Connect with us

Ethiopia

ደብረሊባኖስ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ

Published

on

ደብረሊባኖስ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረሊባኖስ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

በዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል ኃላፊ ኮማንደር እንየው ፈረደ ለኢዜአ እንደገለፁት፥ አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 12 ሰዓት አካባቢ በወረዳው ደብረጽጌ ከተማ ልዩ ስሙ ቀሲም በተባለ ስፍራ ነው።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-10688 አማ የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ፥ በተቃራኒ አቅጣጫ ከጎሃ- ፂዮን ወደ አዲስ አበባ 14 ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ ከነበረ ኮድ 3-54551 ኦሮ ከሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ጋር መንገድ ስቶ በመጋጨቱ አደጋው ደርሷል።

በአደጋው ሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ ሾፌሩንና ረዳቱን ጨምሮ፥ የስምንት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በሰባት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

በአይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ ሹፌሩ ላይ የአካል ጉዳት ከመድረስ ውጭ ሌሎቹ ተርፈዋል፡፡

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአዲስ አበባና በአካባቢው በሚገኙ የጤና ተቋማት የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። እንደ ኮማንደሩ ገለፃ የሟቾቹ አስከሬን ቤተሰቦቻቸው እንዲረከቡ እየተደረገ ሲሆን፥ የአደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ ነው፡፡

 

READ  ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የዳያስፖራው የባንክና የኢንሹራንስ አክሲዮኖች ለሽያጭ እየቀረቡ ነው ተባለ
Continue Reading

Ethiopia

አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

Elias Tesfaye

Published

on

በረከት ስምኦን

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል።
አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ተነግሯል።

አቶ በረከት ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስገባታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ በቢሮአቸው ተገኝተው የነበሩት ሀሙስ ዕለት ነበር።

አቶ በረከት በተመሳሳይ ጊዜ ከሁለት የሃላፊነት ቦታቸው የተነሱ ሲሆን ለሥራ መልቀቃቸው ግልፅ ያለ ምክንያት አልቀረበም።

ነገር ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ብዙም ደስታኛ እንዳልነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።

በተለይ ማዕከሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚያቀርባቸው ሃገር አቀፍ የፖሊሲና የአስተዳደር ጥናቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩና በመንግሥት ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ብዙም ተቀባይነት አግኝተው ተግባራዊ አለመደረጋቸው ለቅሬታቸው ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። More Here

READ  ከሳዑዲ ለመውጣት የተመዘገቡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ማነስ አስደንጋጭ ሆኗል
Continue Reading

Ethiopia

ጠ/ ሚኒስትሩ ለኢቢሲ ሠራተኞች በልዩ ሁኔታ ቤት ለመስጠት ቃል ገቡ

Published

on

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

የኢትዮጵ ያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኢቢሲ) ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበት መንገድ በልዩ ሁኔታ እንደሚታይ፣ የባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት ድርጅቱ የውስጥ አሠራሩን እንዲያሻሽል ጠ/ ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ መምከራቸው ተሰማ።

ጠ/ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኢቢሲ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር ነው።
መንግሥታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በትላንት ዕትሙ የኢቢሲ ሠራተኞች ያለባቸውን የቤት ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት ሠራተኛው በልዩ ሁኔታ ቤት የሚያገኙበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉ ጠ/ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ጵፏል።
የመንግሥት ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለመቅረፍ ኢቢሲ አሠራሩንእንዲያሻሽልና ልማታዊ ጋዜጠኝነትን እንዲተገብር የመከሩት አቶ ሀይለማርያም ልማታዊ ጋዜጠኝነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁለተኛ ድግሪ የሚሰጥበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል። DIRETUBE

READ  የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና የ 28 ቀን ቀጠሮ ተሰጠባቸው
Continue Reading

Ethiopia

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

FanaBC

Published

on

By

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት እና በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዶክተር መረራ “ድርጊቱን አልፈፀምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” ብለው የዕምነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፥ ጠበቃቸው 11 ወር ቆይተው ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸው እንደዘገየ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

በከፊል የሚቀርቡ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞች እንዲጠይቋቸው ችሎቱን የጠየቁ ሲሆን፥ ችሎቱም ይህን ጥያቄያቸውን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ አዟል።

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር በይፋ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይም ዛሬ ብይን ሰጥቷል።

በህገመንግስቱ አንቀፅ 20 ንዑስ ከቁጥር 4 ጋር ይጋጫል ወይስ አይጋጭም በሚለው ላይ ህገመንግስታዊ ትርጉም ማስፈለጉ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከህገመንግስቱ አንፃር እንደማይጋጭ ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ ነው ችሎቱ የምስክሮች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ የአቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ ብይን የሰጠው።

እነዚህን መስክሮች ከጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ።

ፍርድ ቤቱ ከዶክተር መረራ ጋር የተከሰሱ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይም አዟል። ኤፍ ቢ ሲ 

READ  ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ብሔራዊ ባንክን እና የፋይናንስ ድርጅቶችን ከሰሱ
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close