Connect with us

Ethiopia

ሽግግርን ከባህላቸው ከገዳ የተማሩት ክቡር አቶ አባዱላ እና የስልጣን ስንብት

Published

on

ሽግግርን ከባህላቸው ከገዳ የተማሩት ክቡር አቶ አባዱላ እና የስልጣን ስንብት

ሽግግርን ከባህላቸው ከገዳ የተማሩት ክቡር አቶ አባዱላ እና የስልጣን ስንብት | ስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ያው ቀላሉ ብርቅ የሚሆንብን ከኋላ ታሪካችን ተነስተን ነው፡፡ እኛ መሪን ካልገደልነው፣ ካላባረርነው አሊያም ካልቀበርነው የሚሄድ አይመስለንም፡፡ እናም በዓለም ሁሉ የተለመደው ለእኛ ብርቅ ነው፡፡

አባዱላ ከስልጣናቸው ለመሰናበት ራሳቸው ተጠቁ የሚለው ታላቅ ጉዳይ ሆኖ የሰነበተውም ለዚህ ይመስለኛል፡፡
እንግዲህ ሌላውን ትተን አባዱላ ኦሮሞ መሆናቸውን ካሰብን ነገሩ እንግዳ ላይሆን ይችላል፡፡

በገዳ ባህል በየስምንት አመቱ ለተከተለው ትውልድ እያስረከበ ከቀደመው ትውልድ እየተረከበ ለሚተካካ ባህል ባለቤት ከሃያ አምስት ዓመት በኋላ መልቀቅ እስከአሁን ምነው የሚያስብል እንጂ የሚያስደነግጥ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከለመድነው የተለየ በሆነብን ነገር ደንግጠናል፡፡

የአንጋፋውን የኢህአዴግ መሪ መልቀቅ ከኢቢሲ ቀድመን የሰማን መሆናችን፣ በአደባባይ መቀጠል የማይችሉበት ምክንያት መፈጠሩን መናገራቸው ጉዳዩን ልዩ አድርጎታል፡፡

ከዚህ በፊት ተሰናበቱ የተባሉ ታላላቅ የፓርቲው ሰዎች አሁንም ፓርቲው ጉያ፣ አሁንም ከፓርቲው ጋር፣ አሁንም የእጅ አዙር መሪዎች ሆነው አሉ፡፡

በአዳማ ጉባኤ ካድሬ እንባ እያቃረው በቀድሞው መሪ የላቀ ምስጋና የተሸኙት አቶ አዲሱ ለገሰ ዛሬም ቀድሞ በነበሩበት የብአዴን ግንባር ላይ ናቸው፡፡ ህወሃቶች መንደርም ይሄ የተለመደ ነው፡፡ የአባዱላን ሽኝት ከዚህ የተለየ እንዲሆን እመኝላቸዋለሁ፡፡

እኒህ ሰው በኦሮሚያ ተወዳጅነት የነበራቸው ሰው ነበሩ፡፡ ለሰው ቅርብና አዛኝ ተደርገውም ይወሰዳሉ፡፡ ሳቅ የማይለያቸው አባዱላ ከኦሮሚያ ብሔርተኝነት ማበብ ጋር ስማቸው የሚነሳ መሪ ናቸው፡፡ ይቅር ባይነታውንም ቢሆን የሚያወድሱ አሉ፡፡ አሁንም ልንሸኝ የተዘጋጀነው እኒህን ሰው ነው፡፡

ቀሪው ጊዜያቸው የስንብታቸውን ያህል አሳሳቢ ነው፡፡ ከጀርባ ሆነው አቶ ለማን እንዲህ አድርግ የሚሉ የኋላ አጥቂ ከሆኑ ቦታ ቀየሩ እንጂ እዛው ናቸው፡፡ እንደ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ መኖር ከቻሉ ስንብታቸው እውን ይሆናል፡፡ ያም ሆኖ ጠየቁ እንጂ እስከአሁን ተቀባይነት ያገኘ ነገር የለም፡፡

ብዙ ሰው የተመለከተው የዘንድሮ የመክፈቻ ጉባኤ አባዱላን በማን ሊቀይር ይሆን በሚል ዜጎች የጓጉለት ነበር፡፡ ግን ወፍ የለም፡፡ የስንብታቸው ጉዳይ የማያጠያይቅ ቢሆንም የረዘመው ዝምታ ሌላ ስጋት ሆኗል፡፡

ከስንብታቸው ዜና ጋር ጎን ለጎን አዳዲስ ምልክቶች መታየታቸው ደግሞ ኦህዴድን ስራ ሳያዛበት አይቀርም፡፡
ለምሳሌ ቡራዮ በኦነግ ባንዲራ ማሸብረቋ፣ እዚህም እዚያም በክልሉ የሚታዩ ተቃውሞዎች፣ እልባት ማግኘት ያልቻለው የኢትዮጵያ ሱማሌ እና የኦሮሚያ ክልል የድንበር ግጭት እነዚህን የመሳሰሉ ጉዳዮች የወጠሩት ኦህዴድ አቶ አባዱላን በደመቀ ድግስ ለመሸኘት የተመቸው አልመሰለኝም፡፡ ያም ሆኖ የስንብቱ ጉዳይ ቁርጥ ነው፡፡

በኢህአዴግ ታሪክ ከዚህ ቀደም አንድ መሪ ብልሹ በመሆኔ በሃላፊነቴ ልቀጥል አልችልም ማለታቸውን ብቻ ነበር የምናውቀው፤ እሳቸውም ቢሆን ከስልጣን ወደ ወህኒ ነው የወረዱት፡፡ ከዚያ ወዲህ አራቱም ግንባሮች እንዲህ ያለ ውሳኔ የወሰነ መሪ ኖሯቸው አያውቅም፡፡

ሸኙኝ ያለ፤ በቃኝ ብሎ በአደባባይ የወጣ መሪ በመሆን አባዱላ አዲስ ነገር ያስተማሩ ይመስለኛል፡፡ ጉዳዩ ከሽኝቱ በኋላስ ነው? DIRETUBE

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close