Connect with us

Ethiopia

በኢትዮጵያ በጡት ካንሰር ከሚጠቁት 13 ሺህ ሰዎች ወስጥ 53 በመቶዎቹ ለሞት ይዳረጋሉ

Published

on

በኢትዮጵያ በጡት ካንሰር ከሚጠቁት 13 ሺህ ሰዎች ወስጥ 53 በመቶዎቹ ለሞት ይዳረጋሉ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ለጡት ካንሰር ከሚጋለጡ 13 ሺህ ሰዎች ውስጥ 7 ሺህ ያህሉ ለሞት እንደሚዳረጉ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሕብረተሰቡ ለጡት ካንሰር ያለው የግንዛቤ ማነስና ህክምናውን የሚሰጡ ተቋማት በቂ አለመሆን በሽታውን በቀላሉ መከላከል እንዳይቻል ማድረጉንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የጡት ካንሰር በቅድሚያ በጡት ላይ በመከሰት ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመዛመት ለሞት የሚያጋልጥ ሲሆን በሽታው በዋናነት ሴቶችን የሚያጠቃ ቢሆንም አልፎ አልፎ ወንዶችንም ያጠቃል።

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 13 ሺህ ሰዎች ለጡት ካንሰር የሚጋለጡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 7 ሺህ ያህሉ እንደሚሞቱ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የጥቅምት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ የጡት ካንሰርን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ሆኖ ይቆያል። ይህን አስመልክቶ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ጋር በሰጡት መግለጫ ማህበረሰቡ ስለ በሸታው ያለው ግንዛቤ በቂ ባለመሆኑ ተጋላጭነቱን መቀነስ አለመቻሉ ተገልጿል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ ኢትዮጵያ በዚሁ በሽታ ከሚጠቁ አዳጊ አገራት አንዷ መሆኗን ጠቅሰው የህብረተሰቡ የግንዛቤ ማነስ ዋነኛው ችግር መሆኑን ገልፀዋል። የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ጡት አለማጥባት፤ሲጋራ ማጨስ፣አልኮል መጠጣት፣ከሆርሞን ጋር የተያያዙ መድሀኒቶችን መውሰድ፣ቶሎ አለመውለድ እና ሌሎቹ ምክንያቶች ለጡት ካንሰር መንስኤዎች ናቸው።

የጡት ካንሰር ምርመራውም ሆነ ህክምናው በጣም ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅና ህይዎትን ሊያሳጣ ስለሚችል ሕብረተሰቡ ቅድመ ምርመራ በማድረግ መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል።

ሚኒስቴሩም በብሄራዊ ካንሰር መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ እየተመራ እንደማንኛውም በሽታ መከላከሉ ላይ ትኩረት ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል። ሚኒስትሩ አሁን ላይ 12 የመንግስት ሆስፒታሎች ህክምናውን እየሰጡ መሆኑን ጠቅሰው የህክምና ማዕከላት እጥረትን ለመቀነስ ተጨማሪ ስድስት የህክምና ማዕከላት እየተገነቡ መሆኑን ገልፀዋል።

READ  5ኛ ዓመት “የኢትዮጵያ ስፔሊንግ ቢ” ውድድር ግንቦት 19 ይካሄዳል

የግል ህክምና ተቋማት ህክምናውን እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚንስትሩ ሐኪሞችን በተጓዳኝነት ስለ በሽታው በማሰልጠን እንዲመረምሩና ህክምና እንዲሰጡ እየተደረገ ነውም ብለዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ በበኩላቸው በአገራችን ስለ ጡት ካንሰር ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑ በየዓመቱ በበሽተው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንዲመጣ አድርጎታል ብለዋል። በመሆኑም መገናኛ ብዙሃኑን ጨምሮ ማህበረሰቡን ያሳተፈ የግንዛቤ መፍጠሪያ መንገድ መዘጋጀት እንዳለበት ጠቁመዋል።

በተለይም እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑ እናቶች እንቅስቃሴ ስለማይሰሩ ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ይሆናሉ ብለዋል። በመሆኑም የአካል እንቅስቃሴዎችን በመስራት እንዲሁም ቅድመ ምርመራ በማድረግ የበሽታውን መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዘንድሮው የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በኢትዮጵያ ”የጡት ካንሰር በሽታን መከላከል የሁላችንም ሀላፊነት ነው፤ጡትዎን በመዳሰስና ቅድመ ምርመራ በማድረግ ህይዎትዎን ይታደጉ” በሚል መሪ ሀሳብ ለ11ኛ ጊዜ ይከበራል። ena

Continue Reading

Ethiopia

አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

Elias Tesfaye

Published

on

በረከት ስምኦን

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል።
አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ተነግሯል።

አቶ በረከት ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስገባታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ በቢሮአቸው ተገኝተው የነበሩት ሀሙስ ዕለት ነበር።

አቶ በረከት በተመሳሳይ ጊዜ ከሁለት የሃላፊነት ቦታቸው የተነሱ ሲሆን ለሥራ መልቀቃቸው ግልፅ ያለ ምክንያት አልቀረበም።

ነገር ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ብዙም ደስታኛ እንዳልነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።

በተለይ ማዕከሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚያቀርባቸው ሃገር አቀፍ የፖሊሲና የአስተዳደር ጥናቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩና በመንግሥት ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ብዙም ተቀባይነት አግኝተው ተግባራዊ አለመደረጋቸው ለቅሬታቸው ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። More Here

READ  የአዲሱ የ‹‹ኢኮኖሚ አብዮት›› አንድምታዎች
Continue Reading

Ethiopia

ጠ/ ሚኒስትሩ ለኢቢሲ ሠራተኞች በልዩ ሁኔታ ቤት ለመስጠት ቃል ገቡ

Published

on

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

የኢትዮጵ ያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኢቢሲ) ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበት መንገድ በልዩ ሁኔታ እንደሚታይ፣ የባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት ድርጅቱ የውስጥ አሠራሩን እንዲያሻሽል ጠ/ ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ መምከራቸው ተሰማ።

ጠ/ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኢቢሲ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር ነው።
መንግሥታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በትላንት ዕትሙ የኢቢሲ ሠራተኞች ያለባቸውን የቤት ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት ሠራተኛው በልዩ ሁኔታ ቤት የሚያገኙበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉ ጠ/ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ጵፏል።
የመንግሥት ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለመቅረፍ ኢቢሲ አሠራሩንእንዲያሻሽልና ልማታዊ ጋዜጠኝነትን እንዲተገብር የመከሩት አቶ ሀይለማርያም ልማታዊ ጋዜጠኝነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁለተኛ ድግሪ የሚሰጥበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል። DIRETUBE

READ  ከተፈቀደው የክብደት መጠን በላይ ጭናቹዋል በሚል 43 ሺህ ኩንታል ስኳር የጫኑ ተሽከርካሪዎች አዋሽ አርባ ቆመዋል
Continue Reading

Ethiopia

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

FanaBC

Published

on

By

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት እና በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዶክተር መረራ “ድርጊቱን አልፈፀምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” ብለው የዕምነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፥ ጠበቃቸው 11 ወር ቆይተው ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸው እንደዘገየ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

በከፊል የሚቀርቡ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞች እንዲጠይቋቸው ችሎቱን የጠየቁ ሲሆን፥ ችሎቱም ይህን ጥያቄያቸውን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ አዟል።

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር በይፋ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይም ዛሬ ብይን ሰጥቷል።

በህገመንግስቱ አንቀፅ 20 ንዑስ ከቁጥር 4 ጋር ይጋጫል ወይስ አይጋጭም በሚለው ላይ ህገመንግስታዊ ትርጉም ማስፈለጉ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከህገመንግስቱ አንፃር እንደማይጋጭ ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ ነው ችሎቱ የምስክሮች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ የአቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ ብይን የሰጠው።

እነዚህን መስክሮች ከጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ።

ፍርድ ቤቱ ከዶክተር መረራ ጋር የተከሰሱ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይም አዟል። ኤፍ ቢ ሲ 

READ  የዋልድባ ገዳም ተቆርቋሪ አባት ታሠሩ ሲል “ዋልድባን እናድን” የተባለ ስብስብ አስታወቀ
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close