Connect with us

Ethiopia

የባለውለታ ጀግናችን ወገንን የሚጣራ ድምጽ

Published

on

የባለውለታ ጀግናችን ወገንን የሚጣራ ድምጽ

አንድ ወቅት የኢትዮጵያ መሪ ፊት ቀርበው አብዮታዊው መንግስት ምን እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ? በሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው፤

የሰራሁት ለሀገሬ ነው፤ ከአብዮታዊ ሠራዊት የተለየ ምንም ነገር እንዲደረግልኝ አልፈልግም ያሉት ጀግና ውለታዋን በምትበላ ሀገር ለችግራቸው የሚደርስላቸው አጥተዋል፡፡
ስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ኢትዮጵያ ምንም አይደለችም፡፡ አባቶቻችን የደም ውጤት ናት፡፡ የመስዋዕትነት ዋጋ ናት፡፡ በየተራራው የወደቁ፣ በየሸለቆው የተረሱ፤ ስለ እናት ሀገር ፍቅር የተዋደቁ ጀግኖች የታሪክ ማስታወሻችን የቃል ኪዳን ርስታችን ናት፡፡

በሁሉም አቅጣጫ የቀደሙት ስለ ሀገር ፍቅር፣ ስለ ክብሯ፤ ስለ ሉዓላዊነት መስዕዋዕት ሆነዋል፡፡

የሱማሊያ ወራሪ የዚያድ ባሬን ቅዠት እውን አደርጋለሁ ብሎ ሲገሰግስ የገደበው የወገን ደም ነው፡፡ የገታው የጀግኖች የማይበገር ወኔ ነው፡፡ ውለታ መልሱልኝ፤ አቋቁሙኝ፤ ስለ ሞትኩላችሁ ልኑርባችሁ የማይል መንፈስ፡፡

መቶ አለቃ በቀለ በላይ ስማቸውን በኢትዮጵያ መንፈስ በጀግንነት የጻፉ ከሐኪም ጋራ ስር በሶፊት የተዋደቁ ፓራ ኮማንዶ ናቸው፡፡

የጦር ሜዳ ውሎአቸውን የጅግና ወሮታ በሚል ሰለሞን ለማ ገመቹ በድንቅ ሁኔታ ጽፎታል፡፡ የሚበልጠው ታሪካቸው በኢትዮጵያ የሉዓላዊነት መንፈስ ብራና ላይ የታተመ ነው፡፡

አንድ ወቅት በጀብዳቸው ገነው ስማቸው በአብዮታዊ ጓዶች ትልቅ ስፍራ አግኝቶ በታላቅ ክብር ጓድ ሊቀመንበር ፊት ቀርበው ነበር፡፡

የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ ይሄን ለመሰለው ጀግና አንዳች ነገር ሸልመው ደስታቸውን መወጣት ይፈልጉ ስለነበር፤ “አብዮታዊ መንግስት ምን እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ?” ብለው ይጠይቋቸዋል፡፡

ፓራ ኮማንዶው፤ ከጠላት ጋር ጉሬላ ገጥሞ ሀረርን የታደጋት ታሪካዊ ትውልድ አንዱና ሁነኛው ተዋናይ የሆኑት መቶ አለቃ በቀለ “ከአብዮታዊ ሰራዊት የተለየ እንዲደረግልኝ አልፈልግም፡፡ ለሃገሬ ክብር ስል የፈጸምኩት ተግባር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የጀግነት ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆኔ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ይህ ለእኔ በቂ ነው ጓድ ፕሬዝዳንት፡፡” ሲሉ መለሱ፡፡ ጓድ ሊቀመንበር ተደስተዋል፡፡ ባልተለመደ መልኩ ግንባር ስመው ደስታቸውን ገለጹ፡፡

እኒህ ጀግና ግን ዛሬ ሌላ ምዕራፍ መጥቶ ይሄንን ለሀገር የከፈሉትን ወርቃማ ታሪክ ሆን ብሎ የዘነጋ አዲስ ትውልድ አጋጥሟቸዋል፡፡ ስራ የላቸውም፡፡ ገቢ የላቸውም፡፡ የተዋደቁላት ሀገራቸው የከፍታ ዘመን ላይ ስለሆነች ጥድፊያ ላይ ናት፡፡ እሳቸውን ለመመልከት ጊዜ የላትም፡፡

በጽናት የተዋደቁላት ኢትዮጵያ ታሪካቸውን በዘለዓለማዊ ዶሴዋ ብትይዘውም መንቀሳቀስ አቅቷቸው አልጋ ላይ የሚገኙ ባለቤታውን ማሳከሚያ አጥተው ሀገርን ከወራሪ የታደጉት ጀግና ከምርኮኛ የከፋ ሕይወት እየኖሩ ነው፡፡ ውለታቸውን አጣጥመን፤ እሳቸውነታቸውን ጥለነዋል፡፡

የምንወዳት ኢትዮጵያ እንዲህ ባሉ ጀግኖች መስዕዋትነት የተገነባች ናትና መልካም እናድርግ፤ አንድ ጀግናን ደስ ከማሰኘት በላይ ጀግንነት የለም፡፡ እናም እስቲ ይሄን ጀግና እንርዳ!!

ስለሆነም መቶ አለቃ በቀለን በቻሉት አቅም ለመርዳት ከታች በተገለጹት የባንክ የማጠራቀሚያ ሒሳብ ቁጥር መጠቀም የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close