Connect with us

Education

ቀን የጣለው መስከረም ሁለት፤| የዛሬው ቀን በታሪካችን ምዕራፍ፤

Published

on

ቀን የጣለው መስከረም ሁለት

ቀን የጣለው መስከረም ሁለት፤| የዛሬው ቀን በታሪካችን ምዕራፍ፤
(ሔኖክ ስዮም በድሬትዩብ)
(ከ፪፻፰ በድጋሜ የተለጠፈ)
——
ዛሬ ተራ ቀን ሆነ፡፡
ዛሬ ግን መስከረም ሁለት ቀን ነበር፡፡ በነበር ከቀሩ ባለታሪክ ቀኖች አንዱ መጨረሻው ይኽው የአዲስ ዓመት ማግስት ሆኖ ቀረ፡፡ በዘመኑ መስከረም ሁለት ማግስት አልነበረም፡፡ ይልቁንም መስከረም አንድ ዋዜማ ነበር፡፡

ሀገር ዳሷን ጥላ ሽር ጉድ የምትልበት ቀን መስከረም ሁለት እንዳልነበር ዛሬ ይህ ቀን የአዲሱ ዓመት ድባብ ሲነጋ የሚያንዣብብበት ሆነና አረፈው፡፡ መስከረም ሁለት ባለ አደባባይ ነው፡፡

መስከረም ሁለት ሰው ጎዳና የሚሞላበት የፌሽታ ቀን ነው፡፡ መስከረም ሁለት ሰማያዊ ለባሽ ኮሚኒስቶች ከፍ ካለው ስፋራ ቆመው ግራ እጃቸውን ወደ ሰማይ የወረወሩበት የደስታ ቀን ነው፡፡ ዛሬ አዘቦት ሆኗል፡፡ ተራውን ለነ ግንቦት ሃያ የሰጠ መጻተኛ ቀን፤ በዚህ ሰዓት በዚያ ዘመን ራዲዮ ስለ ድል ያወራል፡፡ ጥላሁን ገሰሰ ይለያል ዘንድሮ ይላል፡፡ ከያኒያን አብዮቱን በአብዮት አደባባይ ያደምቃሉ፡፡

የመጨረሻው ንጉስ መጨረሻ የሌለው ሐጢአት ይተነተናል፡፡ ቀኑ መስከረም ሁለት ነው፡፡ ሰዎች ማልደው ከየቤታቸው ወጥተው አብዮት አደባባይ ቆመዋል፡፡ አ.ኢ.ሴ.ማ.ዎች፣ መ.ኢ.ገ.ማ.ዎች፣ አ.ኢ.ወ.ማ.ዎች፣ ኢ.ሰ.ፓ.ዎች በዚህ ዘመን ብዙዎች አብዮት ተባሉ፡፡ መስከረም ከሰላሳው ቀን መገለጫነት ተገድቦ የመስከረም ሁለት መለያ የወል ስም ሆነ፡፡

ዛሬ አብዮት አደባባይ ቦታው እንጂ ስሙ የለም፡፡ ዛሬ ይሄ ግዙፍ የሀገሪቱ ጎዳና ደመራ ሲበራ ብቻ የሚደምቅ ስፍራ ሆኗል፡፡ ዛሬ መስከረም ሁለተኛው ቀን የበዓል ማግስት ብቻ ሆኖ በሌላ ትውልድ በአንጎቨር ሳቢያ እስከ ረፋድ የሚተኛበት ቀን ሆኖ አርፏል፡፡ ትናንትና በዚህ ቀን ማንም አይተኛም፤ መስከረም ሁለት በዘመኑ ማልዶ የሚቀሰቅስ የክት ቀን ነበር፡፡ ቀን ቀንን ጣለው፤ መስከረም ሁለት ከደመቀው ክቡሩ ወርዶ የዘመን መለወጫው ማግስት ሆነ፡፡

READ  የምታያቸውን ብቻ አይደሉም

 

የአብዮት ዘፈኖች ከቴሌቭዥን መስኮት ጠፍተው የቢራ ፋብሪካዎች የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት አጥለቀለቁን፤ የቀን እንጂ የሰው ጅግና የለውም ይሉት ብሂል መስከረም ሁለት ላይ ሰራ፡፡ እናቶች ለአብዮቱ በዓል የሀገር ልብሳቸውን አጥበው እንዳልተኮሱ ቆሸሸ ብለው የሚያወልቁበት ቀን ሆኖ አረፈው፡፡ ይህው ቀን ቀንን ሲጥል፡፡

ይህው መስከረም ሁለት እንኳን ነበር ሲሆን፡፡ በርግጥ የመስከረም ሁለተኛ ቀን ከብዙ የመስከረም ሁለት ቀኖች የሚለይበት ዘመንም ነበረው፡፡ ሀገሪቱ አስረኛውን የአብዮት በዓል ስታክብር፤ አቤት ያ መስከረም ሁለት፡፡ ምናልባት የመስከረም ሁለተኛ ቀን ሞገስ ተሟጦ ያለቀው ያን ቀን ተንጠፍጥፎ አልቆ ይሆን? ያኔ ሰማይ ምሽት ብርሃን ተፋ፣ ያኔ የጠረቤዛ ጨርቆች በውስኪ ራሱ፤ ያኔ ኢትዮጵያ ቀን ዘላ መስከረም ሁለት አዲሱን ዓመት ተቀበለች፡፡

ዛሬ መስከረም ሁለት ተራ ቀን ነው፡፡ ልናስበው ስንሻ ልንዘክረው ስንሞክር እንኳን አምጠን ነው፡፡ ግብሩም ክቡሩም ከዓይነ ህሊናችን ጠፍቷል፡፡ ስንተርከው የሚያደምጠን ትውልድ ርግጥ ከመስረም አንድ በልጦ ብሎ ሊጠይቀን ይችላል፡፡ መስከረም ሁለት ዛሬ ተራ ቀን ነው፡፡ ምናልባት የጥንት ጋዜጦች፣ የትዝታ እስረኞች፣ የአብዮት እሳቶች፣ የእሳቱ አመዶች በትዝታው ካልከነፉ የቀን ክፍ ሌላና ተራ ቀን አድርጎታል፡፡ ከአስራ አራት ዓመታት በላይ ግን የቀን አውራ ነበር፡፡

የዛሬው ቀን በታሪካችን ምዕራፍ፤ DIRETUBE

Continue Reading

Education

የመሰናዶ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

Elias Tesfaye

Published

on

የመሰናዶ መግቢያ

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅያ ወይም የመሰናዶ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

በ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅያ ወይም የመሰናዶ መግቢያ ፈተና(10ኛ ክፍል) ከግንቦት 23-25/2009 ዓ.ም ድረስ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ፈተናው ታርሞ ባለፈው ወር ውጤት በተቋማችን ዌብ ሳይትና በSMS ለተማሪዎች መለቀቁ ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎ የተማሪዎች ወደ መሰናዶ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ በ13/1/2010 ዓ.ም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሠረት ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች ወ 2.71 እና በላይ ሴ 2.57 እና በላይ ለታዳጊና አርብቶ አደር ክልል ተማሪዎች ወ 2.43 እና በላይ ሴ 2.29 እና በላይ መስማትና ማየት ለተሳናቸው ወ 2.14 እና በላይ ሴ 2.00 እና በላይ ለግል ተፈታኞች ወ 3.43 እና በላይ ሴ 3.14 እና በላይ መሆኑን ኤጀንሲው ያሳውቃል፡፡

NEAEA

READ  በአዲስ አበባ ከተማ ስድስት የመናፈሻ ፓርኮች ሊከፈቱ ነው ተባለ
Continue Reading

Art and Culture

የማህበረ ቅዱሳን የቴሌቨዥን ሥርጭት በቅዱስ ፓትረያሪኩ ታገደ

Published

on

የማህበረ ቅዱሳን የቴሌቨዥን ሥርጭት በቅዱስ ፓትረያሪኩ ታገደ

ሀራ ተዋህዶ ድረ-ገጽ፤ ሁለት ከነበሩት ኦርቶዶክሳዊ የቴሌቨዥን ቻናሎች የአንድ ባለቤት በመሆን በከፍታው ዘመን ዝቅ ብለናል፤
ቅሬታ ያደረባቸው ምዕመናን፤

በቅርቡ በአሌፍ ቴሌቨዥን ስርጭቱን የጀመረው የማህበረ ቅዱሳን የቴሌቨዥን ፕሮግራም በፓትረያሪኩ ትዕዛዝ ታገደ ሲል ሀራ ተዋህዶ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡

ሰኞ መስከረም 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ለመንበረ ፓትረያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የጻፍትን ደብዳቤ መነሻ በማድረግ ጽ/ቤቱ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአሌፍ ቴሌቨዥን፣ ለኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትና ለፌዴራል አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር በአድራሻ የተጻፈውን እገዳ በግልባጭ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የጠቅላይ ጽ/ቤት የሕግ አገልግሎትና አስተዳደር መምሪያ፣ የብሮድካስት ኤጀንሲ፣ ለፌዴራል ፖሊስና ለአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቀዋል ይላል የሀራ ተዋህዶ ዘገባ፡፡

የዘገባውን መውጣት ተከትሎ በርካታ ምዕመናን በሀገራችን ነጻ እምነት የማራመድ መብትን በመጠቀም ብዙ አማራጭ የፕሮቴስታንታውያን የቴሌቨዥን ቻናሎች በየቀኑ እየመጡ ባሉበት በዚህ ሰዓት ሦስት ሺ ዘመን እድሜን ያስቆጠረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 2010 ዓ.ም. በሁለት ቻናሎች ጀምራ መስከረም ሳይልቅ ተመልሳ ወደ አንድ ቻናል ባለቤት የገባችበት ሁኔታ የሚፈጠር ከሆን ያሳዝናል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ሌሎች ወገኖች ማህበሩ የቤተክርስቲያኗን ህግና ሥርዓት በመጠበቁ ያገኘው ምቹ ሁኔታ ቢኖር ስደት፣ ክልከላ፣ ጥላቻ እና ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው፡፡

በቅዱስ ሲኖዶሱ መልካም ስምና ቦታ ቢኖረውም በቤተክህነቱ አስተዳደር ግን የተጠላ የሆነበት ምስጢር ለምዕመኑ አልፈታ ያለ እንቆቅልሽ ሆኗል ይላሉ፡፡

ጉዳዮን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የህግ ምሁራን ግን እገዳው በቀና መንፈስ ከተጤነ አወዛጋቢ እንደሆነ ነው የሚገልጹት፡፡

እንደ ምክንያት የሚያስቀምጡት ደግሞ ማህበሩ በአሌፍ ጣቢያ የጀመረው የቴሌቨዥን ፕሮግራም እንደ አንድ የአየር ሰዓት ወስዶ እንደሚሰራ ተባባራ አዘጋጅ ወይም አምደኛ የሚታይ ሆኖ ሳለ ከዚህ በሚበልጥ ሁኔታ በህግ የራሱ ሚዲያ ኖሮት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ያላቸው የህትመት ውጤቶች የሚያዘጋጅና የሚያሳትም ማህበር በዚህ ፕሮግራም የተለየ ነገር ይፈጥራል በሚል ስጋት ውስጥ መግባቱ እርስ በእርሱ የማይጣጣም ሀሳብ መሆኑን ነው የሚጠቁሙት፡፡

READ  ወጣቱን ከአደንዛዥ እጽ ጉዳት ለመታደግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

እንደ ሀራ ተዋህዶ ድረ ገጽ ዘገባ ቅዱስ ፓትረያሪኩ መደበኛው የማህበረ ቅዱሳን አዲሱ የቴሌቨዥን ፕሮግራም እንዲታገድ ከጀርባ አሉ በሚል ያነሷቸው ግለሰቦች ተቋማት ስለመኖር አለመኖራቸው ለማጣራት ባደረግነው ሙኩራ ያገኘነው ተጫባጭ ማስረጃ የለም፡፡

DIRETUBE

 

Continue Reading

Business

የትምህርት ኢንቨስትመንት- ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ማጅራትን የመምታት ስልት

Published

on

የትምህርት ኢንቨስትመንት- ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ማጅራትን የመምታት ስልት

የትምህርት ኢንቨስትመንት- ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ማጅራትን የመምታት ስልት፤ ያው ጥራት የለም፣ ገንዘብ መቆጠብ የለም፡፡

ከስናፍቅሽ አዲስ

ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ ጀመሩ፡፡ ሊማሩ ከማለት ብር ሊያጠፉ የሚለው አይቀልም ብላችሁ ነው፡፡ የትምህርት ጉዳይ ፈተና ሆነብን፡፡

ይኼው በቅርቡ በአዲስ አበባ በተደረገ የመምህራን ምዘና ሃያ በመቶው እንኳን ማለፍ አቃታቸው ተባልን፡፡ እና ማን እያስተማረ ነው የመምህር ፍልሰት እየተባለ ዋጋው ጣራ የነካው?

የትምህርት ኢንቨስትመንት በመንግስታችን በበጎ መታየቱ ዜጎች የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ ነበር፡፡ ግን እኛ ጋር የደረሰው በየዓመቱ እንደ አርባ ስድሳ ተመዝጋቢ ብር ጨምሩ የሚለው ማቆሚያ የሌለው ዋጋ ጭማሪ ነው፡፡

በእርግጥ ብዙሃኑ የትምህርቱ መስክ ባለሃብቶች አንጀታቸው ድርብ ነው፡፡ አይሳሱም፡፡ የትም አይሄድም የተባለው ወላጅ መስከረም ሲጠባ ገንዘብ እንደሚጨምር ራሱን አሳምኖ እንዲኖር አድርገውታል፡፡

የኔ ሀሳብ መንግስት በትምህርት መስክ ለሚሰማሩ የውጪ ባለ ሀብቶች በተለይም ለህንዳውያን በሩን ከፍቶ የላቀ ማበረታቻ ቢሰጥ አሁን ካለው አሰቃቂ አደጋ የሚታደገን ይመስለኛል፡፡

አሁን ትምህርት ቤት የሚመዘገበው ወላጅ ነው፡፡ የሚወዳደረው ወላጅ ነው የሚል እምነት ያላቸው ሰዎች ተበራክተዋል፡፡

ዋጋው በጨመረ ትምህርት ቤት ማስተማር የደረጃ መገለጫ ተደርጎ እንዲወሰድ ለማድረግ በሚጥሩ ጥቂት ሰዎች ሳቢያ ህዝበ አዳም በልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ ሲያለቅስ ይኖራል፡፡

አንዳንዶች ዋጋም ቆልለው ትርፉ ሱስ ማልመድ ሆኖ በሰላም ከቤት የወጣው ልጅ ስለ ሀሺሽ ተምሮ ለሚመለስበት ዋናው ጥራት ነው እያሉ የተፈቀደ የማጅራት መቺነት ስልትን የተከተሉ ይመስለኛል፡፡

የኔታ በ50 ሣንቲም ፊደል ሲያስቆጥሩ የኖሩት ሀገር ለመገንባት ነው፡፡ ቤት እና ተማሪ ቤት አንድ ሰው አእምሮው በስጋት እንዲወጥ ያደረጉ የከተሜ ነዋሪዎች አበሳ ናቸው፡፡

READ  የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ጉብኝት በኢትዮጵያ

የኔታ ስለ ሀገር ግንባታ ያሰቡትን ያህል ማሰብ ያቃተው ኢንቨስትመንት ማንም ቢጮህ መስሚያ የለውም፡፡

እናም አዲስ አመት አዲስ የክፍያ ጭማሪ ግድ እየሆነ መጣ፡፡ ግዴታው በሰኔ ለመንግስት የመገበር ያህል የሚስማማበት ሰው ቁጥር በዝቶ ተቀባይነትን አገኘ፡፡

የት ድረስ እንደሚቀጥል እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ የመንግስት ሰራተኛው ልጁን መካከለኛ በሚባሉ የግል ትምህርት ቤቶች እንኳን ማስተማር አልቻለም፡፡

መንግስት ለትምህርት ዘርፍ ሰጠሁ የሚለው ማበረታቻ ለጥቂቶች ሀብት ማካበቻ እስኪሆን የብዙሃኑን ሰቀቀን አልታደገም፡፡ በዚህ ስሜት ውስጥ ይሄው መስከረም አዲሱ የትምህርት ዘመን ጀመረ፡፡ ልጅ ክፍል እየቆጠረ፤ ትምህርት ቤቱ ደግሞ ገንዘብ….

DIRETUBE

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!