Connect with us

Business

ኬንያ ገበያ ይቀርባል ተብሎ የነበረው 44 ሺ ኩንታል ስኳር እየተመለሰ ነው

Published

on

44 ሺ ኩንታል ስኳር

(ንጋቱ ሙሉ) ለጐረቤት ኬንያ ገበያ ይቀርባል ተብሎ ሞያሌ ድንበርን ማለፍ ያልቻለው 44 ሺ ኩንታል ስኳር በአዳማ እየተፈተሸ ወደተመረተበት ወንጂ ስኳር ፋብሪካ አየተመለሰ ነው ተባለ፡፡

ስኳሩ እስካሁን የጥራት ችግር ስላልተገኘበት ለኢትዮጵያ ገበያ ሊቀርብ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራልም ተብሏል፡፡ ይህን ያለው ስኳር ኮርፖሬሽን ነው፡፡
ከወንጂ ስኳር ፋስሪካ 44 ሺ ኩንታል የጫኑ 110 ተሽከርካሪዎች መዳረሻቸውን ኬንያ ለማድረግ ከ2 ወራት በፊት ግድም ሞያሌ ቢደርሱም ኬንያ መግባት አቅቷቸው ወደመጡበት እየተመለሱ ነው፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አይችሉህም ትናንት ለሸገር እንደተናገሩት ተሽከርካሪዎቹ እስከ ነገ ድረስ አዳማ ደርሰው ፍተሻ ከተደረገ በኋላ ወደ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ይሄዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነግረውናል፡፡

አቶ ጋሻው እንደነገሩን ስኳሩን ከስኳር ኮርፖሬሽን ከገዛው መቀመጫውን ዱባይ ካደረገው አግሪ ኮሞዲቲስ ኤንድ ፋይናንስ ጋር ያለው ውል ተቋርጧል፡፡
ስለዚህም የተመለሰው ስኳር ለኢትዮጵያ ተጠቃሚዎች የሚቀርብበት ሁኔታ ይኖራል ብለዋል፡፡ ስኳሩ በሞያሌ ለወራት በመቆየቱ ቀልጧል እየተባለ ይነገራል ያልናቸው ዳይሬክተሩ እስካሁን መቅለጡን አላየንም ብለዋል፡፡

ስኳሩ በኬንያ ለመድረስ ያልቻለው በስኳር ገዢውና ስኳሩን እንዲያጓጉዝ በተዋዋለው የትራንስፖርት ድርጅት መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ጋሻው ችግሩ እንዲፈታ የተደረገው ጥረትም አልተሳካም ብለዋል፡፡

ስኳሩን ከስኳር ኮርፖሬሽን የገዛው አግሪ ኮሞዲቲስ ኤንድ ፋይናንስ ለስኳሩ ግዢ መክፈል የነበረበትን 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ያልከፈለ ሲሆን ስኳር ኮርፖሬሽን ውሉን ማቋረጡን እንዳስታወቀውና በሂደት ኪሣራና ወጪውን በህግ እንደሚጠይቀው አቶ ጋሻው ተናግረዋል፡፡

ሰሞኑን በገበያ ላይ ያጋጠመውን የስኳር እጥረት ለመቅረፍ ከአልጄሪያና ከታይላንድ የተገዛ 700 ሺ ኩንታል ስኳር በጉዞ ላይ መሆኑ ይታወሣል፡፡

READ  Air Travel: East Africa Rising

Sheger FM

Continue Reading

Business

አምባሳደር ግርማ ተመስገን የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ

Published

on

አምባሳደር ግርማ ተመስገን የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ

በኮትዲዩቫር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ግርማ ተመስገን ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት አላሳን ዋታራ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል፡፡
ክቡር አምባሳደር በስነስርዓቱ ወቅት፣ ሁለቱ አገሮች ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በስደት ጉዳዮች ላይ እና በጸረ ሽብር መዋጋት ትብብርን ጨምሮ በወሳኝ አህጉራዊና አለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ያላቸው መሆኑን አምባሳደር ግርማ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት ስድስት ጊዜ ወደ አቢጃን በረራ ያደርጋል፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም የቱሪዝም እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳደግ ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ አብራርተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታራ በበኩላቸው፣ ሁለቱ አገሮች ያላቸው መልካም ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ በሚቀጥሉባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ጥቅምት 4 ቀን 2010 ዓ.ም.

READ  የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የከፈሉትን መስዕዋትነት የሚያስታውስ "ተከፍሎልናል" ታሪካዊ ዘጋቢ ፊልም እየተዘጋጀ ነው
Continue Reading

Business

ኢትዮጵያ ታንዛኒያውያን የአውሮፕላን አብራሪዎችን ለማሰልጠን ከአገሪቱ ጋር ስምምነት ገባች

Published

on

ኢትዮጵያ ታንዛኒያውያን የአውሮፕላን አብራሪዎችን ለማሰልጠን ከአገሪቱ ጋር ስምምነት ገባች

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የአውሮፕላን አብራሪዎች እና ቴክኒሻኖች ስልጠና የመግባቢያ ስምምነትን ከታንዛኒያ ዓየር መንገድ ጋር ተፈራረመ።

በሁለቱ ዓየር መንገዶች መካከል በተገባው ስምምነት መሰረት የፊታችን ህዳር እና ታህሳስ ወራት ላይ ታንዛኒያውያን የአውሮፕላን አብራሪዎች እና ቴክኒሻኖች በኢትዮጵያ ስልጠና ይወስዳሉ።

ስልጠናው ኪው 400 እና ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ላይ ያተኮረ እንደሚሆንም ነው የታንዛኒያ ዓየር መንገድ ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የተሟላ የስልጠና እና የጥገና ማእከል እንዳለው ያነሳው ዓየር መንገዱ፥ ስምምነቱ ከዚህ አቅም እንድንጠቀም ያስችለናል ነው ያለው።

የኢትዮጵያ አቭዬሽን አካዳሚ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ደበበ ስምምንቱ ሁለቱንም ዓየር መንገዶች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ የተፈረመው በቅርቡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በታንዛኒያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ሁለቱ አገራት የገቡትን ስምምነት መሰረት በማድረግ ነው።  ኤፍ ቢ ሲ

READ  ከደመወዝ በላይ | በያሬድ ነጋሽ
Continue Reading

Business

የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያን ተከትሎ በሸቀጦች ላይ የዋጋ መናር እንዳይከሰት ይሰራል – የንግድ ሚኒስቴር

Published

on

የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያን ተከትሎ በሸቀጦች ላይ የዋጋ መናር እንዳይከሰት ይሰራል - የንግድ ሚኒስቴር

የኢትየጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀዛቅዞ የቆየውን የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ገቢን ለማስተካከል የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን በ15 በመቶ እንዲዳከም ወስኖ፤ ብር ከሌሎች ሀገራት መገበያያዎች አንጻር ያለው ምንዛሬም በዚህ መልኩ ተሰልቶ ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል።

ከዚህ ባለፈም ዝቅተኛው የባንክ ተቀማጭ ሂሳብ ወለድ ከ5 ወደ 7 በመቶ ከፍ እንዲል ተደርጓል፤ ከውጭ ምንዛሬ ተመኑ ጋር በተያያዘ ግን የዋጋ ግሽበት ሊከሰት ይችላል የሚሉ ስጋቶች ይደመጣሉ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፈሰር ጣሰው ወልደሀና የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን መዳከም፥ የዋጋ መወደድን ሊያስከትል እንደሚችል ይናገራሉ።

ሌላው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዶክተር ቆስጠንጢኖስም ይህ የምንዛሪ ተመን ማሻሻያ፥ በተለይም ለወር ደመወዝተኛው መጠነኛ የሸቀጦች ውድነትን የማስከተል ባህሪ ይኖረዋል ይላሉ።

የኢፌዴሪ የንግድ ሚኒስቴር ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የንግዱ ማህበረሰብ አላስፈላጊ ጭማሪዎችን እንዳያደርግ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ፥ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ማለትም ዘይት፣ ስኳር እና የዳቦ ስንዴ መንግስት በቂ ድጎማ አድርጎ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገባቸው በመሆኑ እነዚህ የፍጆታ እቃዎች ላይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ከመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ባሻገር የምንዛሪ ተመኑ ተግባራዊ ከተደረገበት ቀን በፊት በገቡ እቃዎች ላይም ማስተካከያውን ተገን አድርጎ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ነው ያሉት።

እስካሁን በአከፋፋዮችም ሆነ በማጠራቀሚ ዲፖዎች የሚገኘው ነዳጅም ባለፈው የውጭ ምንዛሪ ተመን የገባ በመሆኑ፥ የዋጋ ጭማሪ አይደረግበትም።

ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ግን በአዲሱ የውጭ ምንዛሬ ተመን የሚገቡ በመሆናቸው፥ እንደ መሸጫ ዋጋቸው ታይቶ መጠነኛ ማስተካከያ ሊደረግባቸው እንደሚችል ተናግረዋል።

READ  የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የከፈሉትን መስዕዋትነት የሚያስታውስ "ተከፍሎልናል" ታሪካዊ ዘጋቢ ፊልም እየተዘጋጀ ነው

አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎች እንዳይኖሩ በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ስር ያሉ አለ በጅምላ እና የመንግስት ልማት ድርጅቶችን ማስፋት እና ማጠናከርም በሚኒስቴሩ የተያዙ እቅዶች ናቸው።

አስመጭውም ሆነ አከፋፋዩ ለሀገር እና ለህብረተሰቡ በማሰብ ፍትሃዊ የሆነ ንግድ ማካሄድ ይገባዋል ነው ያሉት አቶ ወንድሙ።

ከዚህ ዉጭ ግን አላስፈላጊ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ካሉ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

ለዚህም እንዲያመች በየገበያ ማዕከላት፣ ሱፐር ማርኬት፣ በዋና ማከፋፋያ እና ችርቻሮ ቦታዎች ላይ ድንገተኛ የቁጥጥር ስራዎች ይካሄዳሉ።

በቁጥጥሩ አላግባብ ትርፍ ለማግኘት በሚል ከፍተኛ ጭማሪ ሲያደርጉ የተገኙ ነጋዴዎች ካሉ ግን ይህን ማስተካከል የሚችል፥ እርምጃ ሚኒስቴሩ ለመውሰድ እንደሚገደድም አስረድተዋል።

መንግስት ከሚያደርገው ቁጥጥር ውጭ ሸማቹ ህብረተሰብ የንግድ ስርዓቱን የሚያዛባ ማንኛውንም ድርጊት ከተመለከተ ተገቢውን ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ሚኒስቴሩ ጥሪውን አቅርቧል። ኤፍ ቢ ሲ

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close