ሙክታር እድሪስ ወርቅ ሲያመጣ ዮሚፍ ቀጀልቻ የውድድሩ ኮከብ ሆኖ አመሸ

0
ሙክታር እድሪስ

“ውድድሩ ሲያልቅ የሞ ፋራን የደስታ አገላለፅ የተጠቀምኩት ለሱ ያለኝን አክብሮት ለመግለፅ ነው፣ እርሱ ብዙ ውድድር አሸንፎአል አሁን ግን ጊዜው የእኔ ነው” በለንደን የአለም ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን ወርቅ ሜዳሊያ ማምጣት የቻለው ሙክታር እድሪስ

በርካቶች ሞ ፋራ በድርብ ድል ከውድድር እንደሚሰናበት ቅድመ ግምታቸውን በሰጡበት ውድድር ሙክታር ግምቱን ሁሉ ውድቅ አድርጎ አዲስ ታሪክ ፅፎአል፡፡

ኢትዮጵያውን ወደ ውድድሩ ይዘውት የገቡት እቅድ ሰርቶላቸዋል፣ ዮሚፍ ቀጀልቻ ቀድሞ በመውጣት ውድድሩን ሲያፈጥን ሙክታር እድሪስ እስከ 200 ሜትር ድረስ ፍጥነቱን ጨምሮ ለማምለጥ እየተዘጋጀ ነበር፣ ሲል ሶስተኛ የወጣው በትውልድ ኬንያዊው በዜግነት አሜሪካዊ የሆነው ፓውሎ ቺሊሞ የኢትዮጵያ ቡድን የተከተሉትን ታክቲክ በአድናቆት አውርቶአል፡፡

Watch Video Here

ፈጣን ባልነበረው በታክቲክ በታጠረው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውን አሰልጣኞች እና አትሌቶች ከ አዲስ አበባ እስከ ታወር ሂል ለንደን ሆቴላቸው የዘለቀ ሞ ፋራን እንዴት እናቁመው ምክክር ተሳክቶላቸዋል፣ በውድድሩ በተለይ ዮሚፍ ቀጀልቻ ውድድሩን በማፍጠን የሞ ፋራን ታክቲክ በማበላሸት እና ከውድድሩ በፊት የተዘጋጁት እቅድ ወርቅ ይዞ እንዲወጣ አድርጎታል፡፡

ለዚህ ውድድር ከሚገባው በላይ ተዘጋጅተናል፣ ያለው ሙክታር እድሪስ ሞ ፋራን እንደምሸናፈው አውቅ ነበር፣ ሞ ፋራ አስር ሺህ ሜትር መሮጡን ተከትሎ መጨረሻ ዙር ላይ ሊደክም እንደማይችል ገምቼ ነበር፣ በመጨረሻዎቹ ሜትሮችም ሊደርስብኝ አልቻለም ብሏል፡፡

ጠንካራ ስራ ታላቅ ታጋሽነት ብሎም በራስ መተማመን የወለደው ሙክታር እድሪስ ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን ወርቅ አምጥቶአል፣ በትራክ ውድድር የመሰናበቻ ውድድሩን ያደረገው ሞ ፋራ በተለይ የኢትዮጵያውያን የውድድር እቅድ በሚገባ ተሳክቶላቸዋል፣ አንዳቸው (ዮሚፍ ቀጀልቻ) እራሱን መስዋእት በማድረግ ውድድሩን ከባድ አድርገውታል ሲል ተናግሮአል፡፡

READ  በአውስትራሊያ ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ሴሪና ዊሊያምስ ታላቋ ቬነስ ዊልያምስን አሸንፋለች

አሜሪካዊው ፓውል ቼሊሞ ሶስተኛ ሲወጣ ዮሚፍ ቀጀልቻ አራተኛ ሰለሞን ባረጋ አምስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡ DireTube Sport

NO COMMENTS