቡብ ኮሪያ ያደረጉት ንግግር በሰሜን ኮሪያ ላይ ተጨማሪ ጫና ለመፍጠር የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ሊቀላቀሉበት የሚችል ለፕሬዚዳንቱ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ያስተላለፉት መልእክት በሰሜን ኮሪያ ላይ የዓለም ሀገራት ተጨማሪ ማእቀቦችን ለመጣል የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በተያያዘ ዘገባ ሩሲያ በኢራን የኒኩሌር ፕሮግራም ላይ ደስተኛ አለመሆኗን በመጥቀስ የትራምፕ አስተዳደር የኢራን ኒኩሌር ፕሮግራም ስምምነት አደጋ ላይ የጣለ ነው በማለት ይተቻል፡፡ እአአ በ2015 የኢራን ኒኩሌር ፕሮግራም የሚቆጣጠር ስምምነት በታህራንና አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝና ቻይና መካከል የተፈራረሙትን ስምምነት አሜሪካ ውደቅ ማድረጓን ይታወቃል፡፡ የተቀሩት ሌሎች አገራትና ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኢራን ስምምነቱን እየተገበረች ነው ይላሉ፡፡

የፕሬዚዳንት ትራምፕ በኢራን ኒኩሌር ፕሮግራም ጉዳይ ላይ ዳግም የመስማማት ፍላጎት በሩሲያ፣ ቻይናና አውሮፓውያን ሀገራት ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ኢራን በአሁኑ ጊዜ እስከ 3ሺ ኪሜ ርቀት የሚጓዝ ተመዘግዛጊ ሚሳይሎች አላት፡፡ ሩሲያ ጎረቤቷ ኢራንን የኒኩሌር ማብላያ ጣቢያ እንዲኖር አትፈልግም በዚህም የቴህራን ሚሳይል ልማት በመቃወም የእስላማዊ መንግስት መብት በዓለም አቀፍ ህግ እንዲተገበር ትደግፋለች፡፡ ዘገባው ከብሉም በርግ ድረገጽ የተገኘ ነው፡፡

በሪሁ ፍትዊ

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close