Connect with us

Ethiopia

የሱሃባዎቹን ማረፊያ ፍለጋ፤ ኮነባ-በተራሮች በተከበበችው ታሪካዊ ስፍራ

Published

on

የሱሃባዎቹን ማረፊያ ፍለጋ፤ ኮነባ-በተራሮች በተከበበችው ታሪካዊ ስፍራ

የሱሃባዎቹን ማረፊያ ፍለጋ፤ ኮነባ-በተራሮች በተከበበችው ታሪካዊ ስፍራ | ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ከነጃሺ ወደ አፋር ተጉዟል፡፡ በአፋር ክልል ከቀይ ባህር ወደ ኮነባ የዘለቁት ቀደምት ሱሃባዎች ያረፉባትን ስፍራ ጎብኝቷታል፡፡ በተራሮች የተከበበችው ታሪካዊ ስፍራ ሲል እንዲህ ያስጎበኘናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

እነኚህ ተራሮች በሀገሬ ሲኖሩ ያለ ዛሬም አይቻቸው አላውቅም፡፡ ሰንሰለታማዎቹ ተራሮች መሀል ነኝ፡፡ ዙሪያዋን በተራሮች የተከበበች ጠረጴዛ መሳይ ምድር፡፡ ይኽቺ ኮነባ የምትገኘው የሱሃባዎቹ ማረፊያ ናት፡፡

ተራሮቹ እጅግ ይገርማሉ፡፡ በሁሉም አቅጣጫ የተደረደሩት ተራሮች ለተራራ ፍቅር ያለውን ጎብኚ ልብ የሚያቀልጡ ናቸው፡፡ ሸለቆና ተራራ የሚበዛው የኮነባ ወረዳ 51,038.7 ሄክታር የቆዳ ስፋት አለው፡፡
አሁን አፋር ክልል ነኝ፡፡ እነ ዳሎል እነ ኤርታኤሌ የሚገኙበት ዞን ሁለት በሚባለው ቀጠና፤ ኮነባ ወይና ደጋማው የአየር ንብረቷ የሚበዛ የአፋር ምድር ናት፡፡ ቆላው ሰላሳ በመቶ ብቻ ነው፡፡
ለገዲ የኮነባ ትልቁ ወንዝ ነው፡፡ ብዙ ነገር የሚመረትባት ወረዳ ስያሜዋ ራሱ እንግዳ ተቀባይ ህዝብ ማለት ነውና ተቀብላኛለች፡፡

ከቀይ ባህር ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚያቀናው የቅፍለት ተጓዥ ማረፊያ የነበረች የታሪክ ስፍራ ላይ ሌላ በዘመን መካከል ብዙ ያልተነገረለት ታሪክ አለ፡፡

የቀደምት ሱሃባዎች ወደ ነጃሺ የተደረገ ጉዞ አንድ ማረፊያ ስፍራ ላይ ነኝ፡፡ እዚህ አንድ ስፍራ አለች፡፡ የውሃ ኩሬ፤ የተመረዘችዋን ውሃ የጠጡ ሱሃባዎች ተመርዘው በመሞታቸው እዚሁ አርፈዋል፡፡

መቃብራቸው ዛሬም በድንጋይ በተቀመጡ ምልክቶች ከትውልድ ትውልድ እየተሻገረ ነው፡፡ ኮነባ አፋሮች የፍትሕ ሀገር ወደተባለችዋ ምድር የሚመጡ እንግዶችን እንዴት አድርገው እንደተቀበሉ ከሚያሳዩ የታሪክ ማረጋገጫዎች አንዷ ስፍራ ይህቺ ናት፡፡

READ  የሙስና ተጠርጣሪዎች የፍ/ቤት ውሎና ቀጠሮዎች

እስልምና በመካ ዋስትና ባላገኘበት ዘመን የአፋር ጫካዎች ግን ለመጀመሪያዎቹ አማኞች የሰላም መንገዶች ነበሩ፡፡ አፋሮችም ቁይረሾች ላሳደዷቸው አማኞች ፍቅርን የቸሩ ባለ ታሪኮች ናቸው፡፡

ያ ባይሆን ከቀይ ባህር እስከ ንጉሡ ቤተ መንግሥት እንዴት ይደረስ ነበር? ይህቺ ታሪካዊ ስፍራ የብዙ ልዩ ክስተቶች ማዕከል ናት፡፡ መድሃኒት የሆኑ በርካታ እጽዋት የሚገኙባት፣ ከጥንትም የፍየሎችና ግመሎች ምርት የንግድ መአከል ያደረጋት ስፍራ ናት፡፡ DIRETUBE

Ethiopia

አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

Elias Tesfaye

Published

on

በረከት ስምኦን

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል።
አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ተነግሯል።

አቶ በረከት ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስገባታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ በቢሮአቸው ተገኝተው የነበሩት ሀሙስ ዕለት ነበር።

አቶ በረከት በተመሳሳይ ጊዜ ከሁለት የሃላፊነት ቦታቸው የተነሱ ሲሆን ለሥራ መልቀቃቸው ግልፅ ያለ ምክንያት አልቀረበም።

ነገር ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ብዙም ደስታኛ እንዳልነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።

በተለይ ማዕከሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚያቀርባቸው ሃገር አቀፍ የፖሊሲና የአስተዳደር ጥናቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩና በመንግሥት ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ብዙም ተቀባይነት አግኝተው ተግባራዊ አለመደረጋቸው ለቅሬታቸው ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። More Here

READ  ከገነት ተራራ ስር-ከጨዋ ሰፈር ልጆች ሆታ ጋር፤ የከተሞች እናት የሆነችው የጎንደር ደመራ ናፍቆት
Continue Reading

Ethiopia

ጠ/ ሚኒስትሩ ለኢቢሲ ሠራተኞች በልዩ ሁኔታ ቤት ለመስጠት ቃል ገቡ

Published

on

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

የኢትዮጵ ያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኢቢሲ) ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበት መንገድ በልዩ ሁኔታ እንደሚታይ፣ የባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት ድርጅቱ የውስጥ አሠራሩን እንዲያሻሽል ጠ/ ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ መምከራቸው ተሰማ።

ጠ/ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኢቢሲ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር ነው።
መንግሥታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በትላንት ዕትሙ የኢቢሲ ሠራተኞች ያለባቸውን የቤት ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት ሠራተኛው በልዩ ሁኔታ ቤት የሚያገኙበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉ ጠ/ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ጵፏል።
የመንግሥት ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለመቅረፍ ኢቢሲ አሠራሩንእንዲያሻሽልና ልማታዊ ጋዜጠኝነትን እንዲተገብር የመከሩት አቶ ሀይለማርያም ልማታዊ ጋዜጠኝነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁለተኛ ድግሪ የሚሰጥበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል። DIRETUBE

READ  ‹‹ሐገሬንና ሐይሌን አትንካ!››
Continue Reading

Ethiopia

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

FanaBC

Published

on

By

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት እና በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዶክተር መረራ “ድርጊቱን አልፈፀምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” ብለው የዕምነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፥ ጠበቃቸው 11 ወር ቆይተው ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸው እንደዘገየ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

በከፊል የሚቀርቡ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞች እንዲጠይቋቸው ችሎቱን የጠየቁ ሲሆን፥ ችሎቱም ይህን ጥያቄያቸውን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ አዟል።

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር በይፋ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይም ዛሬ ብይን ሰጥቷል።

በህገመንግስቱ አንቀፅ 20 ንዑስ ከቁጥር 4 ጋር ይጋጫል ወይስ አይጋጭም በሚለው ላይ ህገመንግስታዊ ትርጉም ማስፈለጉ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከህገመንግስቱ አንፃር እንደማይጋጭ ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ ነው ችሎቱ የምስክሮች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ የአቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ ብይን የሰጠው።

እነዚህን መስክሮች ከጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ።

ፍርድ ቤቱ ከዶክተር መረራ ጋር የተከሰሱ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይም አዟል። ኤፍ ቢ ሲ 

READ  ዲቪ ሎተሪ 2019 በቀጣይ ሳምንት ይጀምራል
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!