Connect with us

Art and Culture

ዝቅ ብለን ከፍ ያሉበት ብዙ ያባባለን ቀንም አለፈ

Published

on

ዝቅ ብለን ከፍ ያሉበት ብዙ ያባባለን ቀንም አለፈ

ዝቅ ብለን ከፍ ያሉበት ብዙ ያባባለን ቀንም አለፈ፡፡ እነሆ ሌላ ቀንም ሆነ፡፡ “እንዲህ ልጠግብ በሬዬን አረድኩት አለ፤” ያገሬ ሰው፡፡
(ስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ)

ዛሬ በዓል አይደለም፡፡ ዛሬ የበዓል ማግስት ነው፡፡ ዛሬ የአዲስ አመት ነገ ነው፡፡ መስከረም አንድን ለመቀበል ነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ የከፍታ ዘመን ይሆናል በሚል መንግሥታዊ አዋጅ ድግሥ ደግሠን ነበር፡፡

ድግሱ ብዙውን ሰው ኡኡ አስብሎም ከርመናል፡፡ የተጮኽው ለድግሱ አጋፋሪዎች ሲጀመር ያለ ጨረታ፤ ሲቀጥል ተገቢ ያልሆነ ክፍያ ተከፈለ ተብሎ ነው፡፡ በዚህ ኡኡታ ውስጥ ደግሞ ሂልተን የሚዘጋጅ የሙዚቃ አልበም ምረቃ ፍቃድ የለውም በሚል ተሰረዘና ብዙ ያባባለን ዋዜማ ሆነ፡፡

ሀገራችን ከፍ ማለቷን የሚጠላ አለ ብዬ አላስብም፡፡ በባነሯ ብዛት ከፍ ያለች ሀገር ባትኖርም፤ በቆንጃጅት አጀብ ድህነትን ያሸነፈች ደሀ ሀገር አይተን ባናውቅም፤ ከዚህ በላይ ማሰብ ፍዳ በሆነባቸው ሰዎች የተነደፈውን ሀሳብ የሚቃወመው ሰው መነሻ ግን እኛን ዝቅ አድርጎ ግለሰብ ከፍ የሚያደርግ ሀሳብ ነው የሚል ይዘት ነበረው፡፡

ዛሬ ሌላ ቀን ነው፡፡ መንግስታችን በኦዲት የመንግስትን ካዝና እና ሰነድ ፈትሾ ይሄ ጎድሏል እንደሚለው ሁሉ በብር ሃይል የሚከናወኑ ኩነቶች ከዝግጅቱ በኋላ ያመጡትን ፋይዳ መርምሮ ኪሳራ ያደረሰውን ልሰር ቢል የገለብ በረሃም እስር ቤት ሆኖ በጠበበ፡፡

ለማንኛውም የዝግጅቱን ይዘትና ታላቅነት አየንና ዶክተር ለሚኒስትርነት የሚመርጠው መንግስት እንዲህ ላሉ ዝግጅቶች ያልተማሩ ፕሮሞተሮዎችን ለምን እንደሚፈልግ እራሳችንን ጠየቅን፡፡
ዛሬ መንግስት እንዲህ የሚል ይመስለኛል፡፡ እንዲህ ልጠግብ በሬዬን አረድኩት፡፡ የህዝብ ቀልብ ከእርሻ በሬ ይበልጣል፡፡ በጉዳዩ ያልተንጫጫ አልነበረም፡፡

የመንግስት ደጋፊ ነን የሚሉ ብሎገሮች ሳይቀር ሥርዓት የጣሰ አሰራር አይተናል ብለው ሂደቱን ኮንነው ነበር፡፡ የመታጋገል ባህል የሌላቸው የዩኒቨርሲቲ ምሁራንን እንዲህ ባለው ቦታ መሾም አበሳው የት ድረስ እንደሆነ ያየንበትም ነው፡፡ ምላሹ ስላቅ እና ጥላቻ ነበርና፡፡

READ  የቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዚዳንት ያህያ ጃሜህ ከሀገር ለቀው ከወጡ በኋላ 11 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከካዝና መጉደሉተሰማ

እዚህም እዚያም የተደመጡ ኡኡታዎች ከእርሻ በሬ በላይ ነበሩ፡፡ መስከረም ሁለት ሲሆን ይሄ ሁሉ ለምን አስብሎ የሚያስቆጭ ድርጊት እንደተፈጸመ ይሰማኛል፡፡ እናም መንግስት ሊጠግብ ነገር የእርሻ በሬውን አርዷል፡፡

ነገ ከነገወዲያ ዝም ያለው የብሔራዊ ቲያትር እና የእነ አርቲስት ዳንኤል ተገኘ የተቀማ ምኞት ይፋ ይሆናል፡፡

ነገ ከነገ ወዲያ በሰነድ ቀርቦ የተዘረፈው የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የንባብ ቀን ሀሳብ ብዙ ያነጋግረናል፡፡

ነገ ከነገ ወዲያ በመንግስት ማህተም የተለመነ ብር በመንግስት ስም የተሰበሰበ ገንዘብ ከገንዘብ ሚኒስትር እስከአልወጣ ድረስ የመንግስት መመሪያ

አያስፈልገውም የሚለው የሌቦች እሳቤ ፍርድ ቤት ቆሞ ዜና ሲሆን እናደምጣለን፡፡ DIRETUBE

 

Continue Reading

Art and Culture

ነይ የኔ ደመራ! | ሚካኤል አስጨናቂ

Published

on

ነይ የኔ ደመራ!

ሀበሻዎች ግን ጥሩ ብርቃሞች እኮ ነን ! ስልክ ሲገባ ፥ መኪና ሲገባ ፥ ጢያራ ሲገባ ፥ ወፍጮ ሲገባ ፥ ለሁሉም አጀብ አጀብ ብለናል።

ስልክን የሰይጣን ድምጥ የሚያስተጋባ እርኩስ እቃ ፥ መኪናን ነፍስ ያላት ቆርቆሮ (ቁርጥ ግልገል መሳይ ) ፥ ወፍጮን ደግሞ የእህል ሰላቢ አድርገን ቆጥረንም እናውቅ ነበር።
ያኔ ደግሞ ፍርኖ ዱቄት ሀገራችን የገባ ጊዜ ልጆቻችንን ሁሉ ሳይቀር ፉርኖ ብለን በዱቄት ስያሜም ጠርተን እናውቃለን (እዚህ ጋር እየሳኩኝ መሆኑ ይታወቅልኝ ) ፥
ይህም ሁሉ ሆኖ እኔን ግን ክፍት ያለኝ ነገር ቢኖር ገኒዬን ከኔ ለመንጠቅ የሚሯሯጠው ያ ትዕቢተኛ የሰፈራችን ልጅ ስሙ መብራቱ ቦጋለ ሆኖ መቅረቱ ነው! እንደምን ቢሉ አንድም ያኔ ድሮ ገና መብራት ተኸተማችን የገባ ጊዜ አባቱ ከኩራዝ መላቀቅ ብርቅ ሆኖባቸው ስም ጥለውበት ፥ ሌላው ደግሞ አንድዬ የሰው መዛበቻ ሁን ሲለው!
.
በመሰረቱ የመብራቱ ፀባይ ለያዥና ለገናዥ የሚያስቸግር ፥ እንደስሙ ብርሀናማ ሳይሆን ጨለምተኛና የደንቃራ ስራን የሚያዘወትር በምስለት ደረጃ ለኔ የጋኔንን ያህል የሚፀልምብኝ ልጅ ነው። በሰፈሩ ሁሉም ሰው ሰላም አውርዶ ከቤቱ ባይወጣ ቢቀር እንኳ ሌላ ሰፈር ሆነ ብሎ ሄዶ ነገርና ጠብ ይፈልጋል! አዎን ፥ ከሲጃራ ከጫትና ከሴስ ሱስ የማይተናነስ ደባል ሱስ ያየሁት በመብራቱ ነው።

እንደው ባባቱ ዘመን አንድም ብልህና ትንቢተኛ ሰው ጠፋ እንጂ ለዚህ ልጅ ቤተሰቦቹ ስያሜ ሲሰጡት መብራቱን አጠፋ፥ ብርሀን ንሳቸው ፥ ፀሊሙ ጋረደው ቢሆን እንደሚመረጥ ሰው መጠቆም ነበረበት እላለሁ!
.
ለነገሩ እኔ ስለሰው ምን አገባኝ? ከዚህ ሁሉ የስም ጋጋታና ውጣ ውረድ ይልቅ ይህን ልጅ ኤልፓ ብለው ሁሉን ገላጭ ስያሜ እንደሰጠሁት አስባለሁ ፥ ምህ እንደምን አላችሁኝ ልበል? ኤልፓ በያንዳንዱ ቀናቶች ብቻ ሳይሆን በዓልን እንኳ መታገስ አቅቶት ብርሀን ሲነሳን ስላየሁ ብዬ እመልስላቹሀለሁ!

READ  ፍላጎትና አቅርቦቱ የተራራቀው የቤት ልማት ፕሮግራም

ይህም የሆነው በአዲሱ ዓመት መግቢያ ቀናችን መስከረም አንድ ዕለት ነው ፥ መቼም በተለምዶው መሰረት እንኳ ለልደታ የቃዠ ልጅ ወሩን ሙሉ ይባንናል እንደሚባለው ሁሉ መስከረም አንድ ብርሀንን የነሳ ድርጅትም ዓመቱን ሙሉ የጨለማ ዝርጋታ ልማዱን አጧጡፎ ቢቀጥለውስ? የሚል ስጋትን ያጭርብኛል! ይሄ በቀን መባቻ መረገም እኮ ክፉ ነገር ነው!
.
ደመራዬ ገኒ ፥ የከተራ በዓልን ልታከብር ነጠላዋን መስቀልያ አጣፍታ ትታየኛለች ! ህዝብ ከተሰበሰበበት አደባባይ መሀከል ቆማ ከዝማሬው ፥ ከደመራው መንቦልቦል ጋር አብራ ብርሀን እየሰጠች የምትዘምር ይመስለኛል! ጉልላት ዓይኖቿ በሚንቀለቀለው የእሳት ብርሀን ዳሰስ ተደርገው ስስ ጨለማ መልሶ ሲጋርዳቸው የሚታየው ትዕይንት ልብን ያነሆልላል!

ገኒን ላገኛት ይገባል ፥ ከጓደኞቿ ለይቻት የያዝኩላትን ስጦታ ብሰጣት እወዳለሁ ! የደመራውን ነበልባል በእኔ እቅፍ ውስጥ ሆና እያየች ልዩ ትዝታን ከልባችን ማህደር ቋጥረን እናስቀር ዘንድ እፈልጋለሁ ፤ ውዴ አንገትህ ስር ግብት ሲሉ ልክ እንደ ደመራው ወላፈን ገላህ ደስ የሚል ሙቀትን ይለግሳል እንድትለኝ እሻለሁ !

የኔ ፍቅር ከከናፍርሽ ድንበር ተላቀው የሚወጡት ቃላቶችሽ ደግሞ ለኔ ወላፈኔ ናቸው ብዬ በስሱ ጉንጮቻን እስማት ዘንድ ነው ምኞቴ!
መብራቱ ግን አለ ! ከስሙ ግብር ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ ፍቅራችንን በጉልበት ሊያደበዝዝ የሚተጋው የክፋት ውላጅ!
.
ገኒዬ መጣች ፥ ንፋሱ ነጠላዋን ያርገበግበዋል ፤ ግንባሯ ላይ የተነሰነችው ፀጉር ሰያፍ ተቀምጣ ከንፋሱ ጋር አብራ ትጫወታለች ፤ ሀጫ በረዶ በመሰሉት ጥርሶቿ ከነበልባሉ ጭስ ጋር አብረው የሚግተለተሉ ይመስላሉ!

ገኒ ደስታዬ ነች ፥ ገኒ ለኔ ስራዬን ማንቂያ ብርሀኔ ነች ፥ በርሷ ውስጥ ተፈጥሮን አያለሁ ፥ በርሷ ውስጥ ነገዬን እተነብያለሁ !
የትንቢቴና ሰናይ ተስፋን የምቋጥርባት ዕንቁዬ ደግሞ ማንንም ሳትሰማ ተንደርድራ ልታቅፈኝ እየሮጠች ነው! እፎይ እየመጣች እኮ ነው።
.
“አይሆንም ገነት ! አይኔ እያየ በገዛ መንደሬ ፥ እንደልቤ በምፈነጭበት መንደሬ ላይ ሆነሽ ለዛ መናኛ ደስታን ልትሰጪ አትቺዪም” ኤልፓ ነበር ስሙን ቄስ ይጥራውና እሱንማ አፌን ሞልቼ አባቱ ባወጣለት ስም አልጠራውም።

READ  አየር መንገዱ ከሳዑዲ ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያን በትኬት ዋጋ ላይ የ50 በመቶ ቅናሽ አደረገ

ውዴ ፍርሀት ሲሸብባት አየሁ ፥ ያን እብሪተኛ ንቆ መምጣት ለሷም ለኔም ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ተረድታዋለች መሰለኝ ……….
ገኒ በመጀመርያ ሩጫዋ ዝግ አለ ፥ ከዛ እንደመራመድም ሞከረች ……….. ያ ተንከሲስ በእጁ በትር ይዞ በድፍርስ አይኖቹ እያቁረጠረጠባት ነው! ……………… የኔ ፍቅር ይባስ ብላ ባለችበት ተገትራ ቀረች !

አይ ኤልፓ ፥ አንድዬ በደልህን ይይልህ ! በያንዳንዱ መሰናክሎች ውስጥ እድገቴን ፥ተስፋዬን እና ነገን ማያዬን እያኮሰስከው መሆኑ የማይገባህ ግዑዝ ነህ! አልኩኝ በሆዴ!
ገኒዬ ከሩቅ ታየኛለች ፥ ከእሳቱ ወላፈን ጋር እየፈካች ፥ ከሚግተለተለው ጢስ ጋር እየበነነች………………………………
.
ተፈፀመ!! DIRETUBE

Continue Reading

Art and Culture

በአዲስ አበባ ሁለት የነገሥታት መታሰቢያ ሐውልቶችና ሦስት ጥንታዊ ቤቶች እድሳት ሊጀመር ነው

Published

on

በአዲስ አበባ ሁለት የነገሥታት መታሰቢያ ሐውልቶችና ሦስት ጥንታዊ ቤቶች እድሳት ሊጀመር ነው

በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁለት የነገሥታት ሐውልቶችና ሦስት ጥንታዊ ቤቶች እድሳት ሊደረግላቸው መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

መንግስት ለሐውልቶቹና ለጥንታዊ ቤቶች እድሳት 30 ሚሊዮን ብር በጀት መድቧል፡፡

የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወርቁ መንገሻ እንደሚሉት በመዲናዋ ያሉ ታሪካዊ፣ባሕላዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን እያደሰ፣ እያስተዋወቀና አዳዲስ የመስህብ ቦታዎችን በማስፋት ላይ ነው።

የአጼ ምኒልክና የአጼ ቴዎድሮስ ሃውልቶች በተጀመረው በጀት ዓመት እድሳታቸው እንደሚደረግላቸው ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ የመጀመሪያው ከንቲባ ቢትወደድ ወልደ ጻድቅ ጎሹ መኖሪያ ቤት፣የሼክ ኦጄሌ አል ሀሰን ቤተ መንግሥትና በአሁኑ ጊዜ የአራዳ ፍርድ ቤት ሆኖ የሚያገለግለው የቀድሞው የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትም እድሳት ከሚደረግላቸው ጥንታዊ ቤቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ሁለቱ የነገሥታት ሐውልቶች 6 ሚሊዮን ብር ለእድሳት የተመደበላቸው ሲሆን፤ ሦስቱን ጥንታዊ ቤቶች ለማደስ ደግሞ 24 ሚሊዮን ብር በጀት እንደተያዘላቸውም ተናግረዋል።

 ሐውልቶቹ የተቀመጡት አደባባይ ላይ በመሆኑ ለጎብኚዎች የማይመቹ ቢሆንም የትራፊክ እንቅስቃሴውን በማያውክ መልኩ እንዲጎበኙ ይደረጋልም ብለዋል።

በቢሮው በ2007 ዓ.ም. ጀምሮ እድሳት ሊያደረግላቸው ከመረጣቸው ሐውልቶች መካከል የአቡነ ጴጥሮስ፣ የስድስት ኪሎ ሰማዕታትና የሚያዝያ 27 የድል መታሰቢያ ሐውልቶች የተጠገኑ ቢሆንም የአጼ ቴዎድሮስ ሴባስቶፖል መታሰቢያና የአጼ ሚኒልክ ሐውልቶች እስካሁን አልተጠገኑም።

ዝርዝር ጥናቱ ጊዜ መፈለጉንና የባቡር ግንባታው ለዕድሳቱ መዘግየት እንደምክንያት ጠቅሰውታል።

ታሪካዊ ቅርሶችንና ሐውልቶችን ይዘታቸው ሳይቀየር ማደስ የሚችል የባለሙያ እጥረትም ሌላው ለሐውልቶቹ ዕድሳት መዘግየት ምክንያት ነው። ena

READ  Africa Faces Economic Challenges but Raising High
Continue Reading

Art and Culture

የድሬ ቲዩብ መረጃ አዘል ጥያቄ – የኢሬቻ በዓል

Published

on

የድሬ ቲዩብ መረጃ አዘል ጥያቄ - የኢሬቻ በዓል

በየዓመቱ መስከረም 21 የሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሠላም እንዲከናወን አባገዳዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የዘንድሮው በዓል በታጠቀ ሀይል እንደማይታጀብ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው ላይ እንደማይኖር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ይህ ስምምነት ተገቢነቱን እንዴት ያዩታል?
ሠላምና መረጋጋት እንዳይጠፋ ከሕዝቡስ ምን ይጠበቃል ይላሉ?
እንደተለመደው መልሳችን ጨዋነት አይለየው | ድሬቲዩብ

READ  ስልጣን በያዙ ገና በአንድ ሳምንት አለምን ያናጉት ትራምፕ
Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!