Connect with us

Law or Order

የሰሜን ኮሪያ የመረጃ ጠላፊዎች የደቡብ ኮሪያን ወታደራዊ ሰነድ መመንተፋቸውን ገለጹ

Published

on

የሰሜን ኮሪያ የመረጃ ጠላፊዎች የደቡብ ኮሪያን ወታደራዊ ሰነድ መመንተፋቸውን ገለጹ

በሰሜን ኮሪያ ያሉ የመረጃ ጠላፊዎች በጣም ግዙፍ መጠን ያለው ወታደራዊ ሰነድ ከደቡብ ኮሪያ መጥለፋቸውን ገልጠዋል፡፡

ከተጠለፈው መረጃ መካከልም የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን የግድያ እቅድ እንደሚገኝበት ተነግሯል፡፡

235 ጊጋ ባይት (gigabytes) መጠን ያለውን ሰነድ ከተቀናጀ የወታደራዊ የመረጃ ማእከል መጥለፋቸውን እና 80 በመቶ የሚሆነው ሰነድ ገና እየተጣራ መሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ከሰነዶቹ መካከልም በአሜሪካ እና በደቡብ ኮሪያ የተዘጋጁ የጦር መርሃ-ግብሮች የሚገኙበት ሲሆን ደቡብ ኮሪያ ከዚህ ቀደም በሰሜን ኮሪያ የሳይበር ጥቃት እንደተፈጸመባት መግለጡዋ የሚታወስ ነው፡፡

North Korea ‘hackers steal US-South Korea war plans’

Hackers from North Korea are reported to have stolen a large cache of military documents from South Korea, including a plan to assassinate North Korea’s leader Kim Jong-un.

Rhee Cheol-hee, a South Korean lawmaker, said the information was from his country’s defence ministry.

The compromised documents include wartime contingency plans drawn up by the US and South Korea.

They also include reports to the allies’ senior commanders.

The South Korean defence ministry has so far refused to comment about the allegation.

Plans for the South’s special forces were reportedly accessed, along with information on significant power plants and military facilities in the South.

Mr Rhee belongs to South Korea’s ruling party, and sits on its parliament’s defence committee. He said some 235 gigabytes of military documents had been stolen from the Defence Integrated Data Centre, and that 80% of them have yet to be identified. bbc

READ  ኢትዮጵያ በሩዋንዳ ኤምባሲ ከፈተች

Continue Reading

Law or Order

አሳሳቢው የቻይናና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ

Published

on

አሳሳቢው የቻይናና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ

የረጅም ጊዜ የ ዘ ኢኮኖሚስት መጽሔት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ቢል ኢሞት በቅርቡ ቻይና ሰሜን ኮሪያን ለዋሽንግተን እና ለተቀረው ዓለም የኒኩሌር ጦር መሳሪያ በነፃ በመስጠት መቆጣጠር ልትጀምር እንደምትችል የሚገልጽ ትንታኔ አቅርበዋል፡፡

ተንታኙ እንደጠቆሙት፣ የቻይና እንቅስቃሴ የኮሪያ ባህረ ሰላጤን ለመያዝ ብቻ ሳይሆን በቀጣናው ጂኦፖለቲካል አቋሟን ለማጠናከር፣ ዓለም አቀፋዊ ኃያልነቷን ከፍ ለማድረግ እንዲሁም በተወሰነም ቢሆን የሰላም አክባሪነት ሚናን ለመጎናጸፍም ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡

ይህም ለሰሜን ኮሪያም ቢሆን ቢያንስ መጥፎ ወታደራዊ አማራጭ ሲሆን፤ የአሜሪካ አጋሮች ደቡብ ኮሪያና ጃፓንን ጨምሮ በኤሺያ ላይ የይገባኛል ሀሳባቸውን የሚያስቀር፣ እንዲሁም ከሰሜን ኮሪያ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የደቡብ ኮሪያ ግዛትን ሊያጠፋ የሚችል በከፍተኛ ኃይል እንደሚያስከትል ኢሞት ተናግረዋል፡፡

ቻይና ሰሜን ኮሪያን ከተቆጣጠረች በታሪክ የድህረ ኮሪያ ጦርነት ተብሎ በሚታወቀው ሁኔታ ውስጥ በመክተት ሰሜን ኮሪያ በቻይና የኑክሌር ከለላ ውስጥ በመሆን አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና ልታገኝ እንደምትችልም ትንታኔው ይጠቁማል፡፡

በተጨማሪም ለሰሜን ኮሪያውያን ከዚህ ዕቅድ ጋር አብሮ መሄድ ማበረታቻ ሲኖረው፤ ከአሜሪካ ጋር የኑክሌዮር ልውውጥ ማድረግ ማለት ግን ውድመት በመሆኑ ለቻይና መሰጠት የመኖር ተስፋ የሚያለመልም እንዲሁም በሉአላዊነት የመቀጠል አጋጣሚም ሊኖር እንደሚችል ኢሞት ይመክራሉ፡፡
የፖለቲካ ተንታኙ ኢሞት ለፕሬዚደንት ኪም ቀረቤታ ካላቸው በስተቀር፤ ይህ የቻይና ስትራተጂ አብዛኛውን የሰሜን ኮሪያ ጦር ድል የሚያስገኝ ነው ብለዋል፡፡

ቻይና በትልቁ አሸናፊ ናት

ሰሜን ኮሪያን በመቆጣጠር ትልቁ አሸናፊ ቻይና ልትሆን እንደምትችል በመጠቆም ቻይና በኮሪያ ባህረ ሰላጤ የሚደረገውን በተለይ ወታደራዊ ቤዝ የመመስረት አጋጣሚ መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን አውዳሚ ጦርነትን በመቆጣጠርም የቀጠናው ምስጋና የሚያስገኛትም ጭምር መሆኑ ኢሞት አክለዋል፡፡

READ  ከ663 ሚሊየን የሚበልጥ ሕዝብ ዛሬም ንጹሕ የመጠጥ ዉኃ ሰለጠንኩ በምትለዉ ዓለማችን እያገኘ አይደለም

በተጨማሪ ቻይና ስኬታማ ወታደራዊ ስራ በቀጠናውና በዓለም አቀፍ በቀጣይ ኩነቶችን ጫና ሊያሳድር የሚችል አቅም ትፈጥራለች፡፡ በአሜሪካ ፍላጎት ሰሜን ኮሪያ ኑክሌር እንዳይኖራት ለማድረግ ቻይናን በግዛቱ ማሰማራት ሲሆን የአሜሪካ የጂኦፖለቲክስ የበላይነት መሆን መልካም እድሎችን የሚያስገኝ ትልቁ ስትራተጂና ከአሜሪካ ጋር የሃይል እኩልነትን በኤሺያ ፓስፊክ ሲያስከትል ከቀጠናው ማስወጣት ግን ለአሜሪካም ይሁን ቻይና የሚጎዳ የአለመረጋጋት ምንጭ ይሆናል፡፡

እንደ ኢሞት ንግግር ማንኛውም የሽምግልና ጣልቃገብነት ቻይናውያን አልያም ከባድ አደጋዎች የሚያስከትል ይሆናል፡፡ ቻይና እንዴት አድርጋ ሰሜን ኮሪያን የኑክሌር ተግባር ልትቆጣጠር እንደምትችልም የሚጠይቁ አንድ አንድ ምሁራንም አልጠፉም፡፡

ተግዳሮቶች
የኑክሌር መርሃ-ግብርን በመገደብ ረገድ የሚከፈል አንድ ዓይነት አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና ጠቅላላ ጥፋት አያመጣም ይላል ትንታኔው፡፡ ከደህንነት ዋስትና በበለጠ የቻይና ጎሮቤት /ሰሜን ኮሪያ/ በተለይ በድንበሯ አከባቢ ከሚገኙ አጎራባች አገሮች ነጻ በመሆን ለሉኣላዊነቷ እንደሚበጃት የሚናገሩም አሉ፡፡ ከዚህም በመነሳት ሰሜን ኮሪያ በቻይና ቁጥጥር ስር መግባት አለባት የሚለው ሃሳብ ይቃወማሉ፡፡
ስለ ሰሜን ኮሪያ የፈለከውን ማናገር እንደሚቻል፣ ለዓለም የአቀራረብ መንፈሷ ከልብ ነው፣ አክራሪ ብሔርተኝነትና እና ለስርአቱ የበላይነትም ዘርን መሰረት ያደረገ

እምነት ያላት አገር መሆኗ የቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣን ሪቬሪ ይመሰክራሉ፡፡ የሰሜን ኮሪያና ቻይና ግንኙነት የከንፈርና ጥርስ ወዳጅነት እንዳልነበራቸው በሰሜን ኮሪያ የጸረ ቻይና ስሜት በጣም እየጠለቀ መምጣቱ ባለስልጣኑ ይገልጻሉ፡፡

የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ የብሔራዊ ስሜት በማህበረሰቡም ይሁን በሁሉም ደረጃዎች ላይ ያለው የፖለቲካ ባህል በጣም ጠንካራ ነው፡፡ ስለዚህ ቻይና ይሁን ሌላ አገር በሰሜን ኮሪያ የበላይነት ይኖራታል ብሎ መገመት እጅግ በጣም ከባድ መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡

READ  ኢትዮጵያ በሩዋንዳ ኤምባሲ ከፈተች

ሰሜን ኮሪያን የመተናኮስ ተግባር በተለይ ከቻይናና ሩሲያ የመሳሰሉ ጎሮቤት አገሮች አዲስ ክስተት አለመሆኑንና የሰሜን ኮሪያ መስራች የፕሬዚደንት ኪም አያት ጠንካራነትን ሪቬሪ መስክረዋል፡፡ ኪም II ሰንግ ከሶቪየትና ቻይና እአአ በ1950ዎቹ አጋማሽ ኮሪያውያን የነበራቸውን ድጋፍ ማስወገዳቸው፣ ከሶቪየት ሕብረት የሚያመጡት እቃዎችን መለየታቸው እንዲሁም በኮሪያ ጦርነት ወቅት በሰሜን ኮሪያና ቻይና ወሳኝ ክርክር፣ ተቃውሞና ፖለቲካዊ ፍልሚያ ማድረጋቸው አብራርቷል፡፡

የሰሜን ኮሪያ ያልታሰበ እቅድ
የአሜሪካ የቀድሞ የባህር ኃይል ኢንተሊጀንስ ባለሙያና የቻይና አማካሪ ጂኦፍ ዊልሰን በመሬት ላይ የአስፈሪዋ ሀገር መሪ ፕሬዚደንት ኪም ከቻይናው ጥቃት ጋር በተያያዘ ለመምከር የሚያስችለው ያልታየ ወታደራዊ እቅድ እንደሌላቸው ይመሰክራሉ፡፡

በተጨማሪ ቻይናውያን የኮሪያን ጦር የቻይና ህዝቦች ነጻነት ጦር ባህረ ሰላጤውን እስከ ሚቆጣጠረው የሚያዘገይ የሰሜን ኮሪያ ሰላይ በእጃው ውስጥ ካላስገቡ በስተቀር ቻይና ሰሜን ኮሪያን ያለ መጠነ ሰፊ ሞትና መቁሰል ልትቆጣጠራት እንደማትችል ዊልሰን አሳስበዋል፡፡

ለጊዜውም ቢሆን የፕሬዚደንቱ አጎት እአአ በ2013 እንዲሁም የአባቱ ልጅ ወንድሙ ግድያዎች የሰሜን ኮሪያ መንግስት በማንኛውም ኃይል ላይ ፍጹም ጠባብነትን የሚገልጽ ነው፡፡ ሁለቱም ሟቾች ከቻይና የቤጂንግ አስተዳደር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸውም ይታወቃል፡፡

ጤነኛ ያልሆነ ሊበራሊዝምን የመስፋፋት ውጥረት
‘የምዕራቡ ዕጣ ፋንታ፤ ጠንካራና ውጤታማ የዓለምን ፖለቲካዊ ሃሳብ የማስቀጠል ውጊያ’ የሚል በኢሞት የተጻፈና በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ አካባቢ የታተመው የጸረ ሊበራሊዝም ርእዮተ ዓለም የመበራከት አሳሳቢነት ቁጥራቸው እየጨመረ ካሉ መጽሐፍቶች አንዱ ነው፡፡
የቻይና የረጅም ጊዜ ጉዞ በግልጽ እንደሚያሳየው ሀገሪቱ ለዘመናት ያክል በኮሚዩኒስት ስርዓት የምትመራ ነች ይህም ለዴሞክራሲያውያኖች እንዲሁም በቻይና ውስጥ ይሁን ውጭ ሀገሪቱን ለመቀየር በሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ላይ አሳሳቢነቱ ከፍተኛ ሆኗል፡፡

READ  የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባለስልጣን የጋናውን ተጫዋች አደነቁ

ወሳኝ ምክረ ሀሳብ
ባለፈው ሳምንት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሽንግተን ዋይት ሃውስ ከከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችና የቀድሞ ሚስታቸው መገናኘታቸውን ጠቅሶ፤ “ከማዕበሉ በፊት መረጋጋት“ በማለታቸው ጋዜጠኞች የማዕበሉ ጉዳይ እንዲያብራ ሩላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ነገር ግን ፕሬዚደንቱ በቀላሉ “ይገባችኋል“ ብለዋል፡፡ በተደጋጋሚ የማዕበሉ ጉዳይ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ ለማብራራት ቢጠየቁም “ይገባችኋል“ ከማለት ውጭ የሰጡት ማብራሪያ የለም፡፡

ቪኦኤ ማዕበሉን የሚያመራው ወዴት እንደሆነ ለጠየቃቸው አንድ አንድ አሜሪካኖች በተለይ ስማቸው ለመጥቀስ ያልፈለጉ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚ ገልጹት፤ ትራምፕ ኢላማቸው ሰሜን ኮሪያ መሆኑ ነው፡፡ የትራምፕ የቀድሞ አማካሪ ስቴቨን ባኖን የዋይት ሃውስ ስልጣናቸው ከመልቀቃቸው በፊት ደቡብ ኮሪያ ለሰሜን ኮሪያ ቅርብ እንደመሆኗ መጠን የአሜሪካ ወታደር በስፍራው መኖር እንደሌለበት ተናግረው ነበር፡፡

ባኖን በሴኦል 10 ሚሊዮን ሰዎች በ30 ደቂቃ ውስጥ በአውዳሚ የጦር መሳሪያ የማይሞቱበት ስሌት ሰርቶ በግልጽ የሚያስረዳ እስከሚገኝ ድረስ ወታደራዊ መፍትሔ እንደማያስፈልግ እንዲሁም ሰሜን ኮሪያውያንም በደምብ አሜሪካኖችን መገንዘባቸው ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜም ቢሆን የአሜሪካ ባለስልጣኖች በሰሜን ኮሪያ ላይ ከወታደራዊ አመራርነት አማራጭ ውጭ አለመሆናቸውን በመጥቀስ አሜሪካ በተጨማሪ ሰላማዊ መፍትሔም እየተመለከተች መሆኑ ትንታኔው ያስረዳል፡፡ ዘገባው ያጠናከረው ቪኦኤ ድረ-ገጽ ነው፡፡

በሌላ በኩል ቢቢሲ በድረ-ገጹ እንዳስነበበው የሰሜን ኮሪያ መረጃ መንታፊዎች /ሃከሮች/ በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ ቤዝ የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚደንት ኪም የመግደል እቅድ ጭምር ያካተተ ትልቅ ዋጋ ያለው መረጃ መዝረፋቸው ሪፖርት አድርጓል፡፡ መረጃው የተዘረፈው ከደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር መሆኑም ደቡብ ኮሪያዊ የህግ ባለሙያ ርሄ ቸኦል ሂ ተናግረዋል፡፡ ethpress

Continue Reading

Ethiopia

ጠ/ ሚኒስትሩ ለኢቢሲ ሠራተኞች በልዩ ሁኔታ ቤት ለመስጠት ቃል ገቡ

Published

on

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

የኢትዮጵ ያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኢቢሲ) ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበት መንገድ በልዩ ሁኔታ እንደሚታይ፣ የባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት ድርጅቱ የውስጥ አሠራሩን እንዲያሻሽል ጠ/ ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ መምከራቸው ተሰማ።

ጠ/ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኢቢሲ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር ነው።
መንግሥታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በትላንት ዕትሙ የኢቢሲ ሠራተኞች ያለባቸውን የቤት ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት ሠራተኛው በልዩ ሁኔታ ቤት የሚያገኙበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉ ጠ/ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ጵፏል።
የመንግሥት ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለመቅረፍ ኢቢሲ አሠራሩንእንዲያሻሽልና ልማታዊ ጋዜጠኝነትን እንዲተገብር የመከሩት አቶ ሀይለማርያም ልማታዊ ጋዜጠኝነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁለተኛ ድግሪ የሚሰጥበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል። DIRETUBE

READ  የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባለስልጣን የጋናውን ተጫዋች አደነቁ
Continue Reading

Ethiopia

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

FanaBC

Published

on

By

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት እና በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዶክተር መረራ “ድርጊቱን አልፈፀምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” ብለው የዕምነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፥ ጠበቃቸው 11 ወር ቆይተው ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸው እንደዘገየ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

በከፊል የሚቀርቡ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞች እንዲጠይቋቸው ችሎቱን የጠየቁ ሲሆን፥ ችሎቱም ይህን ጥያቄያቸውን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ አዟል።

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር በይፋ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይም ዛሬ ብይን ሰጥቷል።

በህገመንግስቱ አንቀፅ 20 ንዑስ ከቁጥር 4 ጋር ይጋጫል ወይስ አይጋጭም በሚለው ላይ ህገመንግስታዊ ትርጉም ማስፈለጉ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከህገመንግስቱ አንፃር እንደማይጋጭ ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ ነው ችሎቱ የምስክሮች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ የአቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ ብይን የሰጠው።

እነዚህን መስክሮች ከጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ።

ፍርድ ቤቱ ከዶክተር መረራ ጋር የተከሰሱ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይም አዟል። ኤፍ ቢ ሲ 

READ  የደቡብ ኮሪያ ስሪት ኪያ ሞተር ብራንድ መኪኖች በአገራችን በበላይ አብ ሞተርስ ተገጣጠሙ
Continue Reading

Trending