Connect with us

Art and Culture

የጆን ኤፍ ኬኔዲን 100ኛ የልደት በዓል የሚዘክር የፎቶ ዓውደ ርዕይ በባህርዳር ለእይታ ክፍት ሆነ

Published

on

ናትየፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን 100ኛ የልደት በዓል የሚዘክር የፎቶ ዓውደ ርዕይ በባህርዳር ለእይታ ክፍት ሆነ

የአሜሪካ ኤምባሲ የፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን 100ኛ የልደት በዓል የሚዘክር የፎቶ ዓውደ ርዕይ በማዘጋጀት ለባህርዳር ወጣቶች የላቀ አስተዋጽኦ ክብር ይሰጣል

ባህርዳር፤ ኢትዮጵያ፤ ጥቅምት 1, 2010 ዓ.ም.፡ – የአሜሪካ ኤምባሲ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የጆን ኤፍ ኬኔዲን 100ኛ የልደት በዓል የሚዘክር የፎቶ ዓውደ ርዕይ አዘጋጅቷል፡፡ የፕሬዚዳንት ኬኔዲን ህይወትና ሥራዎች የሚዘክረው የፎቶ ዓውደ ርዕይ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የፕሬዝዳንቱ 100ኛ የልደት በዓል አካል ሆኖ፤ በባህርዳር ገነሜ የሕዝብ ቤተመጽሐፍ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ማዕከል ከጥቅምት 1-8, 2010 ዓ.ም ድረስ ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር በፎቶ ዓውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች የተሻለ ነገን እንዲያሳኩ ለማስቻል ሀገራቸው እያከናወነች ያለውን ሥራዎች ላይ አጽንኦት የሰጠ ንግግር አድርገዋል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም፤ በፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ አነሳሽነት የተመሰረቱት የሰላም ጓድ እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ፤ የፕሬዝዳንቱ ሥራዎች ዘመን ተሻጋሪ እና ቀጣይነት እንዲኖራቸው ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር ሬይነር በንግግራቸው በተለይም በቅርቡ የተጠናቀቀውን እና ለ240 የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎች የኮምፒዩተር ሳይንስ ክህሎትን ለማዳበር በአምስት የኢትዮጵያ ከተሞች ሲሰጥ የቆየውን Girls Can Code የመሳሰሉ ስልጠናዎች ያላቸውን ጠቀሜታ አፅንኦት ሰጥተው አውስተዋል፡፡

ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት መርሀ ግብሮች አንዱ እና እድሜያቸው ከ15-29 ለሆኑ ሥራ አጥ የገጠር ወጣቶች ገቢያቸውን እና የኢኮኖሚ አቅማቸውን ማዳበር የሚያስችለው “የወጣቶች አቅም ግንባታ” መርሀ-ግብር፤ በአምባሳደሩ ንግግር ከተጠቀሱት ውስጥ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም፤ በአሜሪካ መንግሥት አማካይነት ቀጣይ የአፍሪካ መሪዎችን መፍጠር ላይ የሚያተኩረው የወጣት አፍሪካውያን መሪዎች ጅማሮ መርሀ
ግብር (YALI) በአምባሳደሩ ንግግር ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነበር፡፡

READ  የአልሸባብ ሁለት ከፍተኛ አመራሮች ለሶማሊያ መንግስት እጃቸውን መስጠታቸው ተዘገበ

የዛሬው መርሀ- ግብር፤ እ.አ.አ. በ2018 ለሚካሄደው እና አሸናፊዎች በአሜሪካ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ
የቀለም ትምህርት እና የአመራር ክህሎት ስልጠና ዕድል፤ እንዲሁም የአፍሪካ ቀጣይ መሪዎች የእርስ በርስ ትስስር እንዲፈጥሩ ለሚያስችለው የማንዴላ ዋሽንግተን ፌሎውሽፕ ማመልከቻ የመጨረሻ ቀን ጋር ተገጣጥሟል፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የዝግጅቱ አካል የሆነ እና የፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ሥራዎች ለማስቀጠል ያለመ፤ በበጎ ፈቃደኝነት፤ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ ትምህርት እና ሥራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ የወጣቶች ኮንፈረንስ እና የፓናል ውይይት ለጥቅምት 2, 2010 አሰናድቷል፡፡

የፎቶግራፍ ዓውደ ርዕዩ በባህርዳር ከተማ ከታየ በኋላ፤ በሐዋሳ፤ ጂማ እና ድሬዳዋ ከተሞች በመዘዋወር ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፤ በመጨረሻም፤ በዘላቂነት ወደ ሚታይበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቤተመጻሕፍት ይመለሳል፡፡

በብሩክሊን ማሳቹሴትስ እ.አ.አ. በግንቦት 29፤ 1917 የተወለዱት ፕሬዝዳንት ኬኔዲ፤ በዕድሜ ወጣቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ ሲሆን፤ በተለይም ለትምህርት፤ ወጣቶችን ለሀገራቸው እንዲሰሩ በማበረታታት እና ሰውን በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ በነበራቸው ትልቅ ህልም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ይታወቃሉ፡፡

የፕሬዝዳንት ኬኔዲ የስልጣን ዘመን በአሜሪካ ወርቃማው የፎቶ ጋዜጠኝነት ዘመንም ነበር፡፡ እ.አ.አ. በ1946 ለአሜሪካ የምክር ቤት አባልነት መወዳደር ከጀመሩበት አንስቶ፤ ከጃኩሊን ኬኔዲ ጋር እ.አ.አ. በ1953 የፈጸሙት የተረት ዓለም የሚመስል ጋብቻ፤ እ.አ.አ. በ1960 ወደ ዋይት ሀውስ ለመግባት የነበረው ሂደት፤ እንዲሁም የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምነት እና የ1963ቱን አሰቃቂ ግድያ ጨምሮ ፕሬዝዳንት ኬኔዲ በርካታ ፎቶግራፎችን በመነሳት ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው ፖለቲከኛ ነበሩ፡፡

የኬኔዲ ፕሬዝዳንታዊው ቤተመጽሐፍ እና ሙዚዬም 100ኛውን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በመላው አሜሪካ አዲሱን ትውልድ በማነቃቃት፤ ድፍረት፤ ነጻነት፤ ፍትህ፤ የአገልጋይነት መንፈስ እና ራዕይ የመሳሰሉ የእርሳቸው ዘመን ጠቃሚ እሴቶችን ትርጉም እንዲረዱ ለማስቻል ተከታታይ ሁነቶችን ያዘጋጃል፡፡ ዓውደ ርዕዩ በአሜሪካ ዋሽንግተን በከተማ ደረጃ ከጆን ኤፍ ኬኔዲ ፐርፎረሚንግ አርትስ፤ ከስሚዞንያን ብሔራዊ የስዕል ማዕከል እንዲሁም ከስሚዞንያን ብሔራዊ የታሪክ ሙዚየም እና ከዋይት ሀውስ የታሪክ ማህበር እና
ኒውዚዬም ጋር በጥምር ይከበራል፡፡

READ  ዶናልድ ትራምፕ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር በስልክ ተወያዩ

Continue Reading

Art and Culture

የኢትዮጵያ ባንዲራ ጉዳይ የባንዲራ ቀን አጀንዳ?

Published

on

የኢትዮጵያ ባንዲራ ጉዳይ የባንዲራ ቀን አጀንዳ?

የኢትዮጵያ ባንዲራ የሙስሊሙም የክርስቲያኑም የአይሁዱም ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ከእነዚህ እምነቶች መምጣት በፊት ያገኘችው የህገ ልቦና ዘመን ቃል ኪዳን ነውና?  | ስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

አልታደልንም፡፡ ይህው በባንዲራችን እንኳን መች እንግባባለን፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ እንደኛ ብዙ ባንዲራ ይዞ አንድ መሆን ያቃተው ቀደምት ህዝብ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡

ኮኮቡን የሚጠሉ ወገኖችም ሆኑ አንበሳውን የሚናፍቁ፣ አሊያም ኮኮቡ ጌጣችን ነው ያሉ፤ ዓላማቸው በባንዲራ ልዩነት አንድ የነበረችውን ሀገር አስር የማድረስ እስኪመስል ግራ አጋብተውናል፡፡

የኢትዮጵያን ባንዲራ ቀለማት የእኔ ብላ በመቀበል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፋና ወጊ ናት፡፡ ይሄ የሚያስመሰግን ነው፡፡

ጥቂት መስመር የሳቱ እምነታችን ኦርቶዶክሳውያን ነው የሚሉ ወገኖች ደግሞ ባንዲራውን ሙሉ የእምነታችን ነው በማለት ለሀገራዊ አንድነቱ እንቅፋት የሆኑ ይመስለኛል፡፡

ከዚህ ቀደም አንድ ጽሑፍ ላይ ያነበብኩት ሀሳብ ይሄንን ይበልጥ ያብራራልኛል ብዬ አስባለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ባንዲራ የአይሁዱም፣ የክርስቲያኑም የሙስሊሙም ኢትዮጵያ ነው፡፡ የባንዲራው ታሪክ መነሻ ኖህ ነው፡፡ ኖህ የህገ ልቦና ዘመን ነቢይ ነው፡፡ ኖህ የአይሁድ አባት ነው፡፡ ኖህ የክርስቲያኖች ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ ኖህ በእስልምና ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው ነቢይ ነው፡፡ እንግዲህ ሦስት ሳንሆን በፊት አንድ አድርጎ ያግባባን የነበረው የኖህ ቃል ኪዳን ነበር ማለት ነው፡፡ አሁን በባንዲራችን ሳቢያ ብዙ ሆነናል፡፡

የዘንድሮው ደመራ ላይ የቀድሞውን ባንዲራ ይዘው የታዩ ወገኖች አሁንም የባንዲራ ጉዳይ እንዳልተፈታ አሳይተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በሚደረጉ የቄሮ ሰልፎች የኢትዮጵያ ባንዲራ የመንገድ ላይ ማስታወቂያዎችን ያህል እንኳን ውልብ አትልም፡፡

በኦሮሚያ የኦነግ ባንዲራ አሁን ክልላዊ የሆነ እስኪመስል የሰልፎች ማድመቂያ ሆኗል፡፡

ያለ አግባብ በባንዲራ ጉዳይ እረፍት ወስዶ የተነሳው ኢህአዴግ ዳግም ኢትዮጵያን በአንድ ባንዲራ ለማግባባት እያደረኩ ነው የሚለው ጥረት በተቃራኒው ባንዲራ የማያግባባት ሀገር ትፈጠር ዘንድ አንድ ባለድርሻ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

READ  የአልሸባብ ሁለት ከፍተኛ አመራሮች ለሶማሊያ መንግስት እጃቸውን መስጠታቸው ተዘገበ

በአማራ ክልል ለዘመናት የኖረው የቀድሞ ባንዲራን ይዞ ለቀብር ሥርዓት መውጣት ማስወንጀል ከጀመረ ወዲህ ባንዲራዋ የበለጠ ክብር አግኝታለች፡፡

በተቃራኒው ባለ ኮከቡን ባንዲራ የመንግስት አድርጎ ማየቱም ተለምዷል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የባንዲራ ቀንን ከመደገስ ግን አልቦዘንም፡፡ የእኔ ምኞት የሚያግባባንን ባንዲራ ማየት ነው፡፡ DIRETUBE

Continue Reading

Art and Culture

በ7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች

Published

on

በ7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች

በትላንትናው ዕለት የተካሄደው 7ኛው የለዛ የአድማጮች ምርጥ የኪነጥበባት ሽልማት አሸናፊዎች….

የአመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም – ዘመን
የአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይ – አለምሰገድ ተስፋዬ (ያበደች የአራዳ ልጅ 3)
የአመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይት – ዘሪቱ ከበደ (ታዛ)
የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ – ኢትዮጵያ (ቴዎድሮስ ካሳሁን)
የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ/ድምፃዊት – ዳዊት አለማየሁ
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ – ብስራት ሱራፌል (ወጣ ፍቅር)
የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም – ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)/ኢትዮጵያ/
የአመቱ ምርጥ ፊልም -ታዛ
የሕይወት ዘመን ተሸላሚ – ግርማ በየነ

SHEGER FM 102.1 RADIO

READ  አራት ወጣቶችን አባብሎ ወደ ሳዑዲ በመላክ የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ያደረገው ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ
Continue Reading

Art and Culture

በጣና ሃይቅ የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች ወደስፍራው እያመሩ ነው

Published

on

በጣና ሃይቅ የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች ወደስፍራው እያመሩ ነው

በጣና ሃይቅ የተንሰራፋውን የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻን ለማገዝ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ 200 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ወደ ባህርዳር እያመሩ መሆኑን የሁለቱም ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጎዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት ጣናን ለመታደግ በሚደረገው ዘመቻ ለመሳተፍ ከ200 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች “ጣና የእኛ ነው” በሚል ወደ አማራ ክልል ማምራታቸውን ገልፀዋል።

ጣናን እንታደግ በሚለው ዘመቻ በክልል የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ከዚህ ቀደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒትስር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግስት ባለስልጣናት የእምቦጭ አረምን መስፋፋት በጣና ተገኝተው የስጋቱን ደረጃ ተመልክተዋል።

እምቦጭ አረምን የማስወገድ የ2010 ዘመቻ ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሩ ይታወቃል።

ጣና የአንድ ክልል ሃብት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ገደብ የለሽ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

ይህንንም ተከትሎ የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር በማምራት ለአንድ ሳምንት የቆየ ለ“ጣናን እንታደግ” ዘመቻ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ጨዋታዎችን ከባህርዳር ከተማ፣ ከፋሲል ከነማ እና ከአውስኮድ ጋር ሲያደርግ ሰንብቷል።

ደጋፊዎቹም በጣና ሀይቅ የተንሰራፋውን የእምቦጭ አረም በማስወገድ ዘመቻም ተሳትፈው ነበር።

የጎንደር እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲዎች አረሙን ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ የሚያግዙ የተለያዩ ማሽኖችን በማዘጋጀት ላይ መሆናቸው ተነግሯል። ኤፍ ቢ ሲ

READ  የአይኤስ አጥፍቶ ጠፊን በር ላይ ያስቆመችውና የተሰዋችው ግብጻዊት ፖሊስ በክብር ተሸኘች
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close