Connect with us

Business

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የዓለም አቀፍ ሽልማት ተረከበች

Published

on

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የዓለም አቀፍ ሽልማት ተረከበች

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሽልማት ተረከበች።

ሽልማቱ በረሃማነትን እና የመሬት መሸርሸርን በተሳካ ሁኔታ የሚከላከሉ ህጎችን እና አሰራሮችን አውጥቶ ተግባር ላይ በማዋል ውጤታማ ለሆኑ ሀገራት የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ዓላማውም በረሃማነትን ለመከላከል እና ውጤታማ ዘዴዎችን ለማጠናከር ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በረሃማነትን መዋጋት አካባቢን ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ መረጋጋት ትልቅ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።

በዚህ ተግባር የላቀ ውጤት ያስመዘገበው የትግራይ ክልልም ሽልማቱን ተረክቧል።

ክልሉም በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እና የወጣት ተሳትፎ ጥምረት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ መጠን መሬት መልሶ የማልማት ስራ በመስራት ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል።

በውጤቱም የአፈር መሸርሸር በእጅጉ በመቀነሱ፣ የከርሰ ምድር ውኃ በመጨመር፣ ዘላቂ የግብርና ልምዶችን በማጠናከር፣ በምግብ እህል ራስን በመቻል እና የኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል ተብሏል።

ሽልማቱ የተሰጠው መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም የምርጥ ፖሊሲ ሽልማት በዓል አስመልክቶ በቻይና በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የልማት ኮንፈረንስ 13ኛ ስብሰባ ላይ መሆኑ ተነግሯል። ኤፍ.ቢ.ሲ

READ  ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በየመንና በጂቡቲ ችግር ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን እንዲመለሱ አደረገ
Continue Reading

Business

የአገልግሎት ቀኑን አራዝሜዋለሁ ብሎ መብታችንን ያሳጠረው ኢትዮ ቴሌ ኮም

Published

on

የአገልግሎት ቀኑን አራዝሜዋለሁ ብሎ መብታችንን ያሳጠረው ኢትዮ ቴሌ ኮም

የአገልግሎት ቀኑን አራዝሜዋለሁ ብሎ መብታችንን ያሳጠረው ኢትዮ ቴሌ ኮም እስከ መስከረም 14 ቢባልም ቁጥር የሌላቸው ሞባይሎች በተሰጠው ቀነ ገደብ ተጠቅመው አልተሳካላቸውም፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ

ኢትዮ-ቴሌ ኮም የስልክ ቀፎአችንን ልመዝገብ ብሎ ሲያውጅ ጉዳዩ ብዙም አልገባን ነበር፡፡ አንዲት ጓደኛዬ ደውላ እስክታስረዳኝ እና ባታስመዘግቢ ይዘጋል እስክትለኝ መልዕክቱ በደንብ አልገባኝም ነበር፡፡ ያው አሁን በስራ ላይ ያሉ ስልኮች በሙሉ በአሉበት ተመዝግበዋል ተባልን፡፡

ለካ የተቀመጠ፣ ሱቅ የተደረደረ፣ ስጦታ መጥቶ ቻርጀር የጠፋለት ብዙ ብዙ ዓይነት ሞባይል ቀፎ የተባለው ካልተደረገ እንደሌለ ይቆጠራል፡፡ ይሄ ሲሰማ ሰው እንዴት ነው ብሎ መጠየቅ ጀመረ፡፡

ቴሌም በተገልጋዩ በቀረበው ጥያቄ መሰረት እስከ መስከረም 17 ቀን ተራዝሟል ሲል ማስታወቂያ ለቀቀ፡፡ አሁን ብዙ ሰዎችን ያሳዘነው በማስታወቂያው መሰረት እስከ ቀኑ እድላቸውን ለሞመከር ሲጥሩ ቀፎው መዘጋቱና አገልግሎት ለመስጠት አለመቻሉ ነው፡፡

ከተባለው ቀነ ገደብ በፊት የልቡን ያደረሰው ቴሌ ቃሉን ይጠብቃል ብለው ያመኑት ሜዳ ላይ ቀርተዋል፡፡ ምናልባት ሲስተም አሊያም ሌላ ምክንያት ወይም ቃሌን ለምን አከብራለሁ፡፡
ጎን ለጎን የቆመ ሰው ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው ስል ኖሬስ የለም ውሸት ምኑ ያስፈራል አይነትም ይሆናል፡፡

በርካታ የሞባይል ቀፎ ነጋዴዎች ጉዳዩ አሳዝኖአቸዋል፡፡ አሁን ገና ሀዘን ላይ ናቸው፡፡ ከዚያ ደግሞ ኪሳር አለ፡፡ እንዲህ ለምን እንደሆነ ምላሽ የሚሰጣቸው እንኳን አላገኙም፡፡ ግን ሆኗል፡፡

ኢትዮ ቴሌ ኮም ቃል በገባው መሰረት አራዘምኩ ባለው ቀን ድረስ ምዝገባውን አላራዘመውም፡፡ ቀጣይ የሚሆነውን አብረን እናያለን፡፡

ሚሊዮኖች ይከስሩና አንጋፋው አትራፊ ድርጅት በትርፋማነቱ ቀጥሏል የሚለውን ዜና እናነብ ይሆናል፡፡ በበኩል አንድ ነገር ቢደረግ ደስ ይለኛል፡፡ ጉዳዮን ኢትዮ ቴሌ ኮም መልሶ ቢመለከተው እና እውን የተባለው ችግር ዝም ተብሎ የሚታለፍ ነው ብሎ ራሱን ቢጠይቅ፡፡ DIRETUBE

READ  የማይጠቅም ማህበረሰብ ሲፈጠርና፤ የሰው ልጅ ምድራዊ ፋይዳ ሲያበቃ

Continue Reading

Business

ጠቃሚ መረጃ ስለአዲሱ ሞባይል ምዝገባ | (አዲሱ ሲስተም) አሰራር የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

Published

on

ጠቃሚ መረጃ ስለአዲሱ ሞባይል ምዝገባ

1. የምዝገባው ጊዜ አልፎብኛል እስካሁን ያልተጠቀምኩበትን ቀፎ እንዴት ወደ አገልግሎት ማስገባት እችላለሁ ?

መልስ:- የተሰጠው የምዝገባ የጊዜ ገደብ በማለፉ ሲስተሙ ተግባራዊ ሆኗል በመሆኑም ከዚህ በኋላ ደንበኞችም ሆኑ በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪዎች፤ ሻጮች እና አከፋፋዮች በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ምዝገባ መመሪያ አንቀፅ ስድስት ስለ መሣሪያዎች ምዝገባ እንደሚከተለው ይስተናገዳሉ፤ በመሆኑም ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ አሰራር ውስጥ ፍቃድ ሰጪ መስሪያ ቤቶች በሚኒስቴር መ/ቤቱ ካልተፈቀደ ወይም በጉምሩክ የመቅረጫ ጣቢያዎች ካልተመዘገበ በስተቀር ማንኛውም የሞባይል ስልክ ቀፎ በጥቁር መዝገብ ላይ እንደተመዘገበ ይቆጠራል፡፡

1. አስመጪዎች ወይም አምራቾች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ወይም የተመረቱ/የተገጣጠሙ የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን ለሚኒስቴሩ በማመልከት ማስመዝገብ አለባቸው፡፡

2. ከውጪ ሀገር በግለሰብ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ የሞባይል ስልክ ቀፎ በጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያዎች መመዝገብ አለበት፡፡

3. ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ወይም የተመረቱ/የተገጣጠሙ የሞባይል ስልክ ቀፎ ምዝገባ ማከናወን የሚችሉት ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ሂደት ላይ እያሉ ወይም የማምረት/የመገጣጠም ሥራው ሲጠናቀቅ ብቻ ነው፡፡

4. የምዝገባ ሥርዓቱ የ IMEI ቁጥራቸው በጥቁር መዝገብ የተመዘገበ ካልሆነ በስተቀር የሮሚንግ አገልግሎት ስምምነት ባላቸው ግለሰቦች ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

5. ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ወይም በሀገር ውስጥ የተመረቱ/የተገጣጠሙ የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን ለማስመዝገብ ሲያመለክቱ የሚከተሉትን ሰነዶች ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ሀ/. የሞባይል ስልክ ቀፎዎቹ የገቡበትን ወይም የተመረቱበትን/የተገጣጠሙበትን ቀን፣ የመሣሪያዎቹን ስሪት፣ ሞዴል እና ብዛት የጠቀሰ እንዲሁም ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት የማመልከቻ ደብዳቤ፣
ለ/ የንግድ ፈቃድ
ሐ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
መ/ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን፣
ሠ/ የኤርዌይ ቢል ወይም የማስጫኛ ሰነድ፣
ረ/ የተመረተበት ሀገር ሠርተፊኬት፣
ሰ/ ኮሜርሻል ኢንቮይስ፣
ሸ/ ፓኪንግ ሊስት፣
ቀ/ የመሣሪያ ምዝገባ ስርዓቱ በሚቀበለው የኖትፓድ ፋይል ፎርማት መሠረት የተዘጋጀ የ IMEI ቁጥሮች ዝርዝር የያዘ CD ወይም ፍላሽ ዲስክ፣

READ  አንድ ሙሉ ቀን እንዴት ከሀገር ጥላ ጋር!!

6. በሚኒስቴር መ/ቤቱ ካልተፈቀደ ወይም በጉምሩክ የመቅረጫ ጣቢያዎች ካልተመዘገበ በስተቀር ማንኛውም የሞባይል ስልክ ቀፎ በጥቁር መዝገብ ላይ እንደተመዘገበ ይቆጠራል፡፡

ጥያቄ:- በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡና በአከፋፋዮች መጋዘን ወይም በችርቻሮ መሸጫ መደብሮች የሚገኙ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች እንዴት ይስተናገዳሉ?
መልስ:- በመመሪያው መሠረት በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡና በአከፋፋዮች መጋዘን ወይም በችርቻሮ መሸጫ መደብሮች የሚገኙ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች የ IMEI ቁጥራቸው ተመሳስሎ ያልተሰራ፣ ያልተባዛ ወይም ትክክለኛ ሆኖ ከተገኘ በነጭ መዝገብ ይመዘገባሉ፡፡ አከፋፋዮች ወይንም ቸርቻሪዎች ግዚ በፈጸሙባቸው ህጋዊ አስመጪዎች ወይም አምራቾች በኩል ጥያቄያቸውን ለፈቃድ ሰጪ መስሪያ ቤቶች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን እና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን ማነጋገር ይችላሉ፡፡

ጥያቄ:- የሞባይል ቀፎ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች በሱቃችን ያሉ አዳዲስ ቀፎዎች የወደፊት እጣ ፋንታ ምንድነው?
መልስ:- ከላይ በተመለከተው መመሪያ መሠረት ያለህጋዊ አሰራር በሚኒስቴር መ/ቤቱ ካልተፈቀደ ወይም በጉምሩክ የመቅረጫ ጣቢያዎች ካልተመዘገበ በስተቀር ማንኛውም የሞባይል ስልክ ቀፎ በጥቁር መዝገብ ላይ እንደተመዘገበ ይቆጠራል፡፡ ስለሆነም ከነዚህ ተቋማት በህጋዊ አሠራሩ መሠረት መስተናገድ ይችላሉ

ጥያቄ:- አዲስ ቀፎ መግዛት የሚፈልጉ ደንበኞች ቀፎው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ ይችላሉ?
መልስ:- አዲስ የሞባይል ቀፎ ወይም ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች ሲገዙ በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ለማወቅ :-
· ሲም ካርድ አስገብተው ለሙከራ መጠቀም
· *868# ደውለው 3ኛ ቁጥር ላይ የሚገኘውን የመለያ ቁጥር ሁኔታ ማወቂያ (Check Status) የሚለውን መምረጥ ፤ በመቀጠል by IMEI የሚለውን መርጠው፤ ሊገዙ ያሰቡትን የቀፎ መለያ ቁጥር /IMEI/ አስገብተው ቀፎው በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
· የሚገዙትን ቀፎ የIMEI ቁጥር ለማወቅ፡
· *#06# ይደውሉ
· ከቀፎው ማሸጊያ ካርቶን ላይ ይመልከቱ፡፡
እዚህ ላይ የሚታዩ ስታተሶች
· የተሳሰረ/Locked – ከዚህ ቀደም ተመዝግበው አገልግሎት ላይ ያሉ ሁሉም የሞባይል ዲቫይሶች ሎክድ የሚል ስታተስ ያሳያሉ ይህም አሁን የሚገለገሉበት ሲም ካርድ እና ቀፎ መተሳሰሩን ያሳያል፡፡
· ያልተሳሰረ/Un-Locked – ቀፎው አሁን ካለበት ሲም ካርድ ጋር ያልተሳሰረ እና ሌላ ሲም ካርድ መቀበል የሚችል
· የተፈቀደ/Autorized – መመሪያውን ተከትለው ፈቃድ ያገኙ ቀፎዎች ሆነው በማንኛውም ሲም ካርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ የሆኑ
· ያልተፈቀደ/Unautorized – ፈቃድ ያላገኙ አና የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ላይ መስራት የማይችሉ ቀፎዎች

READ  የማይጠቅም ማህበረሰብ ሲፈጠርና፤ የሰው ልጅ ምድራዊ ፋይዳ ሲያበቃ

5. የሞባይል ቀፎዬን ወደሌላ ለማዛወር (ሌላ ሲም ካርድ ለመጠቀም) ምን ማድረግ አለብኝ?
አማራጭ 1
· ደንበኞች በቀላሉ ስልካቸውን በማጥፋት ወይም ስዊች ኦፍ በማድረግ ሌላ ሲም ካርድ አስገብተው መጠቀም ይችላሉ
አማራጭ 2
· በ USSD *868# በመደወል (በ5 ቋንቋዎች በአማርኛ እንግሊዝኛ ትግርኛ ኦሮምኛ እና ሶማልኛ) አገልግሎት ይሰጣል
· Unlock/ ቀፎ ነጻ ማድረግ የሚለውን በመምረጥ ማላቀቅ እና በሌላ ሲም ካርድ መጠቀም ይችላሉ
· በአጭር የጽሁፍ መልእክት ወደ 868 A ወይም ባዶ መልእክት በመጻፍ መላክ
ሆኖምተመሳስለው የተሰሩ፣ የተባዙ ወይም ትክክለኛ ያልሆነ የ IMEI ቁጥሮች ያላቸው የሞባይል ስልክ ቀፎዎች አሁን ባለበት ሲም ካርድ ብቻ መስራት ይችላሉ (ሌላ ሲም ካርድ መቀበል አይችሉም)

6. ተመሳስለው የተሰሩ/የተዳቀሉ ቀፎዎች ቀጣይ እጣፈንታ ምንድነው?
· ተመሳስለው የተሰሩ፣ የተባዙ ወይም ትክክለኛ ያልሆነ የ IMEI ቁጥሮች ያላቸው የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ይህ መመሪያ ከጸናበት ዕለት ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በትክክለኛ የሞባይል ስልክ ቀፎዎች መተካት ይኖርባቸዋል።

ምንጭ:- ኢትዮ ቴሌኮም

Continue Reading

Business

የትምህርት ኢንቨስትመንት- ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ማጅራትን የመምታት ስልት

Published

on

የትምህርት ኢንቨስትመንት- ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ማጅራትን የመምታት ስልት

የትምህርት ኢንቨስትመንት- ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ማጅራትን የመምታት ስልት፤ ያው ጥራት የለም፣ ገንዘብ መቆጠብ የለም፡፡

ከስናፍቅሽ አዲስ

ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ ጀመሩ፡፡ ሊማሩ ከማለት ብር ሊያጠፉ የሚለው አይቀልም ብላችሁ ነው፡፡ የትምህርት ጉዳይ ፈተና ሆነብን፡፡

ይኼው በቅርቡ በአዲስ አበባ በተደረገ የመምህራን ምዘና ሃያ በመቶው እንኳን ማለፍ አቃታቸው ተባልን፡፡ እና ማን እያስተማረ ነው የመምህር ፍልሰት እየተባለ ዋጋው ጣራ የነካው?

የትምህርት ኢንቨስትመንት በመንግስታችን በበጎ መታየቱ ዜጎች የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ ነበር፡፡ ግን እኛ ጋር የደረሰው በየዓመቱ እንደ አርባ ስድሳ ተመዝጋቢ ብር ጨምሩ የሚለው ማቆሚያ የሌለው ዋጋ ጭማሪ ነው፡፡

በእርግጥ ብዙሃኑ የትምህርቱ መስክ ባለሃብቶች አንጀታቸው ድርብ ነው፡፡ አይሳሱም፡፡ የትም አይሄድም የተባለው ወላጅ መስከረም ሲጠባ ገንዘብ እንደሚጨምር ራሱን አሳምኖ እንዲኖር አድርገውታል፡፡

የኔ ሀሳብ መንግስት በትምህርት መስክ ለሚሰማሩ የውጪ ባለ ሀብቶች በተለይም ለህንዳውያን በሩን ከፍቶ የላቀ ማበረታቻ ቢሰጥ አሁን ካለው አሰቃቂ አደጋ የሚታደገን ይመስለኛል፡፡

አሁን ትምህርት ቤት የሚመዘገበው ወላጅ ነው፡፡ የሚወዳደረው ወላጅ ነው የሚል እምነት ያላቸው ሰዎች ተበራክተዋል፡፡

ዋጋው በጨመረ ትምህርት ቤት ማስተማር የደረጃ መገለጫ ተደርጎ እንዲወሰድ ለማድረግ በሚጥሩ ጥቂት ሰዎች ሳቢያ ህዝበ አዳም በልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ ሲያለቅስ ይኖራል፡፡

አንዳንዶች ዋጋም ቆልለው ትርፉ ሱስ ማልመድ ሆኖ በሰላም ከቤት የወጣው ልጅ ስለ ሀሺሽ ተምሮ ለሚመለስበት ዋናው ጥራት ነው እያሉ የተፈቀደ የማጅራት መቺነት ስልትን የተከተሉ ይመስለኛል፡፡

የኔታ በ50 ሣንቲም ፊደል ሲያስቆጥሩ የኖሩት ሀገር ለመገንባት ነው፡፡ ቤት እና ተማሪ ቤት አንድ ሰው አእምሮው በስጋት እንዲወጥ ያደረጉ የከተሜ ነዋሪዎች አበሳ ናቸው፡፡

READ  የዶክተሮች ዓመት-ከምሁራን እፍ ያለው አዲሱ የፓለቲካችን ፍቅር

የኔታ ስለ ሀገር ግንባታ ያሰቡትን ያህል ማሰብ ያቃተው ኢንቨስትመንት ማንም ቢጮህ መስሚያ የለውም፡፡

እናም አዲስ አመት አዲስ የክፍያ ጭማሪ ግድ እየሆነ መጣ፡፡ ግዴታው በሰኔ ለመንግስት የመገበር ያህል የሚስማማበት ሰው ቁጥር በዝቶ ተቀባይነትን አገኘ፡፡

የት ድረስ እንደሚቀጥል እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ የመንግስት ሰራተኛው ልጁን መካከለኛ በሚባሉ የግል ትምህርት ቤቶች እንኳን ማስተማር አልቻለም፡፡

መንግስት ለትምህርት ዘርፍ ሰጠሁ የሚለው ማበረታቻ ለጥቂቶች ሀብት ማካበቻ እስኪሆን የብዙሃኑን ሰቀቀን አልታደገም፡፡ በዚህ ስሜት ውስጥ ይሄው መስከረም አዲሱ የትምህርት ዘመን ጀመረ፡፡ ልጅ ክፍል እየቆጠረ፤ ትምህርት ቤቱ ደግሞ ገንዘብ….

DIRETUBE

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close