Connect with us

Health

አልኮልን አዘውትሮ መጠጣት በአንጎል ዋነኛ ክፍል የሚፈጠሩ ህዋሶችን እንደሚገድል ጥናት አመለከተ

Published

on

አልኮልን አዘውትሮ መጠጣት በአንጎል ዋነኛ ክፍል የሚፈጠሩ ህዋሶችን እንደሚገድል ጥናት አመለከተ

በአሜሪካ የቴክሳስ ህክምና ቅርንጫፍ ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት አልኮልን አዘውትሮ መጠጣት በአንጎል ዋነኛ ክፍል ላይ የሚፈጠሩና ለነርቭ ህውሶች መፈጠር ምክንያት የሚሆኑ አዳዲስ ህዋሶችን እንደሚገድል ገልፀዋል፡፡

በተለይም ሴቶች በጉዳቱ ግንባር ቀደም ተጠቂዎች እንደሚሆኑ ተመራማሪዎቹ በአይጦች ላይ ባደረጉት ጥናት የምርምር ግኝታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ጥናቱ በአልኮል ጫና ምክንያት በሴቶችና በወንዶች መካከል የአዕምሮ ለውጥ የተለያየ መሆኑን ለመጀመሪያ ግዜ ያሳየ ጥናት ሆኗል፡፡

አልኮልን አዘውትሮ መውሰድ ጫናው በአንጎል ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ጥንቃቄ የሚያሻ መሆኑን የጥናታቸው ውጤት እንደሚያሳይ ተመራማሪዎቹ ተናግርዋል፡፡

ግኝቱ ከባድ የሆነን የአልኮል ሱሰኝነት በርን ለመዝጋት መነሻ ሆኖ እንደሚያገለግልም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡‑ ሽንዋ

READ  ጸጉራችንን ሊጎዱ የሚችሉ አምስት አላስፈላጊ ልምዶች እና ሁኔታዎች
Continue Reading

Business

40 ሚሊዮን ብር በአፍሪካ የመጀመሪያው “የጤና ጣቢያ” አፍሪኸሊዝ ቴሌቪዥን አዲስ ፎርማት ይዞ ቀርቧል

Published

on

በአፍሪካ የመጀመሪያው “የጤና ጣቢያ” አፍሪኸሊዝ ቴሌቪዥን

አዲስ አበባ፣ ህዳር  2010 | ዋናው ነገር ጤና! ጤና ለሁሉም!!  | በይርጋ አበበ

40 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበት ከመቶ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያንንና ለመላው አፍሪካ የጤና ፕሮግራም ተመልካቾች አዲስ ፎርማት ይዞ ቀርቧል። የጤና ጣቢያው መሠረቱን ዱባይ አድርጎ አዲስ አበባ ደግሞ የሥርጭት አድማሱን መነሻ ተክሏል። ናይል ሳት እና ዩቴል ሳት ደግሞ መገኛዎቹ ሲሆኑ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ደግሞ የፕሮግራሙ ልሳኖች ናቸው። ሚሊዮን ብሮችን ይዞ የአልኮል ማስታወቂያ በመስኮቴ አያልፍም” ሲል አቋሙን የገለፀው አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ጣቢያ “ዓላማዬ ለህዝብ በጎና ረብ ያለው ነገር አቅርቤ ትርፍ ማግኘት ነው” ሲል በጣቢያው ኃላፊዎች በኩል አስታውቋል። በዚህ የቴሌቭዥን ጣቢያ ምሥረታ እና ቀጣይ ጉዞዎች ዙሪያ ትኩረት ያደረገውን ዘገባ ከዚህ በታች አቅርበነዋል።


አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥን ይዞ የተነሳውን የረጅምና አጭር ጊዜ ግብ ያቀረቡት የቴሌቭዥን ጣቢያው ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር ሜሎን በቀለ “ማህበረሰቡ የራሱን ጤና በራሱ መፍጠርና መንከባከብ እንዲችል ትክክለኛ የጤና መረጃዎችና ትምህርቶችን በመቀበል ጤናማ ማህበረሰብ መገንባት ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ዶክተር ሜሎን የጣቢያውን መከፈት ይፋ ባደረጉበት መግለጫቸው አክለው ሲናገሩም “በሀገራችን በጤና ላይ ያተኮረ ጋዜጠኝነት እንዲስፋፋ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ነው” በማለት አብራርተዋል።

ህብረተሰቡን በጤና መስክ ግንዛቤ እንዲኖረው ከማስቻል እና የጤና ዘጋቢ ጋዜጠኞችን ከማፍራት በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥት አሳክቼዋለሁ ያለውን የጤናውን ዘርፍ ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ተሞክሮ እንዲሆን ማሳየት ጣቢያው አንዱ የተነሳበት ነጥብ መሆኑን በመክፈቻው ማብሰሪያ ወቅት ተገልጿል።

ጣቢያው ህልሙን ለመኖር ወይም ራዕዩን እውን ለማድረግ በሰው ኃይል በኩል ምን ያህል ተደራጅቷል? ለሚለው ወሳኝ ጥያቄ ቀድሞ ያስቀመጠው ምላሽ “ከ40 የሚበልጡ ሃኪሞችን እና የሚዲያ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው። በዚህም የተነሳ በጣቢያው የሚተላለፉ የጤና ፕሮግራሞች ደረጃቸውን የጠበቁ እና በስፔሻሊስት ሀኪሞች ክትትልና ማብራሪያ የሚሰጥባቸው ይሆናሉ” ሲል ይፋ ያደርጋል። ለዚህ ደግሞ ከደረጃ በታች ወይም የሙያ ሥነ-ምግባር ያልተላበሱ ፕሮግራሞች ለህዝብ እንዳይቀርቡ የሚከታተል በጠንካራ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሚመራ ኤዲቶሪያል ኮሚቴ ማዋቀሩን የጣቢያው ኃላፊዎች ተናግረዋል። ከፍተኛ የምርምር ሥራ የሚከናወን እንደሆነም ኃላፊዎቹ አክለው ገልፀዋል።

READ  በስፔን 5 በኤች አይቪ የተያዙ ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተዘገበ


የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ ማሥታወቂያዎችን ይዘት፣ የጊዜ ርዝማኔ፣ ስለሚተላለፉበት መንገድ እና ተያያዥ ጉዳዮች የሚደነግግ አዋጅ አውጥቷል። በአዋጁ ከተጠቀሱት ህጎች መካከል በኦዲዮ ቪዥዋል ብሮድካስት ጣቢዎያች ለጤና ጎጂ እና አልኮል መጠጦች፣ እንደ ጥሬ ሥጋ የመሳሰሉ ምግቦች አይተዋወቁም ይላል። አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥን ደግሞ የጤና “ጣቢያ” እንደመሆኑ መጠን በጣቢያው ሥለሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ይዘት ምን አቋም አለው? የሚል ጥያቄ ለጣቢያው ኃላፊዎች ቀርቦላቸው ነበር።

ኃላፊዎቹ ሲመልሱ እንዲህ አሉ “እርግጠኛ ሆነን የምንናገረው የቱንም ያህል አጓጊ ገንዘብ ቢቀርብልን የቢራ ምርቶች በእኛ ጣቢያ አይተላለፉም” ሲሉ ፈርጠም ብለው ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት ተደርጎ የቀረበው “ጣቢያው ህዝቡን ጤናችሁን ጠብቁ” እያለ በሌላ በኩል ደግሞ “ትንሽ ጎንጨት አድርጉ” ብሎ መምከር ሙያዊ ሥነ-ምግባር የተከተለ ባለመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል። የትራፊክ ደህንነት ፕሮግራም የሚዘግብ ፕሮግራም በቢራ ፋብሪካ ስፖንሰር እንደተደረገው አይነት እርስ በእርሱ የሚጣረስ አሰራር በአፍሪኸሊዝ ቲቪ እንደማይስተናገድ ነው የተገለፀው።

ታዲያ ይህ ከሆነ ገቢያችሁ ምን ይሆናል? ተብሎ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ ጣቢያውን በገንዘብ የሚደግፉ አጋር አካላት እንዳሉት ኃላፊዎቹ ተናግረው፤ ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ የተሻለ የገበያ አማራጭ እና የማሥታወቂያ አሰራር እንደሚከተሉ ገልፀዋል። “በተለይም” ይላሉ የቴሌቭዥን ጣቢያው ኃላፊዎች “በተለይ የወተት ማሥታወቂያዊችን ብንመለከት ‘እንትን ወተት መጣላችሁ ግዙ እና ተጠቀሙ’ አይነት ሥለምርቱ ውስጠ ይዘት የማይገልፅ ማስታወቂያዎችን አስቀርተን ሥለ ወተቱ ይዘት እና ሥለሚያስገኘው ጠቀሜታ ሙያዊ ማስታወቂያ በመሥራት ተመራጭ ሆነን እንመጣለን” ብለዋል። ሌሎች የማሥታወቂያ መንገዶችን ተከትለው የጣቢያውን ገቢ እንደሚያሳድጉም ተናግረዋል።


የህክምና ሙያ እንደሌሎች ሙያዎች ሁሉ የራሱ የሆኑ ሙያዊ ቃላት (professional Jargons) ያሉት ሙያ ነው። እነዚህ ቃላት ደግሞ እንኳን በቴሌቭዥን በሚገልጽበት ፍጥነት ቀርቶ ሀኪሙና ታካሚው ፊት ለፊት ተቀምጠውም ሊግባቡባቸው አይችሉም። በዛ ላይ የአገራችን ህዝብ የትምህርት ደረጃ ሲታሰብ ደግሞ የቃላቱ “ምስጠራ” ይበልጥ ከባድ ይሆናሉ። በዚህ መልኩ ያሉ ችግሮችን ቀርፎ ህብረተሰቡ በሚገባው መልኩ እንዴት ይተላለፋል? የሚል ጥያቄ ለአፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ኃላፊዎች ቀርቦላቸው ነበር። ከጋዜጠኞቹ ለቀረበው ጥያቄ መልስ የሰጡት ኃላፊዎች የተባለው ችግር መኖሩንና እነሱም ለረጅም ጊዜ ያሰቡበት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም “ለተማረውም፣ ላልተማረውም ሆነ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል በሚገባው መጠን እንዲሰማ ተደርጎ ተቀርጿል” ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በቋንቋ ምክንያት ተመልካቹ እንዳይቸገር ከአማርኛው በተጨማሪ በሌሎች አገርኛ ቋንቋዎችም ፕሮግራሞች እንደሚያሰራጭ ተናግረዋል።

READ  የህብረተሰቡ መዘናጋት የኤች አይ ቪ ስርጭቱን እያስፋፋው ነው - የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ


አንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ በቀን ለ24 ሰዓት ስርጭት ሲጀምር በተለይም አንድን ሙያ ብቻ ማዕከል አድርጎ ሲጀምር የፕሮግራሞች መደጋገም፣ የሃሳብ መናጠብ እና ሌሎች ተመሳሳይ ችግሮች ይፈትኑታል። አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥንም ዋና ጭብጡ ጤና ላይ ብቻ አድርጎ በመነሳቱ የሀሳብ መናጠብ ገጥሞት ፕሮግራሞችን እየደጋገመ በማቅረብ ተመልካችን እንዳያሰለች ምን የቀየሰው መንገድ አለ? ለህዝብ መረጃን ለማድረስ የዜና ቡድኑ ምን ያህል ጠንካራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም።

ለሁለቱም ጥያቄዎች መልስ የሰጡት የጣቢያው ኃላፊዎች “የጤና ነገር ሰፊ ነው። ገና ያልተነካ በመሆኑ የሃሳብ መናጠብ አይገጥመንም” ሲሉ በእርግጠኝነት ተናግረዋል። በተለያዩ የጤና ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ የፕሮፌሽናል ባለሙያዎች ሰፊ ማብራሪያ በአስተማሪነትና በአዝናኝነት መንገድ ተዘጋጅቶ ስለሚቀርብ የሀሳብ እጥረት እንደማይፈጠር በቂ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

ጣቢያው ሲመሠረት ዋና ሃሳቡ የጤና ፕሮግራሞችን ማስተላለፍ ቢሆንም የዜና ሰዓት ጠብቆ ወቅታዊ መረጃዎችንም እንደሚያስተላልፍ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል። ለመገናኛ ብዙሃን በተበተነው ጋዜጣዊ መግለጫ ወረቀት እንደተመለከትነው “በህክምናው ዓለም የተገኙ አዳዲስ ግኝቶችን፣ ለጤና ጠቃሚ ምክሮችን፣ በሽታን የመከላከል ዘዴዎችንና አደጋን የመከላከል ዘዴዎችን፣ አዝናኝና ቀለል ባለ መልኩ ያቀርባል” ይላል። ከዚህ በተጨማሪም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መረጃዎች ባይኖሩበትም ሌሎች የመረጃ ዘገባዎች እና የስፖርት ዘገባዎችን ጣቢያው የሚያስተላልፍ መሆኑን ኃላፊዎቹ በአንደበታቸው ገልጸዋል።

ቴሌቭዥን ጣቢያው ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆንና “ረብ” ያለው ሥራ ይዞ ለመቅረብም ከተለያዩ የሙያ ማህበራት፣ ፖሊሲ አውጭዎች እና ሌሎች ማህበራት ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሱን ተናግረዋል።


አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥን ጣቢያ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የመጀመሪያው የጤና ጉዳዮች የሚተላለፍበት የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው። ይህ ጣቢያ በልዩነት ለመምጣት ለዓመታት ጥናት ላይ መቆየቱን ኃላፊዎቹ የተናገሩ ሲሆን፤ አምስት የዳይሬክተሮች ቦርድ የሚመራው ጣቢያ ነው። ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እና የፖለቲካ አስተሳሰብ ወገንተኝነት የፀዳሁ ነኝ ሲል የገለፀው አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኃላፊዎች እንደተናገሩት እና ድርጅቱ እንዳስቀመጠው ራዕይ የሚቀጥል ከሆነ በእውነትም ለአገሪቱ ህዝብ ጥሩ አማራጭ ሆኖ ይቀርባል ። ዋናው ነገር ጤና! ጤና ለሁሉም!!

READ  ጸጉራችንን ሊጎዱ የሚችሉ አምስት አላስፈላጊ ልምዶች እና ሁኔታዎች

Continue Reading

Health

ውበትን ለመጠበቅ በሚደረግ ሂደት የሚሰሩ ስህተቶች

Published

on

ውበትን ለመጠበቅ በሚደረግ ሂደት የሚሰሩ ስህተቶች

ንጹህና ጽዱ መሆንና ራስን መጠበቅ ከሚያስገኘው የደስተኝነት ስሜት ባሻገር ለጤንነትም መልካም ነው። በዚህ መልኩ ራስን ለመጠበቅ በሚደረግ ሂደት ደግሞ አምሮ ለመታየትና ለመዋብ የተለያዩ ነገሮችን ማድረግ የተለመደ ሊሆን ይችላል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ለመዋብም ይሁን አምሮ ለመታየት በሚደረግ ሂደት ውስጥ ግን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ። ሳያስተውሏቸው አልያም በድንገት ለመዋብና አምሮ ለመታየት በሚል የተለያዩ ስህተቶችን ይፈጽሙ ይሆናል።

ከዚህ በታች ያሉት ደግሞ ባለሙያዎች አምሮ ለመታየት በሚደረግ ጥረት የሚፈጸሙ ስህተቶች ብለው የዘረዘሯቸው ናቸው።

ቡና ከጠጡ በኋላ ጥርስን መቦረሽ፦ ቡናን ጨምሮ አሲድ፣ ስኳር እና ሶዳ የበዛቸውን መጠጦች ከጠጡ በኋላ ወዲያውኑ ጥርስን መቦረሽ አግባብ አይደለም።

ይህን ሲያደርጉ የላይኛወን የጥርስ ክፍል ጥንካሬውን እንዲያጣ በማድረግ ይጎዱታል፤ ይህም የጥርስዎን ውበት ያደብዝዘዋል።

ከዚያ ይልቅ ውሃ መጉመጥመጥ እና ከአንድ ሰዓት በኋላ በአግባቡ መቦረሽ ይኖርብዎታል።

ፀጉርን ሳይታጠቡ መዋኘት፦ ለመዋኘት ሲገቡ ምንጊዜም ፀጉርዎን ረጠብ ማድረግና መታጠብን አይዘንጉ።

የመዋኛ ገንዳ ውሃ ኬሚካል ስለሚኖረው ደረቅ ፀጉር ሲያገኝ በመነቃቀል እንዲገረጣ ያደርገዋል፤ ይህ የሚሆነው የገንዳ ውሃው ሙሉ በሙሉ ፀጉርዎን ስለሚያርሰው ነው።

ከዚያ ይልቅ ግን ፀጉርዎን በውሃ ታጥበው ቢገቡ በገንዳ ውሃው ሙሉ በሙሉ ስለማይርስ የሚደርሰውን አደጋ መቀነስ ይችላሉ፤ ከገንዳ ከወጡ በኋላም ፀጉርዎን መታጠብንም አይዘንጉ።

ሻምፖ ማብዛት ወይም ማሳነስ፦ ሻምፖ የጭንቅላት ቆዳ ድረስ ስለሚዘልቅ ከበዛ ጭንቅላት የተፈጥሮ ዘይቱን እንዲያጣ ሊያደርገው ይችላል።

ሲበዛ ፀጉርን የማድረቅና የማገርጣት ባህሪ ይኖረዋል፤ ይህ እንዳይሆን ደግሞ በአግባቡ መጠቀም ይኖርብዎታል።

በአብዛኛው የፀጉር ሻምፖን በሳምንት ከሁለት ቀናት በላይ ባይጠቀሙት ይመከራል፥ ከዚህ ባለፈ ግን ባለሙያዎችን ማናገርና ከፀጉርዎ አይነት ጋር የሚሄድ ሻምፖን መጠቀምን ይልመዱ።

READ  የምግብ ተመራማሪው እና የአዳዲስ አቀራረቡ ጥበበኛ የካሳንቺሱ ጫኔ አረፉ

ኮንዲሽነር አለመጠቀም፦ ገላዎን አልያም ፀጉርዎን ከታጠቡ በኋላ ኮንዲሽነርን አለመጠቀም መልካም አይደለም።

ከጊዜ እጥረት ወይም ከፍላጎት ማጣት በሚል ይህን አለማድረጉ ፀጉርዎ ወዙን እንዲያጣና እንዲደርቅ ያደርገዋል።

እናም ከታጠቡ በኋላ በተቻለ መጠን ኮንዲሽነሩን በማድረግ ፀጉርዎን ማዳረስና መለቃለቅ ልማድ ያድርጉ።

የጆሮ ኩክ ማውጫን አብዝቶ መጠቀም፦ ይህን ማድረጉ መልካም ቢሆንም በበዛ መልኩ መጠቀሙ ግን ችግር ያስከትላል።

የጆሮ ኩክ ማውጫን አብዝተው ሲጠቀሙ የጆሮ ኩክ ይበልጥ ወደ ውስጥ እንዲገባ ሊያደርገው ይችላል።

ይህ ደግሞ በሂደት የራሱ አሉታዊ ችግር አለውና በተቻለ መጠን የህክምና ባለሙያ በማማከር እንዴት መጠቀም እንዳለብዎት መረጃ ይያዙ።

ብብት አካባቢ ዲዮዶራንት መቀባት፦ ብብት አካባቢ የሚፈጠር ላብን ለማስቆም በተለይም ሰውነት ላይ የሚቀባውን ዲዮዶራንት መጠቀም በአግባቡ ካልሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው።

ይህን ማድረጉ ላብን ለማድረቅ ቢረዳም በምን መልኩ መጠቀም እንደሚገባ መመሪያውን መመልከትና በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል።

ማለዳ እንደነቁና ገላዎን ሳይታጠቡ? ወይስ ገላዎን ከታጠቡ በኋላ? ነው መጠቀም ያለብዎት የሚለውን መመሪያ መከተል ከሚደርስ አላስፈላጊ ጉዳት ይታደግዎታል።

የጺም ጸጉርን በተደጋጋሚ ሼቭ ማድረግ፦ ለማለስለስና ቆዳን ከጸጉር ለማጥራት በሚል አሁንም አሁንም ሼቭ የሚያደርጉት ከሆነ ጉዳት ያስከትላል።

ይህ መሆኑ የቆዳ ላይ መቆጣትን ጨምሮ፥ የመቆረጥ አጋጣሚና እሱን ተከትሎ ለሚመጡ ኢንፌክሽንና መሰል አጋጣሚዎች ይዳርጋል።

ይህም የጉንጭን ቆዳ አላስፈላጊ ገጽታ በመስጠት ገጽታዎን ሊያበላሸውም ይችላል፤ በተቻለ መጠን ሼቭ ሲያደርጉ አንድን ቦታ አለመደጋገም እና በጣም በስሱ ቢሆን ይመረጣል።

በሞቀ ውሃ በተደጋጋሚ ገላን መታጠብ፦ ሳይበዛና በጣም አልፎ አልፎ ይህን ማድረጉ ችግር አይኖረውም።

READ  በ‹‹ብርቱካን›› ፍቅር ለተለከፍኸው ወዳጄ !

ሙቅ ውሃ በተፈጥሮው ቆዳን የማድረቅ ባህሪ ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይህን በተደጋጋሚ መከወኑ ግን መልካም አይደለም።

ለበዛ ጊዜ በዚህ መልኩ ገላን መታጠብ ከሚያስከትለው የቆዳ ድርቀት አንጻር እርሱን መተውና ቀዝቃዛ ካልሆነ ደግሞ በጥቂቱ ለብ ያለ ውሃ መጠቀም።

ፊትን ስክራብ ማድረግ፦ ይህን ማድረጉ ፊት ላይ ያሉትን ቆሻሻዎች ለማስወገድ ቢያግዝም ዘለቄታዊ መፍትሄ ግን አይደለም።

አልኮልና የተለያዩ ነገሮች የበዙበትን መዋቢያ በመጠቀም ፊትን ስክራብ ማድረግ አይመከርም፤ ከዚያ ይልቅ ፊትዎን በቀን ሁለት ጊዜ መታጠብና የጎንዮሽ ጉዳት የማያስከትሉ የፊት ቅባቶችን ሃኪም በማማከር መጠቀም።

መዋቢያ ቅባቶችን አብዝቶ መጠቀም፦ ለመዋብና የቆዳ ጥራትን ለመጠበቅ በሚል የተለያዩ የቆዳ ቅባቶችንና መዋቢያዎችን መጠቀም የጎንዮሽ ጉዳት እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ከዚህ አንጻርም ያገኙትን መዋቢያ ቅባት ከመጠቀም መቆጠብና ሃኪም በማማከር የጎንዮሽ ጉዳት የሌላቸውን ቅባቶች መጠቀሙ ይመከራል።

የሳሙና አጠቃቀም፦ ሳሙናዎች ከያዙት ንጥረ ነገር አንጻር ቆሻሻን ለማጽዳት እጅጉን ቢጠቅሙም በአግባቡ ማድረግ ይገባል። ሳሙናዎችን ባልተፈቀደ ቦታ መጠቀምም የዚያኑ ያክል ከፍ ያለ ጉዳት ያስከትላል።

ለማጽዳት በሚል መራቢያ አለካላትና መሰል ቦታዎች ላይ ሳሙና በተደጋጋሚ መጠቀምንም ባለሙያዎች አያበረታቱም። ይህን ማድረጉ ለእነዚህ የሰውነት ክፍሎች አስፈላጊ የሆኑ ባክቴሪያዎችን ያስወግዳል።

ይህ ደግሞ እነዚህ የሰውነት ክፍሎች ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የሚረዳቸውን ነገር እንዲያጡ በማድረግ ለጉዳት ይዳርጋልና በጥንቃቄ ቢሆን ይመረጣል።

ከዚህ ባለፈም ጥፍርዎን ለመሞረድና ለማሰራት ካሰቡ የእግርዎን ፀጉር ለማስነሳት የያዙትን ፕሮግራም ማዘግየት ይገባዎታል።

ጥፍርዎን በሚሰሩበት አጋጣሚ የእግርዎን ፀጉር የሚያስነሱ ከሆነ ይህ ለጎጂ ባክቴሪያዎች መራባት ምቹ አጋጣሚ ስለሚሆን ለኢንፌክሽን ሊዳርግዎት ይችላል።

READ  ኩላሊት ሲጎዳ የሚታዩ 8 ምልክቶች

እናም ጥፍርዎን ከመሞረድዎ ከ24 ሰዓት በፊት የእግርዎን ፀጉር ባያነሱት ይመከራል፤ ቢቻል ከተሰሩ በኋላ መልካም ነው።

ከላይ ከተጠቀሱት ባለፈ ግን ወይንና መሰል አልኮል ነገር ሲጎነጩ ዘወትር ውሃ መያዝዎን አይዘንጉ።

ይህን ሲያደርጉ በመጠጡና በውስጡ ባለው አሲድና መሰል ንጥረ ነገር ሳቢያ ሊጎዳ የሚችለውን ጥርስዎን ማጽዳት ይችላሉ።

ከዚህ ባለፈም የሚከሰት ድርቀትን ማስወገድም ያስችልዎታልና ይጠቀሙበት።  webmd

 

Continue Reading

Environment

60 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ የግል መፀዳጃ ቤት የለውም- ተመድ

Published

on

60 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ የግል መፀዳጃ ቤት የለውም- ተመድ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዓለም ህዝብ መካከል 60 በመቶ ያክሉ በቤታቸው መፀዳጃ ቤት እንደሌላቸው አስታወቀ።

የመንግስታቱ ደርጅት ትናንት የተከበረው የዓለም የመጸዳጃ ቤት ቀን ምክንያት በማድረግ፥ ከመጸዳጃ ቤት የሚለቀቅ ውኃ አያያዝን ላይ ትኩረት መስጠት አንዳለበት አሳስቧል።

ይህንን ሁኔታም “ዓለም አቀፍ የንፅህና ጉድለት” በማለት በተለያዩ መረጃዎች አስደግፎ አቅርቧል። መረጃው እንደሚያመላክተው በመላው ዓለም 892 ሚሊየን የሚሆነውን ህዝብ ሜዳ ላይ ይፀዳዳል።

በተጨማሪም በአለም ዙሪያ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ከመፀዳጃ ቤት የሚለቀቅ ውኃ ሳይታከም ተመልሶ ወደ ተፈጥሮ ሃብት ይፈሳል።

መረጃው እንደሚያሳየው በቂ መፀዳጃ ቤት እና በቂ የንጽህና መጠበቂያ ስፍራ አለመኖር ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ባሉት እንደ ቻይና እና ህንድ ባሉ አገሮች ውስጥም እንድ ትልቅ ችግርነት ይነሳል።

ለዚህም እንደማሳያ በምሥራቅ የቻይና ግዛት የሻንዱንግ ከተማ የሆቴል ፅዳት ሠራተኞች የመኝታ ፎጣዎች ተጠቅመው ሽንት ቤት ስያፀዳዱ መታየታቸው አስቀምጧል።

በተጨማሪም ህንድ ውስጥ የሚገኘው ቦሊውድ የፊልም ኢንዱስትሪ፥ “መፀዳጃ ቤት” በተባለ የፍቅር ታሪክ ፊልሙ ባለፈው በአገሪቱ ያለውን ደካማ የማፀዳጃ ቤት አያያዝ ጉድለት በሚመለከት እንደማሳያ ማቅረቡን ተጠቁሟል።

ከዚህ በመነሳት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከመፀዳጃ ቤቶች የሚወጡ ቆሻሻዎች አወጋገድ ሰርዓትን በተመለከተ አራት ደረጃዎች አስቀምጣል።

ማጠራቀም፥ ከመፀዳጃ ቤቱ የሚወጣ ቆሻሻ ከሰዎች ንክኪ አርቆ በጽዳት እቃዎች እና በታንከር ውስጥ መቀመጥ አለበት ብሏል።

ማንሳት፥ ከመፀዳጃ ቤቱ የሚወጣ ቆሻሻ በቱቦ በማድረግ ወደ ማከሚያ ስፍራው ማጓጓዝ።

ማከም፥ ከመፀዳጃ ቤቱን የሚወጣ ቆሻሻ ወደ ውሃ ማከሚያ አከባቢ በመውሰድ የአከባቢውን ደህንነት በጠበቀ/በማይበክል ሁኔታ ማከም ያስፈልጋል።

READ  በስፔን 5 በኤች አይቪ የተያዙ ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተዘገበ

ማስወገድ ወይም እንደገና ጥቅም መጠቀም፥ በተገቢው መንገድ የታከመ ቆሻሻ ለኤሌትሪክ ኃይል ወይም ለምግብ ምርት እንደ ማዳበሪያ ሊያገለግል ይችላል ሲልም የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት በሪፖርቱ እንዳሰፈረው ብዙ አገሮች የአካባቢ ንፅህናን ለማሳደግ ሰፊ ሀብቶችን አፍስሰዋል። ለአብነት በቻይና “የመጸዳጃ አብዮት”፥ አካባቢን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ አነፍናፊዎችን (sensors) መጠቀም እንደ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ መሳርያ ተደርጎ ተወስዷል።

በተመሳሳይ በህንድ ውስጥ በአውሮፓውያኑ 2019 በእያንዳንዱ ቤት፥ ሽንት ቤት ለመገንባት የሚያስችል እቅድ መያዙን ተነግሯል።

 

 

ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን.

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close