Connect with us

Ethiopia

የህዝብ ኃላፊነት ያለበት ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ግጭትን ማስቆም እንጅ ማባባስ የለበትም!

Elias Tesfaye

Published

on

መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተዘጋጀ አጭር መግለጫ

የህዝብ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ያለበት ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ግጭትን ማስቆም እንጅ ማባባስ የለበትም!

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ወቅታዊ ግጭት ለማስቆም እና በሁለቱ ህዝቦች መካከል ለዘመናት የኖረውን መልካም ግንኙነት ወደቀድሞው ለመመለስ መንግሥት እየሠራ ይገኛል።

በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረው ግጭት እንዳይባባስ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅትም ጥረቱ ከግብ ሊደርስ የሚችለው አፍራሽ የሆኑና ህዝብን ጥርጣሬ ላይ የሚጥሉ መረጃዎች መሠራጨታቸው ሲቆም መሆኑን መንግሥት አምኖበት በዚህ ጉዳይ ላይ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል። በዚሁ መሠረትም መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ሚዲያዎች ከአፍራሽ ተግባር እንዲታቀቡ መንግሥት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣንም ግጭቱን ተከትሎ የታዩ አፍራሽ አዝማሚያዎችን መሰረት በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት በላከው ደብዳቤ  ሚዲያዎች ከእንዲህ  ዓይነቱ ተግባር እንዲርቁ አስጠንቅቋል። ከድርጊታቸው የማይታቀቡ አካላት ካሉም ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል። በተለይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ መስከረም 6 ቀን 2010 መግለጫ በሰጡወቅት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ግጭት የሚያባብሱ የመገናኛ ብዙኃን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ይህ የማይሆን ከሆነ መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈው እንደነበር አይዘነጋም

ይህ ሁሉ የሚደረገው ከኢትዮጵያ ህዝቦች መሠረታዊ ጥቅምና ፍላጎት በመነሳት እንደሆነ ዕሙን ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ  ህዝቦችም ሆኑ መንግሥት የሚፈልጉት እናም በትክክልም  የሚበጃቸው ሰላም እንጅ ሁከት አይደለም። አንድነት እንጅ መከፋፈል አይደለም። ፍቅር እንጅ ጥላቻ፣ መተባበር እንጅ መቃቃር፣ መተማመን እንጅ መጠራጠር፣ መከባበር እንጅ መናናቅ አይደለም። ሊሆንም አይችልም። ይህንን የህዝቦች መሠረታዊ ጥቅምና ፍላጎት በሚጻረር መልኩ መረጃ ማሰራጨት የኢትዮጵያ ህዝቦችንና መንግሥትን ፍላጎት በመጻረር የሚፈጸም መሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ድረ-ገፅ እና የቢሮ ሃላፊው ፌስቡክ ገጽ ላይ  ” የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስትና አገር ሽማግሎች በኦሮሚያ ጥቃት ላይ የጋራ አቋም መግለጫ ይፋ አደረጉ” በሚል ርዕስ ማክሰኞ መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም. የተሰራጨው መረጃ መንግሥት ያስቀመጠውን አቅጣጫ የሚቃረን፣ ከኢትዮጵያ ሶማሊ ሰላም ወዳድ ህዝብ እና መንግሥት እንዲሁም የፌዴራል ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ከሚያራምድ ማንኛውም አመራር የማይጠበቅ፣ ለኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሶማሊ ወንድማማች ህዝቦችና ለአገራችን ዘላቂ ሰላምና ልማት የማይጠቅም መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም በተቀመጠው የመንግሥት አቅጣጫ መሠረት የሚመለከተው የመንግሥት አካል ጉዳዩን መርምሮ በቀጣይ ውሳኔ የሚሰጥበትም ይሆናል።

የኮሙዩኒኬሽን እና የሚዲያ አካላት አሁንም ቢሆን ይህን መሰሉን መረጃ ከመልቀቅ እንዲሁም ይህን ለመሳሰሉ ዘገባዎች የአጸፋ ምላሽ ከመስጠት እንዲታቀቡ አሁንም መንግሥት በድጋሚ በጽኑ ለማሳሰብ ይወዳል። የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ሥራዎቻችን ካለባቸው አገራዊ ተልዕኮ እንዲሁም ግጭቱን አስመልክቶ መንግሥት በቅርቡ ከሰጠው አቅጣጫ አንጻር ለሁለቱ ህዝቦች ሰላምና አንድነት በሚጠቅሙ መረጃዎች ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ እና ለተፈጠረው ችግር መቀረፍ የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ መንግሥት በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።  

የአገርን ሰላምና ጸጥታ የሚያደፈርስ ይህን መሰሉ መረጃ በምንም ዓይነት መልኩ የየትኛውንም ክልል መንግሥት፣ አመራር፣ የአገር ሽማግሌዎች ብሎም የየክልሎቹን ህዝቦች ፍላጎት ይወክላል ብሎ መንግሥት በፍጹም አያምንም።  

በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ችግር ቢፈጠር እንኳን በህግና በህግ አግባብ ብቻ መፍታት እየተቻለ በጅምላ በመፈረጅና ጥላቻን በመቀስቀስ ብጥብጥን ለማነሳሳት መሞከር የምንከተለው ሥርዓት ባህርይ እንዳልሆነም ይታወቃል። በግጭቱ ሳቢያ ውድ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን እና በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በተፈናቀሉበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግሥትና መላው ህዝብ እያዘኑና ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ብሎም ግጭቱን ለማስቆም እየተረባረቡ ባሉበት ወቅት የተላለፈው መረጃ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው።

በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 29 ስር ሀሳብን የመግለፅ እና የፕሬስ ነፃነት እና መብቶች የተረጋጡ ሲሆን እነዚህ መብቶች ያለገደብ የሚተገበሩ አይደሉም። በህገ መንግስቱ በአንቀፅ 29/6/ ስር በዋናነት የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስም ለመጠበቅ ሲባል  እንዲሁም የጦርነት ቅስቀሳዎችን እንዲሁም ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በህግ ተከልክለዋል። ህጋዊ ገደቦችን ጥሶ መገኘትም በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ በህገ መንግስቱ በአንቀፅ 29/7/ ስር ተጠቅሷል።

በማንኛውም ዓይነት ሚዲያ የሚቀርቡ መረጃዎች የሰው ልጆችን ስብዕና እና ነጻነት ወይም ስነምግባርን የሚጻረር ወይም የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ፤  በመንግስት ጸጥታ ወይም በህገመንግስቱ መሰረት በተቋቋመ የመንግስት አስተዳደር ወይም በሀገር መከላከያ ሀይል ላይ የወንጀል ድርጊት የሚፈጽም፤  የግለሰብን፣ የብሄር ብሄረሰብን፣ የህዝብን ወይም የድርጅትን ስም የሚያጠፋ ወይም በሀሰት የሚወነጅል፣ ብሔረሰብን ከብሄረሰብ የሚያጋጭ ወይም በህዝቦች መካከል የእርስ በእርስ ግጭትን የሚያነሳሳ፤  ጦርነት የሚቀሰቅስ ይዘት ያላቸውን መረጃዎችን ማስተላለፍ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል በህግ መደንገጉም ይታወቃል።

በመሆኑም እነዚህን መሠረታዊ የከሙዩኒኬሽንና የሚዲያ ህግጋት ድንጋጌዎችና መርሆዎች መተላለፍ የህግ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል በመገንዘብ ማንኛውም የኮሙዩኒኬሽንና የሚዲያ ሥራ ህግና ስነምግባርን የተከተለ እንዲሆን መንግሥት በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን በድጋሚ ያስተላልፋል።

የኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሶማሊ ወንድማማች ህዝቦች አንድነትና ትስስር በማይበጠስ ገመድ የተሳሰረ ነው። አሁን የሚታዩ ጊዜያዊ ግጭቶች የህዝቦቹን የጋራ ጥቅምና ፍላጎት የማይወክሉ በመሆናቸው በራሳቸው በህዝቦቹ እና በመንግሥት የማያቋርጥ የጋራ ጥረት በአጭር ጊዜ ተፈትተው የቀደመው ሰላማዊ ግንኙነት እንደሚመለስ የመንግሥት ጽኑ ዕምነት ነው። 

መስከረም 28 ቀን 2010 ዓ.ም.

READ  ክፈት በለው በሩን...

Elias Tesfaye is an Associate at news.et. ‘Elias is a lawyer by profession and a photographer by training. He believes that the status quo is never good enough and that life is best lived to the fullest.

Continue Reading

Ethiopia

አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

Elias Tesfaye

Published

on

በረከት ስምኦን

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል።
አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ተነግሯል።

አቶ በረከት ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስገባታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ በቢሮአቸው ተገኝተው የነበሩት ሀሙስ ዕለት ነበር።

አቶ በረከት በተመሳሳይ ጊዜ ከሁለት የሃላፊነት ቦታቸው የተነሱ ሲሆን ለሥራ መልቀቃቸው ግልፅ ያለ ምክንያት አልቀረበም።

ነገር ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ብዙም ደስታኛ እንዳልነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።

በተለይ ማዕከሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚያቀርባቸው ሃገር አቀፍ የፖሊሲና የአስተዳደር ጥናቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩና በመንግሥት ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ብዙም ተቀባይነት አግኝተው ተግባራዊ አለመደረጋቸው ለቅሬታቸው ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። More Here

READ  በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩት የኢትዮ ቴሌኮም ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ዋስትና ተፈቀደላቸው
Continue Reading

Ethiopia

ጠ/ ሚኒስትሩ ለኢቢሲ ሠራተኞች በልዩ ሁኔታ ቤት ለመስጠት ቃል ገቡ

Published

on

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

የኢትዮጵ ያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኢቢሲ) ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበት መንገድ በልዩ ሁኔታ እንደሚታይ፣ የባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት ድርጅቱ የውስጥ አሠራሩን እንዲያሻሽል ጠ/ ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ መምከራቸው ተሰማ።

ጠ/ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኢቢሲ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር ነው።
መንግሥታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በትላንት ዕትሙ የኢቢሲ ሠራተኞች ያለባቸውን የቤት ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት ሠራተኛው በልዩ ሁኔታ ቤት የሚያገኙበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉ ጠ/ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ጵፏል።
የመንግሥት ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ለመቅረፍ ኢቢሲ አሠራሩንእንዲያሻሽልና ልማታዊ ጋዜጠኝነትን እንዲተገብር የመከሩት አቶ ሀይለማርያም ልማታዊ ጋዜጠኝነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁለተኛ ድግሪ የሚሰጥበት መንገድ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል። DIRETUBE

READ  የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት 7 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ አሳየ
Continue Reading

Ethiopia

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

FanaBC

Published

on

By

ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት እና በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዶክተር መረራ “ድርጊቱን አልፈፀምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” ብለው የዕምነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፥ ጠበቃቸው 11 ወር ቆይተው ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸው እንደዘገየ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

በከፊል የሚቀርቡ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞች እንዲጠይቋቸው ችሎቱን የጠየቁ ሲሆን፥ ችሎቱም ይህን ጥያቄያቸውን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ አዟል።

ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር በይፋ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይም ዛሬ ብይን ሰጥቷል።

በህገመንግስቱ አንቀፅ 20 ንዑስ ከቁጥር 4 ጋር ይጋጫል ወይስ አይጋጭም በሚለው ላይ ህገመንግስታዊ ትርጉም ማስፈለጉ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከህገመንግስቱ አንፃር እንደማይጋጭ ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ ነው ችሎቱ የምስክሮች ስም ዝርዝር ሳይሰጥ የአቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ ብይን የሰጠው።

እነዚህን መስክሮች ከጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ።

ፍርድ ቤቱ ከዶክተር መረራ ጋር የተከሰሱ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይም አዟል። ኤፍ ቢ ሲ 

READ  የህዝቡን መሪ መስደብ ህዝቡን መስደብ ነው
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!