Connect with us

Art and Culture

የወደቀ አንሱ ለባለቤቱም መልሱ | በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቆየት ባለ ጊዜ የተቀበረ ነው የተባለ 2 በርሜል ወርቅ ተገኝቷል…

Published

on

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቆየት ባለ ጊዜ የተቀበረ ነው የተባለ 2 በርሜል ወርቅ ተገኝቷል

የወደቀ አንሱ ለባለቤቱም መልሱ | ኪዳኔ መካሻ በድሬቲዩብ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ ቆየት ባለ ጊዜ የተቀበረ ነው የተባለ 2 በርሜል ወርቅ ተገኝቷል ተብሏል፡፡

መስከረም 1/2010 በባንባሲ ሾንጋ በተባለ ወንዝ ዳርቻ በአካባቢው ነዋሪዎች ተገኘ የተባለው ወርቅ በክልሉ ፖሊስ ጥበቃ እየተደረገለት ነው መባሉንም ከማስታወቂያ ቢሮው ሰምተናል፡

በተለያየ አጋጣሚ እቃ ጥለህ ታውቃለህ? የወደቀስ ነገር ስታገኝ ምን አደረክ? የወንጀል እና የፍትሀ ብሔር ሕጋችን በጉዳዩ ላይ ምን እንደሚሉ እስቲ እናውራው።

የወደቀ ነገር ስታገኝ አንሳው።በድንገተኛ አደጋ ፣በስህተት ወይም ከባለቤቱ ፍቃድ ውጭ በሆነ ምክንያት ከጁ ከወጣ(አውቆ ስላልፈለገው የጣለው ካልሆነ በቀር) እና አንተ እጅ ከገባ ‘‘የማን ነው?’’ ብለህ ባለቤቱን ለማወቅ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ አለብህ። የማን እንደሆነ ማወቅ ካልቻልክ ለፖሊስ ወይም ባካባቢው ላለ የአስተዳደር አካል እቃውን ማግኘትህን ማሳወቅ ግዴታህ ነው። ምክንያቱም ባንተ እጅ ይግባ እንጂ ያንተ አይደለም።

ይህን ግዴታህን ከተወጣህ ባለቤቱ እስኪገኝ እቃውን  በጅህ የማቆየት መብቱ አለህ። በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1155 መሰረት በእጅህ እስካለ  ለእቃው ተገቢውን ጥበቃ በማረግ ተጠንቅቀህ የመያዝ ግዴታ አለብህ።

የእቃው ባለሀብት ሲመጣ ትመልሳለህ።ባለቤቱም እቃውን ለማቆየት ያወጣከው ወጪና ኪሳራ ከምስጋና ጋር የመክፈል ግዴታ አለበት።

ተጨማሪ የወሮታ ክፍያ ወይም ጉርሻ እንዲከፈልህ መጠየቅም ትችላለህ።  ዳኛው ጉርሻ ያስፈልግሀል ወይ ምን ያህል ይሁንልህ የሚለውን ሚወስኑት ያንተን ያግኚውንና እቃው የጠፋበትን ሰው ሀብትና ባለቤቱ እቃውን በራሱ ለማግኘት የነበረውን እድል በማመዛዘን ነው። አዎ ጉርሻ ያስፈልግሀል ብለው ካመኑበት ዳኛው የእቃው ዋጋ እስከ 25 በመቶ እንዲከፈልህ ያዙልሀል። ጉርሻ የመጠየቅ መብት ያለህ እቃውን ከመለስክበት ቀን እስከ አንድ አመት ብቻ ነው።

ድንገት ግቢህ ውስጥ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረትህ ውስጥ የተቀበረ ወይም የተደበቀ ገንዘብ ቢገኝስ? የኔ ነው የሚል ማስረጃ ማቅረብ ማይችልበት ከሆነና ከሀምሳ አመት ለማያንስ ጊዜ ተቀብሮ ወይም ተደብቆ የቆየ የሚመስል ከሆነ እንኳን ደስ አለህ!!

አንተና መንግስት ሀብቱን እኩል ትካፈላላችሁ ። የተገኘው ነገር ቅርስ  ከሆነ ደግሞ  በአዋጅ ቁጥር 209/1992 መሰረት ለቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ማሳወቅ ግዴታህ ነው። ሽልማትና እውቅና ይሰጥሀል።

ሆኖም ለራስህ ወይም ሌላ ሰው የማይገባውን ጥቅም ለማስገኘት አስበህ  አግኝተህ ከደበከው፣ ለራስህ ከወሰድክ  ወይም ለሌላ ሰው ከሰጠህ በወንጀል ትቀጣለህ።
የሌላ ሰው እንስሳ እንኳን ሸስቶ ቤትህ ቢገባ ለባለቤቱ ለማሳወቅ ሳትጥር ወይም ለፖሊስ ወይም ለቀበሌ ሳታሳውቅ የራስህ ካረከው ጥፋት ነውና በወንጀል ሕጋችን አንቀፅ 679 ባለመብቱ ክስ ካቀረበብህ በቀላል እስር( ካስር ቀን እስከ ሶስት አመት የሚደርስ) ወይም በመቀጮ(ከአስር ብር እስከ አስር ሺ ብር) ትቀጣለህ።

የጠፋ እቃ አግኝተህም ለባለቤቱ ለማሳወቅ ወይም ለሚመለከተው አካል ሳታሳውቅ ለራስህ ካረከው  የንብረቱ ባለቤት ክስ ሲያቀርብ ከአምስት ሺ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም እስከ አንድ አመት ቀላል እስር ያስቀጣል።

የተቀበረ ንብረት ስታገኝም ለመንግስት ወይም ንብረቱ ተቀብሮ ለተገኘበት ባለቤት ተገቢውን ክፍያ ሳትሰጥ የራስህ ካደረከው ቅጣቱ ተመሳሳይ ነው።

ለማንኛውም የወደቀ ስናገኝ እናንሳውና የማነው ብለን እንጠይቅ ።ባለቤቱ ካልታወቀ ለፖሊስ ወይም ለሚመለከተው የመንግስት አካል እናሳውቅ።ያስመሰግናል ያሸልማል። ይህን ሳናረግ ያገኘነውን ከወሰድነው ግን በወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል ልብ እንበል። DIRETUBE

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close