Connect with us

Business

እያሽከረከሩ መዝፈን ያስቀጣል!

Published

on

እያሽከረከሩ መዝፈን ያስቀጣል!

የደምጽ ብክለት የሚባል ነገር አለ፡፡ ይህ ደግሞ በትምህርት ቤቶች፣ በመኖሪያ ቤቶች፣ በጤና ተቋማት ወዘተ. አካባቢ ሲከሰት አካባቢው ሊረብሽ፣ ህሙማንን እና በየቤታቸው እረፍት ላይ የሚገኙ ሰላም ሊያጡ ሥራ ሊታወክ ይችላል፡፡ ያለመግባባት ምንጭም እስከ መሆን ይደርሳል፡፡

ይህ ችግር በትራንስፖርት ላይም ያጋጥማል፡፡ ሞባይል ጮክ ብሎ ማነጋገር፣ ቴፕ ካለቅጥ መክፈት ተለምዷል፡፡ ይህም በጨዋታ ላይ የሚገኙ ተጓዦች ውይይታቸው እንዲታወክ፣ ሞባይል የሚያናግሩ እንዳይደማመጡ፣ ጸጥታ የሚፈልግ፣ የታመመም ሆነ ጤነኛ ሰው ሰላሙን እንዲያጣ ያደርጋል፡፡

አንዳንድ አሽከርካሪዎች የተሳፋሪዎቻቸውን የውሎ ሁኔታ የስሜት ጣሪያ መገንዘብ አይፈልጉም፡፡ አንዳንድ አሽከርካሪዎች የሚፈልጉትን ሙዚቃ ወይም መዝሙር ከመጠን በላይ ከፍተው አብረው ይዘፍናሉ፤ ይዘምራሉ፡፡
ሙዚቃ ከጣሪያ በላይ መከፈቱ ያልተመቻቸው አንዳንድ ተሳፋሪዎች አፍ እላፊ አልፎም ተርፎ ጸብ እንዳይከሰት በሚል የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው ይጓዛሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ይቆጣሉ፤ እባክህ ቀንሰው ይላሉ፡፡ ዝጋው የሚሉም ጥቂት አይደሉም፡፡

ሌሎች በቀልድ መልከ አሽከርካሪውን ይሸነቁጣሉ፡፡ ሙዚቃው ሲበዛባቸው ረዳቱን ወይም ሾፌሩን ቢራስ አለ ወይ ብለው ታክሲውን መሸታ ቤት አስመሰልከው የሚል መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ ከፍተው ነው ወይ የሰጡሀ የሚሉም አሉ፡፡ ወደ ቴፑን እያመለከቱም ይቺ ነገር መቀነሻ የላትምን የሚሉም አጋጥመውኛል፡፡

በሀገራችን ችግሩ እያሳሰበ ቢመጣም ሕግ ፊት የቀረበ ጉዳይ ስለመኖሩ ግን እንጃ፡፡ ከዚህ በላይ የማይገባ ድምጽ አሰምተሃል ተብሎ በሕግም የተጠየቀ አሽከርካሪ ስለመኖሩ አላውቅም፡፡

የሲቲቪን ዘገባ ዋቢ አድርጎ ፎክስ የተሰኘው ድረ ገጽ ሰሞኑን ያሰነበበው ጽሑፍ ግን አሽከርካሪዎች የማይገባ ድምጽ ካሰሙ ሊቀጡ እንደሚችሉ አመላክቷል፡፡ በካናዳ ሞንትሪያል የሚኖረው ቶውፊክ ሞአላ የአውቶቡስ አሽከርካሪ ነው፡፡ ተሳፋሪዎቹን ከግንዛቤ ሳያስገባ እአአ 1990ዎቹ የወጣን ዘፈን ድምጹን ከፍ አድርጎ እያንጎራጎረ በማሽከርከሩ ለቅጣት ተዳርጓል።

«ሁሉም አሁን ይወዛወዝ» የሚል ዘፈን እያንጎራጎረ ሲያሽከረክር የነበረው ሞአላ፣ ፖሊስ ሲከታተለው ቆይቶ ውሃ ሊገዛ መኪና እንዳቆመ መንጃ ፈቃድ መያዙን ካረጋገጠ በኋላ ጥፋቱን በማሳወቅ «በሕዝብ ላይ ይጮኸሃል» በሚል 149 ዶላር ቅጣት ጥሎበታል፡፡

አሽከርካሪው ጥፋቱን ሊከድ ቢሞክርም በመጨረሻ ግን እየዘፈነ እንደነበረ አምኗል፡፡ በሞንትሪያል ሕግ መሠረት፤ የማይገባ ድምጽ በማሰማት የሕግ መተላለፍ የፈጸመ አሽከርካሪ ጸጥታን አደፍርሷል፣ ሥርዓተ አልበኝነትን አንግሷል በሚል እስከ ሁሉት ሺ ዶላር እንዲቀጣ ተደንገግጓል፡፡

«ድምጼ አስቀያሚ ስለመሆኑ በጭራሽ አላውቅም፣ ለዚያም ሊሆን ይችላል ቅጣቱ የተጣለብኝ፣ በሆነው ሁሉ በጣም ደንግጫለሁ፤ ፖሊስ ሥራው ነው፤ ሌሎችን ምቾት ነስቼ ሊሆን ይችላል፤ ይህን ያህል ቅጣት ይተላለፍብኛል ብዬ ግን አልጠበኩም» ያለው አሽከርካሪው፣ ይግባኝ ለመጠየቅ አስቧል።

አሽከርካሪዎቻችን ለሁሉም ነገር ጊዜ አለውና ይህም አለ ለካስ ብላችሁ ጠንቀቅ ብትሉ መልካም ነው ፡፡ለስው ብሎ ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ አይደል አባባሉስ፡፡ | እፀገነት አክሊሉ – ethpress

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close