Connect with us

Art and Culture

መስከረም ሁለት፤ እኔም እንደ ግንቦት ሃያ አድርጎኝ ነበር የሚለው ታላቅ ቀን

Published

on

መስከረም ሁለት፤ እኔም እንደ ግንቦት ሃያ አድርጎኝ ነበር የሚለው ታላቅ ቀን፡፡

መስከረም ሁለት፤ እኔም እንደ ግንቦት ሃያ አድርጎኝ ነበር የሚለው ታላቅ ቀን፡፡ | ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ዛሬን በትዝታ ወደ ትናንትና ሊወስደን ነው፡፡ ዛሬ መስከረም ሁለት ነው፡፡ ይህ ቀን በሀገራችን ወታደራዊ መንግስት ታሪክ ከቀናት ሁሉ የሚበልጠው ነበር፡፡ ሄኖክ ስዩም እንዲህ ያስታውሰዋል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

ዛሬ መስከረም ሁለት ነው፡፡ በእርግጥ አሁን የአውደ ዓመቱ ማግስት ነው፡፡ ትናንት ግን እንዲህ አልነበረም፡፡ የአውደ አመት ዕለት ቅርጫ መዋል ሳይሹ ከተማ ሲያስውቡ የሚውሉ አብዬተኞች ምትክ የሌለው በዓላቸው ነበር፡፡

መስከረም ሁለት የአብዮት በዓል ነው፡፡ መስከረም እና አብዮት በሚል ሀገር ያጥለቀለቁ ስሞች ለትዝታ ቀርተው ቀኑ አዘቦት የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡

መስቀል አደባባይ ስሙን ሳይቀር በአብዮቱ ተነጥቆ አብዮት አደባባይ ተብሎ የሚጠራ ስፍራ ነበር፡፡ ደመራ የሚበራው አብዮት አደባባይ ነው፡፡ አብዮትም የሚከበረው እዚሁ አብዮት አደባባይ፡፡

ይህ ቀን ከቀናቱ ሁሉ በላይ ስፍራ የሚሰጠው የአብዮቱ የልደትም የሰርግ ቀንም ነው፡፡ አብዮቱ ደግሞ በየዓመቱ የሚወለድ በየዓመቱ የሚዳር ቅንጡ ነበር፡፡

ዛሬ ሆኜ ሳስበው እንዲህ እላለሁ፡፡ ግንቦት ሃያ መስቀል አደባባይ ሲደምቅ፤ ቀን አንደበት ቢኖረው “እኛም እንዲህ አርጎን ነበር፡፡
ስሙ እና የቦታው ስም ተቀየረ እንጂ በመስቀል አደባባይ እንዲህ ሆኖ ያላለፈ ማን አለ?” ሲል የሚናገር አልያም በጦቢያ ወይም በሳተናው የሚጽፍ ይመስለኛል፡፡

ግንቦት ሃያ ምን ብሎ እንደሚመልስ መገመት አልችልም፡፡ ምናልባት እሱም ወይ በአዲስ ዘመን ወይ በእፎይታ ብዙ ይጽፍ ይሆናል፡፡ ግን ቀን አይናገርም፡፡ እናም እንናገርለታለን፡፡

የሰማይ ርችትና የአዲስ አበባን ሰው በማስተዋወቅ የመስከረም ሁለትን ያክል ባለ ውለታ ቀን የለም፡፡ ጎዳናዎችም ቢሆኑ መብራት በመብራት የመሆን አጀብ ያበዙት በዚህ ቀን ነው፡፡

READ  የአቪዬሽን አካዳሚው በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመረቀ

የንጉሡ የዘውድ በዓል በታሪክ ብዙ ቢባልለትም አስረኛው የአብዮት በዓል ግን ሌላ ነበር፡፡ ዛሬ ሰፈራችሁ የምታይዋቸው ታላላቅ ሰዎች እንደ አሁኖቹ ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ወደ አብዮት በዓሉ በሚጮህ ትራፊክ፣ በሚያርበደብድ ግርማ፣ በሚጋረፍ አጀብ የሚገቡ ናቸው፡፡

ይህንን ቀን ማንም ከአብዮት አደባባይ አይቀርም፡፡ የደርጉ ሹማምንት በሙሉ ከሱፍ በሚበልጥ ዋጋ የሚገዛውን ካኪ ለብሰው አብዮቱን ባለ ቀለም ያደርጉታል፡፡ ዛሬ ትዝታ እንኳን መሆን ያልቻለ ቀን መስከረም ሁለት ነው፡፡
ልጅን መስከረም ብሎ ልጣራ የሚል አባት አቤት የሚለው ልጅ አያገኝም፡፡ በወር ስም መጠራት ኋላ መቅረት ሆኗል፤ እውነት ይሁን ውሸት እንጇ እንጂ አንዱ ልጁን ህዳሴ ብሏታል የሚል ነገር ሰምቻለሁ፡፡

እውነት ከሆነ የመስከረም እና አብዮት የመባል ስም ማውጣት ባህሎች በህዳሴ ተተክተዋል ማለት ነው፡፡

የመስከረም መልካም ፍቅር ግን በልባችን ዛሬም አለ፡፡ ከመስከረም ሁለተኛዋን ቀን መርጦ በፍቅር የሚያብደው ልክፍት ሳይሆን ድፍን መስከረምን የሚሞሽረው መንፈስ ዛሬም ከእኛ ጋር ነው፡፡

ነገሥታት ያልፋሉ፡፡ ታሪክ እንደየዘመኑ ስፍራ ይዞ ስፍራውን ይለቃል፡፡ መስከረምና ኢትዮጵያውያን ግን በአበባ እንደደመቁ በቦታቸው ይኖራሉ፡፡ DIRETUBE

 

Continue Reading

Art and Culture

ወደ ዳንጉር ተራራ፤ ከማንቡክ እስከ ጉብላክ

Published

on

ወደ ዳንጉር ተራራ፤ ከማንቡክ እስከ ጉብላክ

ወደ ዳንጉር ተራራ፤ ከማንቡክ እስከ ጉብላክ | ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ዳንጉር ተራራ ይዞን ሊወጣ መተከል ዞን ገብቷል፡፡ በማንቡክ የነበረውን ቆይታ የጉብላክ ከተማን ድባብ እየተረከ ዳገቱን ይዞን ይወጣል፡፡ ስውሩ የተፈጥሮ መስህብ እስከ ዛሬስ የት ነበር? ብሎ ይጠይቃል፡፡ ቋንቋ አብሮ ለመኖር እንቅፋት የማይሆንበትን አኗኗርን እንዲህ ያስጎበኘናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

ማንቦጓ የሚለው ቃል የመጣው ከጉምዝኛ ነው፡፡ መዋቢያ ማለት ነው ትርጉሙ፡፡ ማንቦጓ የሚለው ቃል ደግሞ ማንቡክን ወለደ፡፡ እኔ ማንቡክ ነኝ፡፡

በአሶሳ በኩል ነው የመጣሁት 379 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዤ እዚህ ደርሻለሁ፡፡ ያለሁባት ከተማ ስያሜዋን ያገኘችው ከማንቡክ ወንዝ ነው፡፡

የጉምዝ ሴቶች ወደ ወንዙ እየወረዱ ከሚዋቡበት፤ እናም ወንዙን ማንቦጓ ሲሉ መዋቢያ አሉት፡፡ ማንቡክ ከዚህ ቃል ተገኘ፡፡

ዳንጉር ነኝ፡፡ መተከል ገብቻለሁ፡፡ እዚህ ብዙ ተሸሽጎ የኖረ መስህብ አለ፡፡ እዚህ ምንም ያልተነገረለት ተአምር ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ የጠንካራ ገበሬዎች ከተማ በጠዋት ትነቃለች፡፡ ሲያቅላላ የታረደው በሬ ጸሐይ ስትወጣ ትዝታውም አይተርፍ፡፡ እንዲህ ናቸው ስጋ ቤቶቿ፤ ብዙው ሱቅ ከግብርና የተቆራኘ ነው፡፡ ብዙ ሰው የሚያወጋችሁ ምድር ምን ያህል ፍሬ እንደሰጠችው ነው፡፡ ብዙ ቋንቋ የሚሰማባት ከተማ ናት፡፡

የሰው ልጆች ከተማ፤ 838700 ሄክታር ቆዳ ስፋት ካለው ዳንጉር ወረዳ ብዙው ቆላማ ነው፡፡ ሦስት እጁ ቆላማ በሆነበት ምድር ደግሞ ሃያ በመቶ የሚሆን አስደናቂ ደጋ ምድር አለ፡፡ ማንቡክ ግን ሞቃታማ ናት፡፡

በ1962 ዓ.ም. ነበር ከተማ ሆና የተቆረቆረችው፡፡ ከከተማዋ ታሪክ ጋር ባለውለታ ሆነው ፊታውራሪ ኢያሱ ዘለቀ እና አቶ ተፈራ ሆሬ ስማቸው ጎልቶ ይነሳል፡፡ ማንቡክን በጠዋት ለቅቄ መንገድ ጀመርኩ፡፡ ቀጥዬ የምንደረደርባት ከተማ ጉብላክ ነች፡፡

READ  ሁለት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የሮቦቶች እግር ኳስ ግጥሚያ አሰናድተዋል

ጉብላክ ከማንቡክ በበለጠ ለግብርና ሕይወት ትቀርባለች፡፡ ሁለ ተገሯ ከምድር ፍሬ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ እዚህም እዚያም ሰሊጥ በቆሎ ማሽላ ነው ጨዋታው፡፡ ትራክተሮች ማየት ብርቅ አይደለም፡፡ የማሳ ላይ ውሎ አላደርስ ብሏቸው የነተበ ልብሳቸውን አላወልቅ ያሉ ብርቱዎች ወዛም ያደረጓት ከተማ ናት፡፡

ጉብላክ ሰባ በመቶ ምድሩ ሜዳማ ለሆነው ዳንጉር አንድ ማሳያ ናት፡፡ ሩቅ ድረስ በተዘረጉ የእርሻ ማሳዎች ተከባለች፡፡ ከጉብላክ እስከ ድባጉያ እጓዛለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በእግር ነው፡፡

ለብዙ ሰዓታት በእግር መጓዝ፤ ወደ ዳንጉር ተራራ አናት መውጣት፤ ከዳንጉር አናት ሆኖ ትይዩውን በላያን ማየት፤ እድሜ ጠገቡን ገዳም መጎብኘት፤ የደገኛውን ምድር እስክጠግበው መቆየት፡፡ ወደዚያው ለመሄድ መንገድ ላይ ነኝ፡፡ DireTube

Continue Reading

Art and Culture

“ህዳር ሲታጣን” በዚህ ዘመን….

Published

on

“ህዳር ሲታጣን” በዚህ ዘመን….

ከ100 ዓመታት በፊት በአገራችን በህዳር ወር ተከስቶ የበረው የኢንፍሉዌንዛ በሽታ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰው ህይወት እንዳጠፋ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

በዘመኑ የነበሩት ነግስታት የበሽታውን ስያሜ “የህዳር በሽታ” ብለው በሽታው በቀላሉ ሊስፋፋ የሚችለው ደግሞ ከጽዳት ጉድለት መሆኑን ለህዝብ በማስገንዘብ ነዋሪዎች የመንደራቸውን ቆሻሻ እያሰባሰቡ በማቃጠል በሽታውን ለመከላከል እንዲዘምት በአዋጅ አዘዙ።

ይህ የቆሻሻ ማቃጠልና በጭስ የማጠኑ ልምድ በጊዜው የነበረውን በሽታ በማጥፋት ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ቢሆንም አሁን የምናቃጥላቸው ፌስታልና የተለያዩ ኬሚካል ያላቸው ቁሶች የከባቢ ሙቀት መጨመርን የሚያባብስ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

በዘንድሮው ህዳር 12 ማለዳም አዲስ አበባ በግራጫማ ጭስ ታፍና ተስተውላለች፡፡

በጉዳዩ ላይ ያለዎት ሀሳብ አስተያየት ያካፍሉን!!  ebc

READ  የሚያዝበት ገንዘብ በባንክ ሳይኖረው ቼክ በመጻፍ ያታለለው ግለሰብ ተቀጣ
Continue Reading

Art and Culture

የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከፊት መምጣት

Published

on

የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከፊት መምጣት

የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከፊት መምጣት፤ የኦቦ ለማ መገርሳ ካቢኔ ሩቅ አሳቢነት እና የኦሮሞ ባህል ጥላቻን የመጥላት እሴት | ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የኦዳ ትራንስፖርት የብስራት ጉባኤ ላይ ከፊት ታይተዋል፡፡ ጎናቸው ያሉት ያሳደጓቸው የፖለቲካ ልጆች ናቸው፡፡ በርሃ ሳሉ አይተዋወቁም፡፡ የበርሃ ጓዱን ለእግዜሃር ሰላምታ ዓይኑን አያሳየኝ በሚል የፖለቲካ ሜዳ ሌላ ዓይነት ጨዋታ ማየታችን አጃኢብ አስብሎን ከርሟል፡፡

እውነቱ ግን ኦሮሚያን የሚመሯት የኦሮሞ ልጆች መሆናቸው ነው፡፡ አንድ መሪ የሚመራው ሕዝብ አብራክ ክፋይ ሲሆን ባህሉን ያከብራል፡፡ እንደ ባህሉ ይኖራል፡፡ ከሀገር ወግ አያፈነግጥም፡፡

እኔ በኦዳ ትራንስፖርት ጉባኤ ላይ ነጋሶን ከነ ለማ ጋር አብሬ ሳያቸው የገባኝ የገዳ ሥርዓት እሴት ምን ያህል ታላቅ መሆኑን ነው፡፡ በሀሳብ ልትለያይ ትችላለህ ግን ጠላት አይደለህም፡፡

ኦሮሚያን በመምራት በኩል የኦሮሞን ባህል አውቆ እንደ ኦሮሞ በመምራት ረገድ የተሳካላቸው መሪ አባዱላ ነበሩ፡፡ ግን እሳቸው በዚያን ወቅት ብቻቸውን ናቸው፡፡ ዛሬ ድፍን ካቢኔው ሊባል በሚችል መልኩ የአባቶቹን ወግ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ የአባቶቹ ወግ ደግሞ ጥላቻን ይጠላል፡፡

እናም እንደ ገዳ ባህል ወንድም ወንድሙን አይጠላም፡፡ ሀሳቡን ስለ ጠላ ወንድሙን አያሳድም፡፡ የዶክተር ነጋሶ ከፊት መምጣት ምስጢሩ ይሄ ይመስለኛል፡፡ ያም ሆኖ በጥላቻ ፖለቲካ መጠጥ የሰከርን ስለሆነ በሆነው ነገር ደንግጠናል፡፡ ተገርመን አላበቃንም፤ አሰላስለን አልጨረስንም፡፡

ዶክተሩ በምን አግባብ ዳግም በኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ እንደ አንድ ኦሮሞ በጉባኤ እንግዳ ሆነው ይታደማሉ ብለን እናስብ ነበር፡፡ አዲስ ትውልድ መጣና አደረገው፡፡ በዶክተሩ ቋንቋ ስንጠቀም፤ መንግስቱ ሃይለማርያምን የማይመስል አዲስ ትውልድ፡፡ ይሄ ሌሎቹም ጋር ቢለመድ መልካም ነበር፡፡ ግን ውሃ መውቀጥ ስለሆነ አልናፍቀውም፡፡ ኦሮሚያ ይቀጥል ዘንድ ግን እመኛለሁ፡፡

READ  የማንጎ ተክል ከውጭ በገቡ ነፍሳት አደጋ ላይ ወድቋል ተባለ

ኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ብዙ ዓመታት ቀድማ የጀመረች ሀገር ናት ብለን ስንሟገት ማስረጃችን ገዳ ነው፡፡ ሀሳብ እንጂ ሰው እንደማይገፋ ማሳያ የሆነው ይህ ባህል የገዳ ስርዓት እሴት የፈጠረው ነው፡፡ እናም ደስ ያሰኛል፡፡

ኦህዴድ ቀጥሎ ስለ ዶክተሩ ህልውና ያስብበት፡፡ ተገፍተዋል፡፡ እንደ አንድ ተራ ሀገር ዘራፊ ካድሬ እንኳን የሚታዩ አይደሉም፡፡ ርዕሰ ብሔሩ በብዙ ችግሮች ውስጥ ናቸው፡፡

ትናንትናቸውን ማሰብ ባይቻል እንኳን ጀርመንን ከመሰለች ሀገር ከሞቀ ህይወት የሰው ሀገር ሰው ጭምር ይዘው ሀገር አለኝ ብለው የመጡት የኦሮሞን ህዝብ ለማገልገል እንጂ የጀመሩት ትምህርት አላልቅ ብሏቸው አሊያም፤ ከዚች ሀገር ስራ ፍለጋ አይደለምና፤ አርቀን በማሰብ ትውልድ የሚኮራበት ስራ እንስራ፡፡ DireTube

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close