Connect with us

Ethiopia

በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በነበሩ ሰልፎች የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል

Elias Tesfaye

Published

on

የኦሮሚያ

የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትላንት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ማን እንደጠራቸው ባለታወቁ ሰልፎች ላይ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት እንዳረጋገጠው በትላንትናው ዕለት በተለያዩ የክልሉ ከተሞች በነበሩ ሰልፎች የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ33 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል። ከሟቾቹ መካከል ሶስቱ በሻሸመኔ ከተማ ነው ህይወታቸው ያለፈው።

በዚሁ ከተማ ከተገደሉት መካከል የ67 ዓመት አዛውንት የሆኑት አቶ ገለቶ ገነሞ ይገኙበታል። አቶ ገለቶ በሻሸመኔ ከተማ ነዋሪ የሆነውን ልጃቸውን ሃምዳ ገለቶን ለመጠየቅ ከገጠር መጥተው ነበር በትላንትናው ዕለት በጥይት ተመተው ህይወታቸው ያለፈው። ሃምዳ ለቢቢሲ እንደተናገረው ”አባቴ መንገድ ላይ በነበረበት ጊዜ ምንም ዓይነት ተቃውሞ አልነበረም። መንገድ ላይ እየተጓዘ ነበር ከመኪና ላይ በተተኮሰበት ጥይት ተመትቶ ህይወቱ ያለፈው” ብሏል።

ለደህንነቱ ሲባል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ሌላ ተጎጂ እጁ ላይ በጥይት ተመቶ ጉዳት እንደረሰበት ለቢቢሲ ተናግሯል። ”በመጀመሪያ በድንጋይ የተመታሁ ነበር የመሰለኝ አትኩሬ ስመለከት ነው በጥይት እንደተመታሁ የተረዳሁት። በድንጋጤ ስሜት ውስጥ ሆኜ ወደኋላ ዞሬ ሳይ አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል የጫነ ፓትሮል መኪና ተመለከትኩ። በገቢና ውስጥ ሌሎች ሊኖሩ ይችላሉ እኔ ግን አላየሁ” ብሏል።

በሰልፉ ላይ ተሳታፊ የነበረው ይህ ወጣት ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሃዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል እንደተላከ ነግሮናል።

የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ጠይባ ሃሰን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ትላንት በነበረው ሰልፍ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጠዋል። ወ/ሮ ጠይባ ለሁለት ወጣቶች እና ለአንድ አዛውንት መሞት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት እና አንድ የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባል በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ቁጥጥር ስር ይገኛሉ ብለዋል።

READ  ጳጳስና ፓትረያሪክ ፊት የነሳው የአባባ ተስፋዬ ቀብር

More on BBC

Elias Tesfaye is an Associate at news.et. ‘Elias is a lawyer by profession and a photographer by training. He believes that the status quo is never good enough and that life is best lived to the fullest.

Continue Reading

Ethiopia

አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

Elias Tesfaye

Published

on

በረከት ስምኦን

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል።
አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ተነግሯል።

አቶ በረከት ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስገባታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ በቢሮአቸው ተገኝተው የነበሩት ሀሙስ ዕለት ነበር።

አቶ በረከት በተመሳሳይ ጊዜ ከሁለት የሃላፊነት ቦታቸው የተነሱ ሲሆን ለሥራ መልቀቃቸው ግልፅ ያለ ምክንያት አልቀረበም።

ነገር ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ብዙም ደስታኛ እንዳልነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።

በተለይ ማዕከሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚያቀርባቸው ሃገር አቀፍ የፖሊሲና የአስተዳደር ጥናቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩና በመንግሥት ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ብዙም ተቀባይነት አግኝተው ተግባራዊ አለመደረጋቸው ለቅሬታቸው ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። More Here

READ  ከሽብር ቡድኖች ጋር ተባብረዋል በተባሉ ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ
Continue Reading

Ethiopia

ጠ/ ሚኒስትሩ ለኢቢሲ ሠራተኞች በልዩ ሁኔታ ቤት ለመስጠት ቃል ገቡ

Published

on

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

የኢትዮጵ ያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኢቢሲ) ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበት መንገድ በልዩ ሁኔታ እንደሚታይ፣ የባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት ድርጅቱ የውስጥ አሠራሩን እንዲያሻሽል ጠ/ ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ መምከራቸው ተሰማ።

ጠ/ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኢቢሲ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር ነው።
መንግሥታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በትላንት ዕትሙ የኢቢሲ ሠራተኞች ያለባቸውን የቤት ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት ሠራተኛው በልዩ ሁኔታ ቤት የሚያገኙበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉ ጠ/ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ጵፏል።
የመንግሥት ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለመቅረፍ ኢቢሲ አሠራሩንእንዲያሻሽልና ልማታዊ ጋዜጠኝነትን እንዲተገብር የመከሩት አቶ ሀይለማርያም ልማታዊ ጋዜጠኝነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁለተኛ ድግሪ የሚሰጥበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል። DIRETUBE

READ  የከተሞች የጎንዮሽ መስፋፋት ለአርሶ አደሮች ሥጋት መሆኑ ተገለጸ
Continue Reading

Ethiopia

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

FanaBC

Published

on

By

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት እና በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዶክተር መረራ “ድርጊቱን አልፈፀምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” ብለው የዕምነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፥ ጠበቃቸው 11 ወር ቆይተው ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸው እንደዘገየ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

በከፊል የሚቀርቡ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞች እንዲጠይቋቸው ችሎቱን የጠየቁ ሲሆን፥ ችሎቱም ይህን ጥያቄያቸውን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ አዟል።

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር በይፋ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይም ዛሬ ብይን ሰጥቷል።

በህገመንግስቱ አንቀፅ 20 ንዑስ ከቁጥር 4 ጋር ይጋጫል ወይስ አይጋጭም በሚለው ላይ ህገመንግስታዊ ትርጉም ማስፈለጉ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከህገመንግስቱ አንፃር እንደማይጋጭ ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ ነው ችሎቱ የምስክሮች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ የአቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ ብይን የሰጠው።

እነዚህን መስክሮች ከጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ።

ፍርድ ቤቱ ከዶክተር መረራ ጋር የተከሰሱ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይም አዟል። ኤፍ ቢ ሲ 

READ  ከሽብር ቡድኖች ጋር ተባብረዋል በተባሉ ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close