Connect with us

Business

የኦሮሚያ – ሶማሌ አዋሳኝ ግጭት ምርት ወደ ውጪ እንዳይላክ እክል ፈጥሯል

Elias Tesfaye

Published

on

Negeri Lencho

አለማየሁ አንበሴ

  • “ግጭቱን የሚያባብሱና ህዝብን የሚያጋጩ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል”
  • የሶማሌ ክልል፤ ከኦሮሚያ ጋር ለተፈጠረው ግጭት “መንስኤዎችን” ለየሁ አለ
  • “ግጭቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም የማረጋጋትና ሰላም የማስፈን ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው” ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ
  • የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት ሰሞኑን ይቀርባል

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ሌሎች የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል ባለስልጣናትንና የሀገር ሽማግሌዎችን በግጭቱ ዙሪያ ሰሞኑን በድጋሚ ያወያዩ ሲሆን ግጭቱ የሀገሪቱን ምርት ወደውጪ በመላክ ላይ ጭምር እክል መፍጠሩን በመጠቆም፣ ሰላምና መረጋጋት በአፋጣኝ እንዲሰፍን አሳስበዋል።

ከትናንት በስቲያ የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በግጭቱ ወቅት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላትን ወደ ህግ በማቅረብ በኩል የፌደራል መንግስቱ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ጠ/ሚኒስትሩ መናገራቸውን ጠቁሞ በግጭቱ የተፈናቀሉ ዜጎች ተመልሰው እንዲቋቋሙና የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችን የመምከርና የማስታረቅ ስራ መስራት እንዳለባቸው ማሳሰባቸውንም አመልክቷል፡፡

ውይይቱን የተከታተሉት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በበኩላቸው፤ ግጭቱ አሁን ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ሪፖርት በውይይት መድረኩ ላይ መቅረቡን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ በግጭቱ አካባቢዎች በሚገኙ ኬላዎች ተሽከርካሪዎች እንዳያልፉ መደረጉን ተከትሎ፣ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ ለመላክ ችግር መፈጠሩ መታወቁን የጠቆሙት ዶ/ር ነገሪ፤ ከዚህ በኋላ የየትኛውም ክልል የፀጥታ አካል ኬላ አቁሞ እንዳይፈተሽ ትዕዛዝ መተላለፉን ተናግረዋል፤ ይህን ስራ የመቆጣጠር ተግባርም የፌደራል የፀጥታ አካላት መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ በግጭቱ የተፈናቀሉ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ፣ የተዘረፈ ንብረታቸው እንዲመለስ፣ ያለዚያም ካሳ እንዲከፈላቸው እንደሚደረግም ዶ/ር ነገሪ አስታውቀዋል፡፡ የተፈናቀሉትን መልሶ የማቋቋምና አስፈላጊውን ከለላ የመስጠት ኃላፊነቱም ዜጎች የተፈናቀሉባቸው ክልሎች እንዲሆን መወሰኑንና የየክልሎቹን አመራሮችም ይህን ለመፈፀም ቃል መግባታቸውን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም እንደ ማንኛውም ዜጋ ጥበቃ ስለሚደረግላቸው ለደህንነታቸው ሳይሰጉ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው እንዲማሩ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

READ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ ቁጥር 1 እና 2 ላይ ማሻሻያ ተደረገ... በጋምቤላ የሙርሌ ጎሳ አባላት ያደረሱትን ጥቃት በተመለከተም ኮማንድ ፖስቱ መረጃ ሰጥቷል

የሁለቱም ክልሎች አመራር አባላት፣ ለግጭቱ መንስኤ የሆኑ አካላትን በማጋለጥ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዶ/ር ነገሪ፤ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የሚመሯቸውና የሁለቱም ክልል ህዝቦች የሚሳተፉባቸው ህዝባዊ ጉባኤዎች በተከታታይ እንደሚደረጉም አውስተዋል፡፡
በሌላ በኩል የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የክልሉ አስተዳደሮችና የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ለግጭቱ መነሻ ናቸው ያሏቸውን ሶስት ጉዳዮች ተለይተዋል ብሏል፡፡

በመግለጫው መንስኤ ተብለው ከተጠቀሱት መካከልም መሬትን በኃይል የመውሰድ ፍላጎት፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ የማስገባት ፍላጎትና የፌደራል ስርአቱን የማፈራረስና የደርግ ስርአትን የመመለስ ፍላጎት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኩል በመኖሩ ነው ይላል፡፡

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በበኩላቸው፤ በአሁን ወቅት ግጭቱን የሚያባብስና ህዝብን የሚያጋጭ መረጃ በማንኛውም መገናኛ ብዙሃንም ሆነ ግለሰብ እንዳይተላለፍ አቅጣጫ መቀመጡን አስታውቀው፣ መመሪያውን ተላልፈው ግጭቱን የብሄር ግጭት አስመስለው የሚያናፍሱ የኮሚኒኬሽን አካላትና መገናኛ ብዙኃን ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ በድጋሚ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ፤ በሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ፣ የምርመራ ቡድን ወደ ስፍራው ልኮ፣ የግጭቱን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት ሲያጣራ መሰንበቱን የገለጸ ሲሆን ምርመራውን እያጠናቀቀ በመሆኑ፣ ውጤቱን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚያቀርብ፣ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደምሰው በንቲ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ Addis Admas

Continue Reading

Business

አምባሳደር ግርማ ተመስገን የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ

Published

on

አምባሳደር ግርማ ተመስገን የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ

በኮትዲዩቫር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ግርማ ተመስገን ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት አላሳን ዋታራ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል፡፡
ክቡር አምባሳደር በስነስርዓቱ ወቅት፣ ሁለቱ አገሮች ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በስደት ጉዳዮች ላይ እና በጸረ ሽብር መዋጋት ትብብርን ጨምሮ በወሳኝ አህጉራዊና አለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ያላቸው መሆኑን አምባሳደር ግርማ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት ስድስት ጊዜ ወደ አቢጃን በረራ ያደርጋል፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም የቱሪዝም እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳደግ ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ አብራርተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታራ በበኩላቸው፣ ሁለቱ አገሮች ያላቸው መልካም ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ በሚቀጥሉባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ጥቅምት 4 ቀን 2010 ዓ.ም.

READ  British Officials Attempts to Rescue Andargachew Proves Futile
Continue Reading

Business

ኢትዮጵያ ታንዛኒያውያን የአውሮፕላን አብራሪዎችን ለማሰልጠን ከአገሪቱ ጋር ስምምነት ገባች

Published

on

ኢትዮጵያ ታንዛኒያውያን የአውሮፕላን አብራሪዎችን ለማሰልጠን ከአገሪቱ ጋር ስምምነት ገባች

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የአውሮፕላን አብራሪዎች እና ቴክኒሻኖች ስልጠና የመግባቢያ ስምምነትን ከታንዛኒያ ዓየር መንገድ ጋር ተፈራረመ።

በሁለቱ ዓየር መንገዶች መካከል በተገባው ስምምነት መሰረት የፊታችን ህዳር እና ታህሳስ ወራት ላይ ታንዛኒያውያን የአውሮፕላን አብራሪዎች እና ቴክኒሻኖች በኢትዮጵያ ስልጠና ይወስዳሉ።

ስልጠናው ኪው 400 እና ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ላይ ያተኮረ እንደሚሆንም ነው የታንዛኒያ ዓየር መንገድ ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የተሟላ የስልጠና እና የጥገና ማእከል እንዳለው ያነሳው ዓየር መንገዱ፥ ስምምነቱ ከዚህ አቅም እንድንጠቀም ያስችለናል ነው ያለው።

የኢትዮጵያ አቭዬሽን አካዳሚ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ደበበ ስምምንቱ ሁለቱንም ዓየር መንገዶች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ የተፈረመው በቅርቡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በታንዛኒያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ሁለቱ አገራት የገቡትን ስምምነት መሰረት በማድረግ ነው።  ኤፍ ቢ ሲ

READ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ ቁጥር 1 እና 2 ላይ ማሻሻያ ተደረገ... በጋምቤላ የሙርሌ ጎሳ አባላት ያደረሱትን ጥቃት በተመለከተም ኮማንድ ፖስቱ መረጃ ሰጥቷል
Continue Reading

Business

የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያን ተከትሎ በሸቀጦች ላይ የዋጋ መናር እንዳይከሰት ይሰራል – የንግድ ሚኒስቴር

Published

on

የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያን ተከትሎ በሸቀጦች ላይ የዋጋ መናር እንዳይከሰት ይሰራል - የንግድ ሚኒስቴር

የኢትየጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀዛቅዞ የቆየውን የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ገቢን ለማስተካከል የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን በ15 በመቶ እንዲዳከም ወስኖ፤ ብር ከሌሎች ሀገራት መገበያያዎች አንጻር ያለው ምንዛሬም በዚህ መልኩ ተሰልቶ ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል።

ከዚህ ባለፈም ዝቅተኛው የባንክ ተቀማጭ ሂሳብ ወለድ ከ5 ወደ 7 በመቶ ከፍ እንዲል ተደርጓል፤ ከውጭ ምንዛሬ ተመኑ ጋር በተያያዘ ግን የዋጋ ግሽበት ሊከሰት ይችላል የሚሉ ስጋቶች ይደመጣሉ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፈሰር ጣሰው ወልደሀና የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን መዳከም፥ የዋጋ መወደድን ሊያስከትል እንደሚችል ይናገራሉ።

ሌላው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዶክተር ቆስጠንጢኖስም ይህ የምንዛሪ ተመን ማሻሻያ፥ በተለይም ለወር ደመወዝተኛው መጠነኛ የሸቀጦች ውድነትን የማስከተል ባህሪ ይኖረዋል ይላሉ።

የኢፌዴሪ የንግድ ሚኒስቴር ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የንግዱ ማህበረሰብ አላስፈላጊ ጭማሪዎችን እንዳያደርግ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ፥ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ማለትም ዘይት፣ ስኳር እና የዳቦ ስንዴ መንግስት በቂ ድጎማ አድርጎ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገባቸው በመሆኑ እነዚህ የፍጆታ እቃዎች ላይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ከመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ባሻገር የምንዛሪ ተመኑ ተግባራዊ ከተደረገበት ቀን በፊት በገቡ እቃዎች ላይም ማስተካከያውን ተገን አድርጎ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ነው ያሉት።

እስካሁን በአከፋፋዮችም ሆነ በማጠራቀሚ ዲፖዎች የሚገኘው ነዳጅም ባለፈው የውጭ ምንዛሪ ተመን የገባ በመሆኑ፥ የዋጋ ጭማሪ አይደረግበትም።

ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ግን በአዲሱ የውጭ ምንዛሬ ተመን የሚገቡ በመሆናቸው፥ እንደ መሸጫ ዋጋቸው ታይቶ መጠነኛ ማስተካከያ ሊደረግባቸው እንደሚችል ተናግረዋል።

READ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ ቁጥር 1 እና 2 ላይ ማሻሻያ ተደረገ... በጋምቤላ የሙርሌ ጎሳ አባላት ያደረሱትን ጥቃት በተመለከተም ኮማንድ ፖስቱ መረጃ ሰጥቷል

አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎች እንዳይኖሩ በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ስር ያሉ አለ በጅምላ እና የመንግስት ልማት ድርጅቶችን ማስፋት እና ማጠናከርም በሚኒስቴሩ የተያዙ እቅዶች ናቸው።

አስመጭውም ሆነ አከፋፋዩ ለሀገር እና ለህብረተሰቡ በማሰብ ፍትሃዊ የሆነ ንግድ ማካሄድ ይገባዋል ነው ያሉት አቶ ወንድሙ።

ከዚህ ዉጭ ግን አላስፈላጊ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ካሉ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

ለዚህም እንዲያመች በየገበያ ማዕከላት፣ ሱፐር ማርኬት፣ በዋና ማከፋፋያ እና ችርቻሮ ቦታዎች ላይ ድንገተኛ የቁጥጥር ስራዎች ይካሄዳሉ።

በቁጥጥሩ አላግባብ ትርፍ ለማግኘት በሚል ከፍተኛ ጭማሪ ሲያደርጉ የተገኙ ነጋዴዎች ካሉ ግን ይህን ማስተካከል የሚችል፥ እርምጃ ሚኒስቴሩ ለመውሰድ እንደሚገደድም አስረድተዋል።

መንግስት ከሚያደርገው ቁጥጥር ውጭ ሸማቹ ህብረተሰብ የንግድ ስርዓቱን የሚያዛባ ማንኛውንም ድርጊት ከተመለከተ ተገቢውን ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ሚኒስቴሩ ጥሪውን አቅርቧል። ኤፍ ቢ ሲ

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close