Connect with us

Ethiopia

‹‹በህልም የተፈጠረ መወስለት ከሐጢያት ይቆጠር ይሆን?››

Published

on

‹‹በህልም የተፈጠረ መወስለት ከሐጢያት ይቆጠር ይሆን?››

‹‹በህልም የተፈጠረ መወስለት ከሐጢያት ይቆጠር ይሆን?›› | አሳዬ ደርቤ በድሬ ቲዩብ

እንዴት አደራችሁ ምዕመናን?
እኔ ከስንት መንጠራራትና ማዛጋት በኋላ የወሰደኝ እንቅልፍ ያልሆነ ህልም ውስጥ አስገብቶ ሲያዳክረኝ ካደረ በኋላ እንዱንም ሳልቋጨው አስበርግጎ ስለለቀቀኝ… ቀኔን የጀመርኩት በጸጸትና በንደት መሃከል ሆኜ እየተወዛገብኩ ነው፡፡

ከሁሉ አስቀድሜ መናገር የምፈልገው ነገር… ስተውንበት ያደርኩት ህልም እናት አገራችን ያለችበትን አስከፊ ሁኔታ ያላገናዘበና አንድ ታማኝ ባለትዳርን ያባለገ በመሆኑ በተባበረ ክንዳችሁ ብታወግዙት ቅር አይለኝም፡፡
በእውነቱ የልቤን ጥንካሬ የተረዳው ጋኒን ጊዜውን የኋሊት ጠምዝዞና ጭንቅላቴ ውስጥ ያለውን የጋብቻ ፋይል ሰርዞ… ከሰርጌ በፊት ወዳለው ዘመን በመመለስ ለትወናው ምቹ ሁኔታን ባይፈጥርልኝ ኖሮ ልሳሳት ባላቻልኩኝ ነበር፡፡ (ብሳሳት እንኳን እኔ አሳዬ ደርቤ ኮንዶሜን ደርቤ እንጂ…..Lol)
ወደ ህልሜ ላስገባችሁማ!

ሜክሲኮ አካባቢ ነው፡፡ (የህልም መቼቴን አዲስ አበባ ላይ ያደረገው ሰይጣን ሚስቴን የት እንዳደረሳት ‹‹እሱን ስትጸበል ታወራዋለህ!›› ብለን እንለፈው፡፡

እናላችሁ በቅርቡ ለሁለተኛ ጊዜ ሶሉን ያስቀየርኩትን ብቸኛ ‹ሹልቴክስ ጫማዬን› ከሚቀባልኝ ሊስትሮ ወንበር ላይ ተቀምጨ ይመስለኛል፡፡

ሊስትሮው ወደ ሰማይ ያንጋጠጠውን የጫማዬን ጫፍ በመዶሻ በመቀጥቀጥ መሬት ለማስነካት እየታገለ ‹‹መቼም ጋሼ ሂሳቡን ባግባቡ ብትመዘግበው ኖሮ ይህች ‹ጥሩንባ› መሰል ጫማህ ከተገዛችበት ዋጋ ይልቅ የተቀባችበት ዋጋ በእጥፍ መብለጡ አይቀርም ነበር›› ይለኛል፡፡

ከዚያም በሊስትሮው ድፍረት በሽቄ ጫማዬን ከእጁ ቀምቼ በማጥለቅና መሃል ቂጡን በካልቾ በመዛቅ ጠደፍ፣ ጠደፍ እያልኩኝ ስሄድ… መንገድ ላይ ከአንዲት አጭር ጉርድ ከለበሰች… ነዶ ጸጉሯን በማንጅራቷ አዙራ ያበጠ ጡቷ ላይ ከነሰነሰች… ብስል ፊት፣ መለሎ ቁመት፣ የጎመራ ከንፈር፣ ጉደኛ ‹ፖስቸር› ካላት ‹ምልዑና ደንቧሻ› ሴት ጋር እገጣጠማለሁ፡፡ (ምነው በሌላ መንገድ ሄጄ በሆነ!)

READ  መድረክ ከጥልቅ ተሀድሶ አፈጻጸም ጋር አያይዞ ገዥውን ፓርቲ አብጠለጠለ

ልጂቱ እየቀረበችኝ በመጣች ቁጥር ኮስሞቲክስ አልባ ውበቷ አስገርሞኝ አፌን ከፍቼ ሳዘግም የሆነ ድንጋይ ያነቅፈኝና በአፍ-ጢሜ ልተከል ስል ለስላሳና ውብ ጭኗን ጨምድጄ ለጥቂት እተርፋለሁ፡፡

እናም እግሯን እንደጨመደድኩ ቀና ብዬ ስመለከታት ንጣትና ውበት ባንድ ላይ የታደለውን ጥርሷን አፍክታ ልክ እንደሚተዋወቅ ሰው ‹‹እኔ እኮ አላምንም!›› ትለኛለች፡፡

የት እንደማውቃት እያሰላሰልኩ እንዳለ ‹ጋኒኑ› በጆሮዬ ጠጋ ብሎ ‹‹የፌስቡክ ጓደኛህ እከሌ እኮ ናት›› ይልና ሊንኩን ያቀብለኛል፡፡

ከዚያም ‹‹ቤቲ ስዊት እንዳትሆኝ!›› ስላት እራሷ መሆኗን ጭንቅላቷን በመወዝወዝ ትነግረኛለች፡፡ (ስሟን ስለቀየርኩት ሰርች ማድረጉን ትታችሁ ተከታተሉኝ!)

እኔ ልሙትላችሁ የጋለበኝ ሰይጣን ከምኔው ከወደኩበት አስነስቶ፣ ከምኔው የባጥ የቆጡን አስወርቶ ለምሳ እንዳደረሰልኝ እሱ ይወቅ፡፡

‹‹ክላስ ነገር ይዘን ብንጫዎት ይሻል ይሆን?›› እላታለሁ፡፡
‹‹አይ ቤትህ ብንሄድ ይሻላል›› ትለኝና እግረ-መንገዷን የሸገር ልጅ አለመሆኗን ትነግረኛለች፡፡ (መቼም የሸገር ልጅ ብትሆን ኖሮ ላቀረብኩላት ጥያቄ ባለኮከብ ሆቴል እንጂ የተዝረከረከ ሳሎን አትመርጥም ነበር፡፡ (ሲጀመር የሸገር ሴቶች መኪናና ሱፐር ማርኬት መኖርህን ሳያጣሩ መቼ ወደገደለው ይገባሉ? በህልማቸው እንኳን ከእግረኛ ጋር የማይፎርሹ ጉዶች አይደሉ እንዴ?)
.
ትችቱን ትቼ ወደ ትዕይንቱ ስመለስ…. ቤትህ ውሰደኝ እንዳለችኝ የሆነ ታክሲ በአጠገቤ ሊያልፍ ሲል በፉጨት አስቆመዋለሁ፡፡ (በአፍላ የወጣትነት ዘመኔ ብዙ ጊዜ ሞክሬ ልለማመደው ያልቻልኩት ፉጨት እንዴት በህልሜ ሊከሰት እንደቻለ አልገባኝም፡፡)

አፏጭቼ ያስቆምኩት ታክሲ ውስጥ ልገባ ስል በገሃዱ ዓለም የምታስቸግሩኝ አንሶ በህልሜም ተከስታችሁ የተለመደ አበሻዊ ምቀኝነታችሁን ይፋ አደረጋችሁት፡፡

በሚገርም ሁኔታ እንደ ጉንዳን ተቀጣጥላችሁ ‹‹ስማ! እኛ እኮ እዚህ የተሰለፍነው ታክሲ እየጠበቅን እንጂ ጸሐይ እየሞቅን አይደለም›› ትሉኛላችሁ፡፡

READ  የዘንድሮ የኢሬቻ በዓልን በታጠቀ ሀይል አይታጀብም

‹‹እና ጸሀይ የሚያጠወልጋት ‹እንቡጥ አበባ› (እንዲሁም ቀዘባ) ይዤ እናንተ ጋር ተሰጥቼ ልዋል?›› በማለት ኮረዳዋን ታቅፌ ወደታክሲው ልገባ ስል አንባገነን መንግስታችሁ ላይ ልታሰሙት የሚገባውን ተቃውሞ አንድ ምስኪን ወንድማችሁ ላይ ታንጸባርቁት ጀመር፡፡ በዚህም የተነሳ ከህልሜ አልፎ እስካሁን ድረስ የዘለቀ ቅያሜየን በልቤ አኑሬ ጣኦቴን ከእናንተ ጋር ለማሰለፍ ተገደድኩኝ፡፡

ከዚያም ከሰልፉ መጨረሻ በመሄድ ከኮረዳዋ ጀርባ ላይ ተለጥፌ እንደ እርግብ አንገት የሚለሰልስ ማጅራቷን በስሱ ስስማት ‹‹አበስኩ ገበርኩ! አይ ስምንተኛው ሺ!›› አይነት ዝባዝንኬ እያወራችሁ ፋታ ታሳጡኛላችሁ፡፡ ይሄም ሆኖ ‹ይለይላችሁ› በማለት ከንፈሯን ለመጉረስ ስንጠራራ የሆነ እጅ ትከሻዬን ይዞ ወደ ኋላ ይስበኛል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ጉብሏም ፊቷን አዙራና ከንፈሯን ገርበብ አድርጋ ልትስመኝ ስትል እሷንም ጠፍንጋችሁ በመያዝ ‹‹በአደባባይ’ማ እንዲህ አይነት ብልግና አይፈጸምም›› ትሏታላችሁ፡፡ እናም በዚህ ድርጊታችሁ ኮረዳዋ ተበሳጭታ ፊት ለፊት ወደሚታየኝ ሆቴል በጣቷ እያመለከተች ‹‹ና ማርዬ እዚያ ሆቴል እንሂድና ክላስ እንያዝ›› በማለት በሎጋ ጣቷ እየሳበች ይዛኝ ትሄዳለች፡፡

ከዚያም ሆቴሉ ውስጥ ወዙ ችፍ ችፍ ያለ ዝልዝል ጥብስ በእኔ ሂሳብ ከጋበዝኳት በኋላ በዋሌቴ ከያዝኩት በርካታ ገንዘብ መሃከል ጥቂቱን ቀንሼ በማውጣት የምሳ ሂሳቡን ከአልጋው ጋር በመደመር ከፍዬ ወደተያዘልን ክላስ ልንገባ ስንል አንዲት አስተናጋጅ ወደ እኔ ትመጣና በድጋሜ እንዲከፍል ትጠይቀኛለች፡፡

‹‹ከፈልኩ እኮ›› ብያት ልሄድ ስል ኮሌታዬን ጨምድዳ ‹‹በፍጹም አልከፈልክም›› ብላ ድርቅ ስትል… ኮረዳዋ እየተቅለሰለሰች ‹‹እባክህን ውዴ ፍቅር የምንሰራበትን ሰዓት በክርክር አታሳልፈው›› እያለች ልታግባባኝ ብትሞክርም የገሃዱ ዓለም ባህሪዬን ከስቼ ‹‹ቆሜ ነው ሞቼ ሁለተኛ የምከፍለው›› እያልኩ ስንገታገት አስተናጋጇ ትከሻዬን እየወዘወዘች ‹‹ሳትከፍልማ አትሄዳትም›› ትለኛች፡፡

READ  የሀገራችን ስልጣን የነብር ጅራት ነው

እናም ውዝዋዜውና ንቅናቄው እየበረታ ሲመጣ የኮረዳዋ ፊት እየከሰመ፣ የሚስቴ ፊት እየለመለመ ይታየኝ ጀመር፡፡

ነገርዮው እየተከሰተ ያለው በህልም መሆኑ ሲገባኝም ከመባተቴ በፊት ከፍለ-ሐገር እያለሁ በህልሜ ስጠቀምበት የነበረውን የመንሳፈፍ ጥበብ እውን በማድረግ እንደ Spider man ኮረዳዋን አንጠልጥዬ ወደ አልጋ ቤቱ ይዣት ለመሄድ ተፍገመገምኩኝ፡፡ ሆኖም ግን አዲስ አበባ ላይ የሚካሄድ ህልማዊ ጉዞ በሰልፍ እንጂ በመንሳፈፍ የሚታጀብ ባለመሆኑ ሳይሳካልኝ ቀረ፡፡

ይሄም ሆኖ በቅጽበት ውስጥ ከወንደላጤነት ወደ ልጅ አባትነት ላለመዛወር ህልሜ ውስጥ ለመቆየት መፍጨርጨሬን አልተውኩም፡፡ ከዝልዝል ጥብስ ወደ ሽሮ ፈሰስ ላለመመለስ በከባዱ ተስለመለምኩኝ፡፡ ሙሉ በሙሉ ከመንቃቴ በፊትም ያለኝን ገንዘብ በሞላ ከእነ ዋሌቱ ለአስተናጋጇ ልሰጣትና ሸሚዜን ላስለቅቃት ተጣደፍኩኝ፡፡

ሆኖም ግን በአስተናጋጇ ተመስላ እጅ ከፍንጅ የያዘችኝ ሚስቴ ልትለቀኝ አልቻለችም፡፡ እናም የቲሸርቴ ኮሌታ ስፌቱ እስኪተረተር ድረስ ጨምድዳ እየሰባች ልታባትተኝ ስትታገል በእንቅልፍ ልብ ውስጥ ሆኜ ‹‹ምን ሆንሽ?›› የሚል ጥያቄ አወጣሁኝ፡፡

‹‹ሽሮው ሳይቀዘቅዝ ተነስና ቁርስህን ብላ እንጂ!›› ስትለኝ ‹‹በልቻለሁ ማለት አማርኛ አይደለም እንዴ? አንቺ ሴትዮ ግን የእንቅልፍ ክቡርነት የሚገባሽ መቼ ነው?›› ብያት ከአልጋዬ ላይ ተስፈንጥሬ በመነሳት ወደ ውጭ ወጣሁኝ፡፡

ከዚያም ስሟንና ብልግናዋን ያልረሳሁላትን ያችን አሳሳች ዉብ ኮረዳ በሚሴጅ ልክ-ልኳን ልነግራት ስሟን ፌስቡክ ላይ አስፍሬ ‹ሰርች› አደርጋት ጀመር፡፡ DIRETUBE

Continue Reading

Africa

ስለግድቡ በግብፅ መገናኛ ብዙሃን እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች በግንባታው ሂደት ላይ ተፅእኖ አይፈጥሩም-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Published

on

ስለግድቡ በግብፅ መገናኛ ብዙሃን እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች በግንባታው ሂደት ላይ ተፅእኖ አይፈጥሩም-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እና የተወሰኑ የመንግስት ተቋማት በኩል እየወጡ ያሉ አፍራሽ መረጃዎች በግንባታው ሂደት ላይ አንዳች ተፅእኖ እንደማይፈጥር የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፥ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ አትፈልግም ብለዋል።

ከ60 በመቶ በላይ የደረሰው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ብቻ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፥ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ከማፋጠን ጎን ለጎን ከግብፅ እና ሱዳን ጋር የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እና የተወሰኑ የመንግስት ተቋማት እያራመዱት ያለው አቋም ግን ከመርሆች መግለጫ ስምምነት ጋር የሚጣረስ፤ አፍራሽ ድርጊት ነው ብለዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኳታር ይፋዊ ጉብኝት አድርገው መመለሳቸውን እና በቅርቡ ካይሮ ውስጥ ሶስቱ ሀገራት 17ኛውን ድርድር አድርገው ያለ ስምምነት መለያየታቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ።

በተለይ የግብፅ የተወሰኑ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴን ግድብ ግንባታ ለማፋጠን ከኳታር ገንዘብ አግኝታለች የሚል መረጃ አሰራጭተዋል።

ከዚህ ባለፈም እየተካሄደ ያለው ድርድር ፍሬ ቢስ እየሆነ መምጣቱን እና ጉዳዩን ወደ አለም አቀፍ መድረክ ለመውሰድ ያላቸውን ፍላጎት በግልፅ አንፀባርቀዋል።

የተወሰኑ የሀገሪቱ ፖለቲከኞችም ባገኙት መድረክ ሶስቱ ሀገራት ካርቱም ውስጥ ከተስማሙት የመርሆች መግለጫ ወይም ያፈነገጠ አስተያየት በተደጋጋሚ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ አቶ መለስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ለማጠናቀቅ ከኳታር ገንዘብ አግኝታለች በሚል የዘገቡ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ፍፁም ተቀባይነት የሌሌው ሀሰተኛ እና የሌላ አጀንዳ ማስቀየሻ አድርገው ያቀረቡት መሆኑን ተናግረዋል።

READ  የዘንድሮ የኢሬቻ በዓልን በታጠቀ ሀይል አይታጀብም

“የግድቡ ግንባታ እየተከናወነ ያለው ሁላችንም እንደምናውቀው ያለ አንዳች ሀገር ድጋፍ፤ ያለ አለም አቀፍ ተቋም የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያዊያን ጉልበት፣ እውቀት እና ገንዘብ ነው” ብለዋል።

የአባይ ውሃ ከኢትዮጵያ 70 በመቶ የገፀ ምድር ውሃ፣ ሁለት ሶስተኛው የውሃ ሃይል የማመንጨት አቅም ከመያዙ ባሻግር፥ ከዘጠኝ ክልሎች ስድስቱን በሙሉ እና በከፊል የሚሸፍን ሲሆን፥ ይህም ከ36 በመቶ በላይ የሀገሪቱን የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፤ 45 በመቶ የሚሆን ህዝብ የሚኖርበት አካባቢ ነው።

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ዓለም አቀፍ ህግን አክብራ የአባይን ወንዝ የህዝቧን የአሁን እና የወደፊት ትውልድ ፍላጎት ለማሳካት መጠቀሟን አጠናክራ እንደምትቀጥልም በመግለጫቸው ላይ አረጋግጠዋል።

ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት 17ኛው የካይሮው የሶስቱ ሀገራት የውሃ ሀብት ሚኒስትሮች ድርድር ያለ ውጤት የተበተነው ግብፅ የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን በተለይ የ1929/1959 ስምምነቶች የድርድሩ አካል ይሁኑ በማለቷም እንደሆነ ነው ያነሱት።በስላባት ማናዬ  ኤፍ ቢ ሲ

Continue Reading

Business

40 ሚሊዮን ብር በአፍሪካ የመጀመሪያው “የጤና ጣቢያ” አፍሪኸሊዝ ቴሌቪዥን አዲስ ፎርማት ይዞ ቀርቧል

Published

on

በአፍሪካ የመጀመሪያው “የጤና ጣቢያ” አፍሪኸሊዝ ቴሌቪዥን

አዲስ አበባ፣ ህዳር  2010 | ዋናው ነገር ጤና! ጤና ለሁሉም!!  | በይርጋ አበበ

40 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበት ከመቶ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያንንና ለመላው አፍሪካ የጤና ፕሮግራም ተመልካቾች አዲስ ፎርማት ይዞ ቀርቧል። የጤና ጣቢያው መሠረቱን ዱባይ አድርጎ አዲስ አበባ ደግሞ የሥርጭት አድማሱን መነሻ ተክሏል። ናይል ሳት እና ዩቴል ሳት ደግሞ መገኛዎቹ ሲሆኑ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ደግሞ የፕሮግራሙ ልሳኖች ናቸው። ሚሊዮን ብሮችን ይዞ የአልኮል ማስታወቂያ በመስኮቴ አያልፍም” ሲል አቋሙን የገለፀው አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ጣቢያ “ዓላማዬ ለህዝብ በጎና ረብ ያለው ነገር አቅርቤ ትርፍ ማግኘት ነው” ሲል በጣቢያው ኃላፊዎች በኩል አስታውቋል። በዚህ የቴሌቭዥን ጣቢያ ምሥረታ እና ቀጣይ ጉዞዎች ዙሪያ ትኩረት ያደረገውን ዘገባ ከዚህ በታች አቅርበነዋል።


አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥን ይዞ የተነሳውን የረጅምና አጭር ጊዜ ግብ ያቀረቡት የቴሌቭዥን ጣቢያው ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር ሜሎን በቀለ “ማህበረሰቡ የራሱን ጤና በራሱ መፍጠርና መንከባከብ እንዲችል ትክክለኛ የጤና መረጃዎችና ትምህርቶችን በመቀበል ጤናማ ማህበረሰብ መገንባት ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ዶክተር ሜሎን የጣቢያውን መከፈት ይፋ ባደረጉበት መግለጫቸው አክለው ሲናገሩም “በሀገራችን በጤና ላይ ያተኮረ ጋዜጠኝነት እንዲስፋፋ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ነው” በማለት አብራርተዋል።

ህብረተሰቡን በጤና መስክ ግንዛቤ እንዲኖረው ከማስቻል እና የጤና ዘጋቢ ጋዜጠኞችን ከማፍራት በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥት አሳክቼዋለሁ ያለውን የጤናውን ዘርፍ ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ተሞክሮ እንዲሆን ማሳየት ጣቢያው አንዱ የተነሳበት ነጥብ መሆኑን በመክፈቻው ማብሰሪያ ወቅት ተገልጿል።

ጣቢያው ህልሙን ለመኖር ወይም ራዕዩን እውን ለማድረግ በሰው ኃይል በኩል ምን ያህል ተደራጅቷል? ለሚለው ወሳኝ ጥያቄ ቀድሞ ያስቀመጠው ምላሽ “ከ40 የሚበልጡ ሃኪሞችን እና የሚዲያ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው። በዚህም የተነሳ በጣቢያው የሚተላለፉ የጤና ፕሮግራሞች ደረጃቸውን የጠበቁ እና በስፔሻሊስት ሀኪሞች ክትትልና ማብራሪያ የሚሰጥባቸው ይሆናሉ” ሲል ይፋ ያደርጋል። ለዚህ ደግሞ ከደረጃ በታች ወይም የሙያ ሥነ-ምግባር ያልተላበሱ ፕሮግራሞች ለህዝብ እንዳይቀርቡ የሚከታተል በጠንካራ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሚመራ ኤዲቶሪያል ኮሚቴ ማዋቀሩን የጣቢያው ኃላፊዎች ተናግረዋል። ከፍተኛ የምርምር ሥራ የሚከናወን እንደሆነም ኃላፊዎቹ አክለው ገልፀዋል።

READ  የሀገራችን ስልጣን የነብር ጅራት ነው


የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ ማሥታወቂያዎችን ይዘት፣ የጊዜ ርዝማኔ፣ ስለሚተላለፉበት መንገድ እና ተያያዥ ጉዳዮች የሚደነግግ አዋጅ አውጥቷል። በአዋጁ ከተጠቀሱት ህጎች መካከል በኦዲዮ ቪዥዋል ብሮድካስት ጣቢዎያች ለጤና ጎጂ እና አልኮል መጠጦች፣ እንደ ጥሬ ሥጋ የመሳሰሉ ምግቦች አይተዋወቁም ይላል። አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥን ደግሞ የጤና “ጣቢያ” እንደመሆኑ መጠን በጣቢያው ሥለሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ይዘት ምን አቋም አለው? የሚል ጥያቄ ለጣቢያው ኃላፊዎች ቀርቦላቸው ነበር።

ኃላፊዎቹ ሲመልሱ እንዲህ አሉ “እርግጠኛ ሆነን የምንናገረው የቱንም ያህል አጓጊ ገንዘብ ቢቀርብልን የቢራ ምርቶች በእኛ ጣቢያ አይተላለፉም” ሲሉ ፈርጠም ብለው ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት ተደርጎ የቀረበው “ጣቢያው ህዝቡን ጤናችሁን ጠብቁ” እያለ በሌላ በኩል ደግሞ “ትንሽ ጎንጨት አድርጉ” ብሎ መምከር ሙያዊ ሥነ-ምግባር የተከተለ ባለመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል። የትራፊክ ደህንነት ፕሮግራም የሚዘግብ ፕሮግራም በቢራ ፋብሪካ ስፖንሰር እንደተደረገው አይነት እርስ በእርሱ የሚጣረስ አሰራር በአፍሪኸሊዝ ቲቪ እንደማይስተናገድ ነው የተገለፀው።

ታዲያ ይህ ከሆነ ገቢያችሁ ምን ይሆናል? ተብሎ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ ጣቢያውን በገንዘብ የሚደግፉ አጋር አካላት እንዳሉት ኃላፊዎቹ ተናግረው፤ ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ የተሻለ የገበያ አማራጭ እና የማሥታወቂያ አሰራር እንደሚከተሉ ገልፀዋል። “በተለይም” ይላሉ የቴሌቭዥን ጣቢያው ኃላፊዎች “በተለይ የወተት ማሥታወቂያዊችን ብንመለከት ‘እንትን ወተት መጣላችሁ ግዙ እና ተጠቀሙ’ አይነት ሥለምርቱ ውስጠ ይዘት የማይገልፅ ማስታወቂያዎችን አስቀርተን ሥለ ወተቱ ይዘት እና ሥለሚያስገኘው ጠቀሜታ ሙያዊ ማስታወቂያ በመሥራት ተመራጭ ሆነን እንመጣለን” ብለዋል። ሌሎች የማሥታወቂያ መንገዶችን ተከትለው የጣቢያውን ገቢ እንደሚያሳድጉም ተናግረዋል።


የህክምና ሙያ እንደሌሎች ሙያዎች ሁሉ የራሱ የሆኑ ሙያዊ ቃላት (professional Jargons) ያሉት ሙያ ነው። እነዚህ ቃላት ደግሞ እንኳን በቴሌቭዥን በሚገልጽበት ፍጥነት ቀርቶ ሀኪሙና ታካሚው ፊት ለፊት ተቀምጠውም ሊግባቡባቸው አይችሉም። በዛ ላይ የአገራችን ህዝብ የትምህርት ደረጃ ሲታሰብ ደግሞ የቃላቱ “ምስጠራ” ይበልጥ ከባድ ይሆናሉ። በዚህ መልኩ ያሉ ችግሮችን ቀርፎ ህብረተሰቡ በሚገባው መልኩ እንዴት ይተላለፋል? የሚል ጥያቄ ለአፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ኃላፊዎች ቀርቦላቸው ነበር። ከጋዜጠኞቹ ለቀረበው ጥያቄ መልስ የሰጡት ኃላፊዎች የተባለው ችግር መኖሩንና እነሱም ለረጅም ጊዜ ያሰቡበት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም “ለተማረውም፣ ላልተማረውም ሆነ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል በሚገባው መጠን እንዲሰማ ተደርጎ ተቀርጿል” ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በቋንቋ ምክንያት ተመልካቹ እንዳይቸገር ከአማርኛው በተጨማሪ በሌሎች አገርኛ ቋንቋዎችም ፕሮግራሞች እንደሚያሰራጭ ተናግረዋል።

READ  የ2017 የዓለም ውሃ ሃይል ጉባኤ በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል


አንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ በቀን ለ24 ሰዓት ስርጭት ሲጀምር በተለይም አንድን ሙያ ብቻ ማዕከል አድርጎ ሲጀምር የፕሮግራሞች መደጋገም፣ የሃሳብ መናጠብ እና ሌሎች ተመሳሳይ ችግሮች ይፈትኑታል። አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥንም ዋና ጭብጡ ጤና ላይ ብቻ አድርጎ በመነሳቱ የሀሳብ መናጠብ ገጥሞት ፕሮግራሞችን እየደጋገመ በማቅረብ ተመልካችን እንዳያሰለች ምን የቀየሰው መንገድ አለ? ለህዝብ መረጃን ለማድረስ የዜና ቡድኑ ምን ያህል ጠንካራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም።

ለሁለቱም ጥያቄዎች መልስ የሰጡት የጣቢያው ኃላፊዎች “የጤና ነገር ሰፊ ነው። ገና ያልተነካ በመሆኑ የሃሳብ መናጠብ አይገጥመንም” ሲሉ በእርግጠኝነት ተናግረዋል። በተለያዩ የጤና ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ የፕሮፌሽናል ባለሙያዎች ሰፊ ማብራሪያ በአስተማሪነትና በአዝናኝነት መንገድ ተዘጋጅቶ ስለሚቀርብ የሀሳብ እጥረት እንደማይፈጠር በቂ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

ጣቢያው ሲመሠረት ዋና ሃሳቡ የጤና ፕሮግራሞችን ማስተላለፍ ቢሆንም የዜና ሰዓት ጠብቆ ወቅታዊ መረጃዎችንም እንደሚያስተላልፍ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል። ለመገናኛ ብዙሃን በተበተነው ጋዜጣዊ መግለጫ ወረቀት እንደተመለከትነው “በህክምናው ዓለም የተገኙ አዳዲስ ግኝቶችን፣ ለጤና ጠቃሚ ምክሮችን፣ በሽታን የመከላከል ዘዴዎችንና አደጋን የመከላከል ዘዴዎችን፣ አዝናኝና ቀለል ባለ መልኩ ያቀርባል” ይላል። ከዚህ በተጨማሪም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መረጃዎች ባይኖሩበትም ሌሎች የመረጃ ዘገባዎች እና የስፖርት ዘገባዎችን ጣቢያው የሚያስተላልፍ መሆኑን ኃላፊዎቹ በአንደበታቸው ገልጸዋል።

ቴሌቭዥን ጣቢያው ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆንና “ረብ” ያለው ሥራ ይዞ ለመቅረብም ከተለያዩ የሙያ ማህበራት፣ ፖሊሲ አውጭዎች እና ሌሎች ማህበራት ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሱን ተናግረዋል።


አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥን ጣቢያ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የመጀመሪያው የጤና ጉዳዮች የሚተላለፍበት የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው። ይህ ጣቢያ በልዩነት ለመምጣት ለዓመታት ጥናት ላይ መቆየቱን ኃላፊዎቹ የተናገሩ ሲሆን፤ አምስት የዳይሬክተሮች ቦርድ የሚመራው ጣቢያ ነው። ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እና የፖለቲካ አስተሳሰብ ወገንተኝነት የፀዳሁ ነኝ ሲል የገለፀው አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኃላፊዎች እንደተናገሩት እና ድርጅቱ እንዳስቀመጠው ራዕይ የሚቀጥል ከሆነ በእውነትም ለአገሪቱ ህዝብ ጥሩ አማራጭ ሆኖ ይቀርባል ። ዋናው ነገር ጤና! ጤና ለሁሉም!!

READ  ምርጥ ደራሲያን ሊሸለሙ ነው

Continue Reading

Africa

ፕሬዝደንት አል ሲሲ፤ የግብፅ ውስጣዊ ፖለቲካ ውጥረትን ወደ ናይል ወንዝ መርጨታቸው አነጋጋሪ እየሆነ ነው

Published

on

ፕሬዝደንት አል ሲሲ፤ የግብፅ ውስጣዊ ፖለቲካ ውጥረትን ወደ ናይል ወንዝ መርጨታቸው አነጋጋሪ እየሆነ ነው

የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ የናይል ውሃን አጠቃቀም ጉዳይ የሕልውና ጉዳይችን ነው ሲሉ ኢትዮጵያን በተለያዩ መድረኮች በመጠቀም ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ የግብፅ ውስጣዊ የፖለቲካ ውጥረትን ወደ ናይል ወንዝ በመርጨት ለማቀዝቀዝ የመረጡበት መንገድ መሆኑን አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣን ለሰንደቅ ገልጸዋል፡፡

ሥማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ከፍተኛ የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣን በተለይ ለሰንደቅ እንደገለጽት፣ “የግብፅ ዋና ዓላማ የዓባይን ወንዝ ጉዳይ የገጠማትን ውስጣዊ የፖለቲካ ውጥረት ለማርገብ ለመጠቀም ነው፡፡ የቅኝ ግዛት ውል ቃልተቀበላችሁ የሚል ጥያቄ አቅርባለች፡፡ ኢትዮጵያ ለዘመናት የቅኝ ግዛትም ሆነ ሌሎች ያልተሳተፈችባቸውን ስምምነቶች እንደማትቀበል ግልፅ የሆነ አቋም እንዳለት ይታወቃል፡፡”

አያይዘውም፣ “የሕዳሴውን ግድብ በግልጽ እንዲጎበኙ የምናደርገው በተፋሰሱ ሀገሮች መካከል መተማመን እንዲፈጠር ቢሆንም ግብፆች ግን ይህንን እርማጃችን በአዎንታዊ ጎኑ ሊቀበሉት ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ በሱዳን ካርቱም የደረስነውን የመርሆች ስምምነትን በግልጽ እየጣሱ ነው፡፡ በስምምነቱ መሰረት ሶስቱ ሀገራት በምክንያታዊነት እና በፍትሃዊነት የናይል ውሃ ሌላው ላይ ጉልህ ጉዳት ሳያደርሱ እንደሚጠቀሙ እደሚደነግግ እየታወቀ፣ ግብፆች ግን በአደባባይ ስምምነቱን የጣሰ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ የሕዳሴው ግድብን ውሃ ሙሌትን በተመለከተም ምክንያታዊ እና ፍትሃዊ የመጠቀም መብቷን ተጠቅማ ትሞላለች፤ በዚህ የማንንም ፈቃድ አትጠይቅም” ብለዋል፡፡

በተያያዘም፣ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ባለፈው ሳምንት ባለመግባባት የተበተነውን የካይሮ ድርድር ተከትሎ ግብፅ ታሪካዊ የውሃ ድርሸዬ በማለት አጥብቃ የያዘችውን መከራከሪያ ሀሰብ በተመለከተ ሱዳን አዲስ ሚስጥር አውጥታለች፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም ጋንዶር ለሩስያ ቱደይ በሰጡት ማብራሪያ በ1959 የአባይ ውሃ የድርሻ ክፍፍል መሰረት ሱዳን የነበራትን ድርሻ ሙሉ በሙሉ ሳትጠቀም የቆየች መሆኗን በመግለፅ ይህንኑ የውሃ ድርሻ መጠንም እስከዛሬም ድረስ በብድር መልኩ ለግብፅ ስትለቅ የቆየች መሆኗን ገልጸዋል፡፡

READ  የሀገራችን ስልጣን የነብር ጅራት ነው

እንደውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለፃ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ውሃ መያዝ ከጀመረ ሱዳን በክረምትም ሆነ በበጋ የተመጣጠነ ውሃን ማግኘት ስለምትችል፣ ለግብፅ በብድር መልኩ ስትሰጥ የነበረውን ውሃ መጠቀም ትጀምራለች፡ይህም በመሆኑ፣ ግብፅና ሱዳን ከዚህ ቀደም በ1959 በነበራቸው ስምምነት መሰረት ሱዳን ከሚደርሳት የውሃ መጠን ድርሻ በብድር መልክ ለግብፅ የምትሰጠው ውሃ እንደሚያስቀር ታውቋል፡፡

በ1959 የተደረገው የቅኝ ግዛት ውል ኢትዮጵያን ባገለለው የሁለቱ ሀገራት የአባይ ውሃ ክፍፍል ድርሻ ስምምነት መሰረት የግብፅ ድርሻ 55 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ሲሆን የሱዳን ድርሻ ደግሞ 18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ በዓመት ነበር፡፡ ሆኖም ሱዳን ኮታውን በመጠቀሙ ረገድ ከነበረባት የአቅም ውስንነት ጋር በተያያዘ ግብፅ ተጨማሪ ውሃን ከሱዳን በብድር መልኩ በመውሰድ ትጠቀም እንደነበር ይሄው ዘገባ ያመለክታል፡፡
የሱዳን የውሃ ሃብት መስኖና ኤሌትሪክ ኃይል ሚኒስትር ሙታዝ ሙሳን ሱዳን ትሪብዩን ባሰራጨው መረጃ ከዚሁ ጋር በተያያዘ እ.ኤ.አ እስከ 1977 ድረስ ሱዳን ለግብፅ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃን በየዓመቱ ለመልቀቅ ተስማምታለች፡፡ ከዚህ ስምምነት በኋላም ሱዳን ለግብፅ ተጨማሪ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃን በዓመት ስትለቅ የቆየች መሆኗን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው የውስጥ ስምምነት በይፋ ግልፅ በማድረግ አወዛጋቢ ጉዳይን የፈጠረው የህዳሴው ግድብ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ ሊፈጥር የሚችለውን አካባቢያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖን የሚያጠኑት ቢአርኤል እና አርቲሊያ የተባሉት ኩባንያዎች ሪፖርታቸውን በካይሮ ለሶስቱ ሀገራት ተወካዮች ባቀረቡበት ወቅት መሆኑን ዘገባው ያመለክታል፡፡

በዚህም ሪፖርት ላይ ሱዳን ለግብፅ በብድር መልኩ ስታቀርበው የነበረው የውሃ ድርሻ ባለመቅረቡ፣ ሱዳን በጥናቱ ተአማኒነት ላይ ጥያቄ እንድታነሳ ያደረጋት መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል፡፡ ካይሮ የህዳሴው ግድብ ውሃ የመያዝ አቅምና የውሃ ሙሌት ሂደት የውሃ ድርሻዬን ይነካብኛል ከማለት ውጪ፣ ከሱዳን ስለምትበደረው የአባይ የውሃ መጠንና፣ የህዳሴው ግድብም ሱዳን ለግብፅ ስትሰጥ የነበረውን የውሃ ድርሻ መጠን ሊያስቀር ስለመቻሉ የገለፀችባቸው አጋጣሚዎች እስካሁን አልነበሩም፡፡

READ  ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ፍርደኞችን ያስለቀቁ የማረሚያ ቤት ሠራተኞች ጥፋተኛ ተባሉ

ካይሮ ከሰሞኑ በፕሬዝዳንት አልሲሲና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል የካይሮውን ድርድር ያለመግባባት መጠናቀቅን ተከትሎ የተለያዩ መግለጫዎችን በመስጠት ላይ ናት፡፡ እንደ አልሃራም ኦንላይን ዘገባ ከሆነ የካይሮው ስብሰባ ያለድርድር ከተበተነ በኋላ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በተለያዩ አለም አቀፋዊ ጉዳዮች በተወያዩበት ወቅት የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ የህዳሴው ግድብ ድርድር አስመልከተው ስምምነት ላይ አለመድረሳቸውንና ውጥረት ላይ መሆናቸውን አንስተው እንደተወያዩ የአልሃራም ኦንላይን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close