Connect with us

Health

የቆዳዎን ጤንነት በመጠበቅና ውበትን በማጎናፀፍ ወደር የለሽ ምግቦች

Published

on

የቆዳዎን ጤንነት በመጠበቅና ውበትን በማጎናፀፍ ወደር የለሽ ምግቦች

የመዋቢያ ቁሳቁሶችን ለመሸመት ምን ያህል ገንዘብ ያፈሳሉ?

ምናልባትም ከፍተኛ ወጪዎትን የሚያውሉት የመዋቢያ ነገሮች በመሸመት ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም።

የቆዳዎን ጤንነት በመጠበቅና ውበትን በማጎናፀፍ ረገድስ ውጤታማነታቸውን እንዴት ይለኩታል?

እስኪ በመጠነኛ ወጪ ሊያገኟቸው የሚችሏቸውንና የተሻለ ጤንነትና ውበትን ለቆዳዎ በማጎናፀፍም ቢሆን አቻ የሌላቸውን ምግቦች እንጠቁምዎ።

1.ጥቁር ቸኮሌት
ብዙዎቻችን ቸኮሌት መመገብ እንደምንዎድ መቼስ አይጠረጠርም፤ ከቸኮሌት አይነቶች ታዲያ የጥቁር ቸኮሌትን ያህል ለጤና ጠቃሚ ነገር ማግኘት ግን አዳጋች ነው።

ጥቁር ቸኮሌት በተፈጥሮ በያዘው ፍላቫኖስ በተሰኘው አንቲኦክስዳንትስ እና በውስጡ በያዘው ፋቲ አሲድ አማካኝነት ቆዳዎ አንፀባራቂ እና ለስላሳ እንዲሆን ያስችላል።

የጥቁር ቸኮሌት ግብዓት በዋናነት ካካዋ እንደመሆኑ የደም ዝውውር ሂደትን ጤናኛ እንዲሆን ያስችላል።

በተጨማሪም ጥቁር ቸኮሌትን መመገብ ቆዳችን የፀሃይ ጨረርን እንዲቋቋም የማድረግ አቅም አለው።

2.ካሮት
ካሮት በዋናነት ለአይን ጤንነት ፍቱን መሆኑ ነው የሚታወቀው፥ ይሁንና ለቆዳችን ጤንነት ምን ያህል አበርክቶ እንዳለው ስንቶቻቸን እናውቅ ይሆን?

ካሮት በቫይታሚን ኤ የበለፀገ እንደመሆኑ በቆዳ ላይ ያሉ አላስፈላጊ ስንጥቆች እና የደረቁ የቆዳ ክፍሎች እንዲወገዱ ያደርጋል።

በተጨማሪም በላይኛው የቆዳችን ክፍል ላይ ያለው የሴል ምርትን በመቆጣጠር የቆዳን ገፅታ ማራኪ እንዲሆን ያስችላል።

3.ሳልመን
ሳልመን ተወዳጅ የአሳ ዝርያ ሲሆን፥ በበርካታ የጤና ጠቀሜታዎቹ የሚታወቅ ነው።

በአንፃራዊነት ከሌሎቹ የአሳ ዝርያዎች ሊወደድ እንደሚችል ቢታወቅም፥ ከጥቅሙ አንር ግን የዋጋው መወደድ ያን ያህል አሳሳቢ አይደለም።

ሳልመን መመገብ ጭንቀት፣ ውጥራተ እና የድካም ስመትን በማስወገድ ይታወቃል።

ሳልመን ባለው የቫይታሚን ዲ ይዘት ለአጥንት፣ ጥንካሬ፣ ለአዕምሮ ዕድገት ፣ ለልብ ጤንነት ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ጎን ለጎን ብሩህ እና ጤነኛ ቆዳ እንዲኖረን ያግዛል።

READ  የጀርባ ህመምን በቀላሉ ለማከም የሚረዱን ዘዴዎች

4.ኮኮናት ዘይት
የኮኮናት ዘይት ከፍተኛ ካሎሪ ያለው ሲሆን፥ በውስጡ ያለውም ፋተ ቢሆን እጅግ ጠቃሚ ነው።

በተጨማሪም በሉሪክ አሲድ የበለፀገ በመሆኑ በቆዳችን ላይ ያሉ ባክቴሪያዎችን ይገድላል።

እኛ ኮኮናት ዘይትን እናዘውትር እንጂ በቆዳችን ላይ የማቃጠል ስሜትን በማስታገስ፣ ኢንፌክሽንን በመከላከል ተጨማሪ ጠቀሜታዎችንም ይቸረናል።

5. ስፒናች
ስፒናች በማግኒዚየም፣ ክሎሮፊል፣ ቨይታሚን ሲ፣ ፈይበር፣ ቫይታሚን ኤ፣ ኢ እና በረት እጅግ የበለፀገ እና ለቆዳቸን ውጤታማ የሆኑ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።

ስለሆነም ስፕናችን አዘውትሮ መመገብ አስገራሚ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል።

6.ፓፓዬ
በዜሮ የኮሌስትሮል መጠኑ የሚታወቀው ፓፓዬ አንዳንዴ ተዓረኛው ፍሬ በመባለ ይታወቃል።

በተለያዩ ቫይታሚን እና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የበለፀገው ፓፓዬ ለማራኪ ቆዳ ተመራጭ ነው።

ፓፓዬ ጫፋጭ እና አንስተኛ የካሎሪ መጠን መያዙ ደግሞ ቆንጆ የሰውነት ቅርፅ (ተክለ ሰውነት) እንዲኖረን ያግዛል። wmnlife

Continue Reading

Ethiopia

የኢንዱስትሪ መንደሮችና የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ስጋት

Published

on

የኢንዱስትሪ መንደሮችና የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ስጋት

ኢትዮጵያ የዓለምን ባለሀብቶች ቀልብ ስባለች ለሚለው ገለጻ እንደማስረጃ የሚቀርቡ የኢንዱስትሪ መንደሮች ለብዙ አስር ሺዎች የስራ እድል የፈጠሩ የእንጀራ ገበታዎች ናቸው፡፡

ስጋታችን ለስንት ሰው ሞት ምክንያት ይሆኑስ የሚለው ነው፡፡ አሁንም በወረርሺኝ ደረጃ የሚገኘው የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት እንደልቡ ከሚሆንባቸው ስፍራዎች አንዱና ዋናው ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ሰፈር ነው፡፡

የሃይል ማመንጫዎቻችን የስንት ወጣት እህቶቻችንን ህይወት እንዳጨለሙ ለሚያስብ ሰው መንግስት ከግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ጋር አብሮ ኤች አይ ቪ ኤድስን ማጤን አለበት ያስብላል፡፡

ኢንዱስትሪ መንደር የተገነባባቸው ከተሞች ብዙ ሺ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥረዋል የሚለው የምስራች ብዙ ሺ ዜጎች ስራውን ፍለጋ ወደ ኢንዱስትሪ መንደሮቹ መገኛ ከተሞች መጥተዋል የሚለውን አብሮ የያዘ ነው፡፡

ከዚያ ከነባሩ ነዋሪ በተጨማሪ የስራ እድሉን ፍለጋ የመጣው ቁጥር ኢንዱስትሪዎቹ ዙሪያ ትንንሽ ሰርቪስ ቤቶችን እየተከራየ ኑሮውን ይጀምራል፡፡ ይህንን ኑሮ ከነባሩ ኑሮ ጋር ማስታረቅ፣ ነባሩን ነዋሪ ከአዲሱ ጋር የተስማማ እንዲሆን ማድረግ ዋናው ስራ ቢሆንም ተዘንግቷል፡፡

አዳዲስ ጫት ቤቶች፣ አዳዲስ ሺሻ ቤቶች፣ ከትዳር አጋራቸው አሊያም ከፍቅር ጓደኛቸው ርቀው የመጡ ወጣቶች በአዲሱ አካባቢ ከነባሩ ማህበረሰብ ጋር ሲዋህዱ ሊከሰት የሚችለውን ነገር አንተነብየውም፡፡

እየሆነ ካለው ነገር በመነሳት ብዙ ማለት ይቻላልና፡፡ ወጣቶች ለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚጋለጡበት እድል የሚፈጠረው ይሄንን ተከትሎ ነው፡፡ ይሄ የመጋለጥ እድል ደግሞ ጠባብ ሳይሆን የተንቦረቀቀ ነው፡፡

ኢንዱስትሪዎቹ ስለ ማሽኖቹ የሚጨነቁትን ያህል ስለ ተተከሉበት ዙሪያ ማህበረሰብ ግድ ሊላቸው ይገባል፡፡ ሰራተኞች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የሚሰጣቸው ስልጠና እና የሚደረገው ክትትል ከሚቆርጥና ከሚፈልጥ አደጋ ብቻ መሆን የለበትም፡፡

READ  “የኛ” በወጣት ሴቶች ዙሪያ በኢትዮጵያ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚሠራውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል

ኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በርካታ ሰዎች በጋራ የሚኖሩባቸው የልማት አካባቢዎች ኤች አይ ቪ ኤድስ ያደረሰብን ጉዳት የሚረሳ አይደለም፡፡ ብዙ አምራች ሃይል አጥተናል፡፡ ብዙ ቤተሰብ ተበትኗል፡፡

ዛሬም ለግዙፍ የልማት አካባቢዎች የተለየ ትኩረት ሰጥተን ካልሰራን ተመሳሳይ ጉዳይ ይገጥመናል፡፡ ታሪክ ራሱን ይደግማል፡፡ መራር ታሪክ፤ በኢንዱስትሪ መንደሮች ዙሪያ ለሚኖረው ማህበረሰብ እና ወጣት ትውልድ የኢንዱስትሪ ማዕከሉ መጠንቀቅ ይኖርበታል፡፡

ሰራተኞች ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ መስራት አለበት፡፡ እንደ ኢንቨስተመንቱ ሁሉ ገንዘብ መድቦ ከወረርሺኝነት ያላወጣነውን ኤች አይ ቪ ኤድስ ዳግም የሀገራችን ልማት አደጋ እንዳይሆን ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ህጎች እና ይሄንን አሰራር የሚያስገድዱ መመሪያዎች ያስፈልጋሉ፡፡

ማህበራዊ ዋስትና በሚያረጋግጥ ስልት የሚመሩ የኢንቨስትመንት ማዕከሎች እንዲሆኑ ኤች አይ ቪ ኤድስን ግምት ውስጥ የከተቱ ስራዎች መሰራት አለባቸው፡፡ አሁን ግን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሌላ ነው፡፡ እንወያይበት፡፡

DIRETUBE

 

Continue Reading

Health

የደም ግፊት፣ በደም ውስጥ ያለን ስብ ለመቀነስ፣ ኢንፌክሽንና ጉንፋንን ልንከላከል የምንችልባቸው መንገዶች

Published

on

የደም ግፊት፣ በደም ውስጥ ያለን ስብ ለመቀነስ፣ ኢንፌክሽንና ጉንፋንን ልንከላከል የምንችልባቸው መንገዶች

ነጭ ሽንኩርት፣ ሎሚ እና ዝንጅብል በዉሃ ውስጥ አንድ ላይ ደባልቆ መጠቀም የደም ግፊት፣ በደም ውስጥ ያለ ስብን ለመቀነስ እንዲሁም ኢንፌክሽንና ጉንፋንን ለመከላከል እንደሚረዳ ከወደ ጀርመን ሀገር የወጣ መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምም ከፍ እንዲል እንደሚረዳም ተጠቁሟል።

ውህዱን ለማዘጋጀት የሚስፈልጉን ነገሮች፦

አራት ራስ ነጭ ሽንኩርት፣ አራት ያልተላጠ ሎሚ፣ አነስ ያለ ዝንጅብል እንዲሁም ሁለት ሊትር ዉሃ።

አዘገጃጀት፦

ሎሚውን አጥበን መቆራረጥ፣ ነጭ ሽንኩርቱንና ዝንጅብሉን ልጠን አንድ ላይ መደባለቅ።

በመቀጠል ከብረት የተሰራ ጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ በመጨመር እና ሰሃኑ ውስጥ ሁለት ሊትር ውሃ በመጨመር አንድ ላይ ማፍላት።

የፈላው ውሃ ለብ እስኪል በመጠበቅ በውሃ መጠጫ ብርጭቆ አድርጎ መጠጣት።

የነጭ ሽንኩርት፣ ሎሚ እና ዝንጅብል ውህዱን በየቀኑ ጠዋት ምግብ ከመመገባችን ከሁለት ሰዓት በፊት በባዶ ሆድ መጠጣት ይመከራል።

ከመጠጣታችን በፊት ውህዶቹ ከስር ዘቅጠው እንዳይቀሩ ለመደባለቅ መወዝወዝ ይኖርብናል።

healthyfoodteam

READ  ስልክ በመነካካት የሚያሳልፉ እናቶች ልጆቻቸውን እንደማይንከባከቡ አንድ ጥናት አመለከተ
Continue Reading

Health

ማር እና ሎሚን በመጠቀም የምናገኛቸው የጤና ጠቀሜታዎች

Published

on

ማር እና ሎሚን በመጠቀም የምናገኛቸው የጤና ጠቀሜታዎች

ማር እና ሎሚ በተፈጥሮ በተፈጥሮ የያዙት አንቲ ኦክሲደንት የሰውነታችንን በሽታ የመካለከል አቅም እንዲጨምር የማድረግ ሃይል እንዳላቸው በተለያዩ ጊዜያቶች የተካሄዱ ጥናቶች ያመለክታሉ።

በተጨማሪም ማር እና ሎሚ ውፍረትን ለመቀነስ እንዲሁም ለውበት መጠበቂያነት እንደሚያገለግሉም ተጠቅሷል።

ለብ ባለ አንድ ብርጭቆ ዉሃ ውስጥ ሎሚ እና ማር ጨምሮ ሁሌም ጠዋት መጠጣት ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት።

ቦርጭን ለማጥፋት እና ሰዉነታችንን ክብደት ለመቆጣጠር ይረዳናል፦ ለብ ባለ 1 ብርጭቆ ውሃ ውስጥ ግማሽ ሎሚ እና አንድ የሻይ ማንኪያ ማር በማድረግ መጠጣት።

ይህም ሎሚ በውስጡ ባለው አንቲኢክሲደንት አማካኝነት የስብ ሴሎች እንዲጠፉ ያደርጋል እንዲሁም ማር በተፈጥሮ ሃይል ሰጪ በመሆኑ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ስለሚረዳን ማር እና ሎሚን መጠቀም ይመከራል።

የተስተካከለ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲኖረን ያድርጋል፦ ለብ ባለ 1 ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር እና ሁለት የሻይ ማንኪያ ሎሚ ጨምሮ ጠዋት ጠዋት መጠጣት የመተንፈሻ አካላችን እንዲፀዳ በማድረግ የተስተካከለ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲኖረን ያግዛል።

የጠራ ቆዳ እንዲኖረን ይረዳናል፦ እኩል መጠን ሎሚ እና ማር በመደባለቅ ቆዳችን ላይ ጠቆር ያለ ምልክት ባለበት ቦታ ላይ ከቀባን በኃላ ከ20 እስከ 30 ደቂቃ አቆይተን በቀዝቃዛ ውሃ በመታጠብ የጠራ ቆዳ እንዲኖረን ማድረግ እንችላለን።

በተጨማሪም ማር እና ሎሚን መጠቀም ቆዳችንን ከድርቀት እና ከኢንፌክሽን ይከላከላል።

ጉንፋን ሲይዘን ፍቱን መድሃኒት ነው፦ ማር እና ሎሚ በውስጣቸው ቪታሚን ሲ ስላላቸው ጉንፋን አምጪ ባክቴሪያዎችን የመከላከል አቅም አላቸው።

ግማሽ ሊትር ውሃ፣ ሶስት የሻይ ማንኪያ ማር እና ሶስት የሻይ ማንኪያ ሎሚ እንዲሁም ዝንጅብል በመጨመር አንድ ላይ በማፍላት መጠጣት ጉንፋንን ለመከላከል ይመከራል።

READ  ህብረተሰቡ "ኤክስል ኦሬንጅ'' የተባለ ጭማቂ ገበያ ላይ ሲያገኝ ጥቆማ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ብጉርን ያጠፋል፦ ሎሚ እና ማር አንድ ላይ ደባልቆ መቀባት ቆዳችን ላይ ያለ ብጉር ደርቆ እንዲረግፍ በማደርግ ከብጉር የፀዳ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል። healthdigezt

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close